ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከልን ዛሬ (እሁድ) መርቀው ከፍተዋል። ማዕከሉ በጠቅላይ ሚኒስትሩ ሀሳብ አመንጪነት በ2012 ዓ.ም የተቋቋመ ነው። አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማሽኖች ሰው ሰራሽ የሆነ የማሰብ ክህሎትን በተለያዩ የስራ መስኮች የሚያሰማራ ቴክኖሎጂ ነው። ሙሉ ለሙሉ ራሳቸውን ችለው ለሰው ልጅ አድካሚ የሆኑ ተግባራትን በፍጥነት ማከናወን ያስችላል በማት ኢዜአ ዘግቧል። በኢትዮጵያም የተቋቋመው ማዕከል ለግብርና፣ የትምህርት፣ ጤና እንዲሁም ለህብረተሰብ ጥበቃና ደህንነት አገልግሎቶች ይውላል። ማዕከሉ ከተቋቋመ አጭር ጊዜ ቢሆነውም አሁን ላይ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ የተደገፉ የጡት ካንሰርና የጭንቅላት ዕጢ መለየት በሚያስችሉ መተግበሪያዎች እየሰራ ይገኛል። ጎልጉል የድገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ማዕከል በኢትዮጵያ ተከፈተ