ወደ ታይላንድ ዋና ከተማ ባንኮክ ሊጓጓዝ የነበረ 400 ሺህ ዶላር የሚያወጣ 4 ኪሎግራም ኮኬይን በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ በቁጥጥር ሥር ማዋሉን የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት አስታወቀ።
አገልግሎቱ ለኢቲቪ በላከው መረጃ እንደገለጸው በዛሬው ዕለት ከቀኑ 7 ሰዓት ላይ አንድ ኢትዮጵያዊ 4 ኪሎ ግራም ኮኬይን የተባለ አደንዛዥ ዕጽ በማይሰራ ላፕቶፕ ቦርሳ ውስጥ ደብቆ ለማሳለፍ ሲሞክር በቀጥጥር ሥር ውሏል።
ተጠርጣሪው ከአዲስ አበባ ወደ ባንኮክ በላፕቶፕ ቦርሳ ለማሳለፍ የሞከረው አራት ኪሎ ግራም ኮኬይን በኤክስሬይ ፍተሻ አማካኝነት የተያዘ ሲሆን፤ በወንጀል ድርጊቱ ተባባሪ እንደሆኑ የተጠረጠሩ ሌሎች ሶሰት ግለሰቦችም እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተገልጿል።
በወንጀል ድርጊቱ የተሳተፉት አራት ተጠርጣሪዎችና አደንዛዥ ዕፁ ለተጨማሪ ምርመራ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን የፀረ አደገኛ ዕፅ መምሪያ መላካቸውም ተመልክቷል።
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply