አቶ ልደቱ አያሌው የፖለቲካ ህይወቱን አሀዱ ብሎ የጀመረው 1983ዓ.ም. ህወሃት/ኢህአዴግ አዲስ አበባን ከተቆጣጠረ በኋላ የከተማዋን ወጣቶች የማደራጀት ስራ ላይ ከተሰማሩ ወጣቶች አንዱ ሆኖ ነው። በዚያ ወቅት ወጣቱ ልደቱ ለወያኔ መንግስት የመወገን ጫና በነበረበት የወጣት ማህበር ምስረታ ሂደት ንቁ ተዋናይ ነበረ። በመሆኑም የማህበሩ ሊቀመንበር የመሆን ፍላጎት እንደነበረው በወቅቱ አብረውት የነበሩ የመሰከሩት ነገር ነው። ነገር ግን በ1990 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ወጣቶች ማህበር በይፋ ሲመሰረት ወጣቱን በማደራጀት ምንም ተሳትፎ ያልነበረው የዳዊት ዮሃንስ (አፈጉባዔ የነበረ) ሚስት ወንድም የሆነው ወጣት ታጠቅ ካሳ ሊቀመንበር ሆኖ ተመረጠ። ይሄኔ ነው እንግድህ የልደቱ የመጀመሪያው የፖለቲካ አቋም እጥፋት የተጀመረው። የታጠቅን በሊቀመንበርነት መመረጥ አሚን ብሎ መቀበል አልፈለገም። … [Read more...] about ልደቱ አያሌውን ስድስት ነገሮች ሆነው ይሆናል በሉት
Opinions
የኔ ሃሳብ
የ360 ሤራ “ተንታኞች” መከፋፈል – “ጅብ ደም ከታየበት በጅቦች ይበላል”
ቁጭ ብዬ ናሽናል ጂኦግራፊክ ስመለከት ጅቦች አየሁ። አንድ ጎረምሳ አንበሳ ይተናኮላሉ። አንበሳው እየገላመጠ መንጋጋውን እያጓራ ያሳያቸዋል። ራሱን ለመከላከል ብዙም ያልተጨነቀው አንበሳ እየተቆጣና እየተገላመጠ ሲራመድ ጅቦቹ የልብ ልብ ተሰማቸው። ጅቦች አንበሳን ሊበሉ ቋመጡ። በመካከሉ አንዱ ጅብ ዘልቆ ሲገባ አንበሳው ተወናጭፎ መቀመጫው አካባቢ ነከሰው። ይህኔ የተነከሰው ጅብ ጩኸቱን አምባረቀ። አንበሳው በጣም ተናዶ ጉልበቱን ማሳየት ሲጀምር ጅቦች አፈገፈጉ። ይህን ጊዜ የተነከሰውን ጅብ መቀመጫ የማየት ዕድል የገጠማቸው ጅቦች አንበሳውን ትተው “ወንድማቸውን” ያሳድዱ ጀመር። አባረው ያዙት። አንበሳው በነከሰው በኩል የሚፈሰውን ደም ተከትለው በደቦ በሉት። ጅብ ሌላው ጅብ ላይ ደም ካየ አይምርም። ደም ሲደማ ሆዱ እንደሚሞላ ስለሚያውቅ ማድማት ወይም በደማው በኩል ገብቶ … [Read more...] about የ360 ሤራ “ተንታኞች” መከፋፈል – “ጅብ ደም ከታየበት በጅቦች ይበላል”
ወንድማማቾቹ የኢትዮጵያ ዘማቾች
ወጣት አለኸኝ ይመኑ እና ወጣት ግርማ ብሩ ከአንድ ማህጸን የተወለዱ ወንድማማቾች ናቸው። ውልደትና እድገታቸው ደግሞ በአዳማ አቅራቢያ በሚገኘው ልዩ ስሙ ቆቃ በተባለው አካባቢ ነው። ምንም እንኳን የእናት አንጀት ለልጆቿ ምን ያህል እንደሚራራ ቢተወቅም አገር ጥሪ ባቀረበች ጊዜ ግን ከሰንደቅ ዓላማ የሚበልጥ የለምና ኢትዮጵያን ከጠላት እንዲታደጉ እናታቸው መርቀው በደስታ ለውትድርና እንደላኳቸው ይናገራሉ።ቤተሰብና የአካባቢው ሰዎችም ልጆቻቸው ለአገር መከታ ይሆኑ ዘንድ በምርቃትና በደስታ ሸኝተዋቸዋል። (ኢብኮ) ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ … [Read more...] about ወንድማማቾቹ የኢትዮጵያ ዘማቾች
ትውስታ ዘ ዳንሻ – ታላቁ ጥቁር!
አምስተኛ መካናይዝድ ክፍለጦር ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ እንደ ወትሮው ከዋርድያዋች ውጭ ሁሉም ተኝቷል። አንድ ታላቅ ፣ ጥቀር የሌሊት ልብሱን እንደ ለበሰ መፅሃፍ ያነባል ድንገት የቶክስ ድምፅ ሰማ በአካባቢው ሁሌም የቶክስ ድምፅ መስማት የተለመደ ቢሆንም ወታደር ነውና ምልልስ ካለ ብሎ ለማዳመጥ ሞከረ ከሁለት አቅጣጫ መሆኑን ተረዳ። ስልኩን አነሳ ወደተለያየ ቦታ ደወለ ሁሉም አይሰራም ስልኩን አየው ኔትወርክ የለውም አሁን ችግር እንዳለ ተራዳ ካለበት ክፍል ግድግዳ እየታከከ ወደ በሩ ተጠጋና በሩን ሲከፍተው የተመታ ጓዱ ከነክላሹ በጀርባው ወደቀ ወዲያው የቶክስ ሩምታ ወደ በሩ አቅጣጫ ተከፈተበት እንደምንም ከወደቀው ጓዱ ካላሹን ተቀብሎ እየተኮሰ በቅርብ ቀን ወደተሰራች የብሎኬት ግቢ ዘሎ ገባ። በግቢው ውስጥ አንደ ገባ የራሱ ጓድ የሆነች ሴት ወታደር በብሎኬት አጥር ቀዳዳ … [Read more...] about ትውስታ ዘ ዳንሻ – ታላቁ ጥቁር!
ጥቁር ውሃ ላይ አስጨርሶ፣ እንደገና የፈረጠጠው ጄኔራል ከበደ ፈቃዱ ማን ነው?
የህወሃቱ ታጋይ ጄ/ል ከበደ በ1988 ዓም የ31ኛ ክ/ጦር 3ኛ ብርጌድ ፓራ ኮማንዶ፣ የ1ኛ ሻለቃ አዛዥ ሆኖ ሰርቷል። በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት በ31ኛ ክ/ጦር ምክትል ብርጌድ አዛዥ ሆኖ አገልግሏል። በ1992 ዓም 35ኛ ክ/ጦር ስትፈጠር የ35ኛ ክ/ጦር 3ኛ ብርጌድ አዛዥ ሆኖ ተሹሟል። በ1997 ዓም ኮር የሚባለው አጀረጃጀት ፈርሶ ዕዝ የሚባል አደረጃጀት ሲቋቋም፣ ግለሰብ የ35ኛ ክ/ጦር ም/አዛዥ ቀጥሎም የ33ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ሆኖ እስከ 2006 ዓ/ም ሠርቷል። በ2006 ዓ/ም እነ ጄኔራል አበባው ታደሰን ለማስወጣት በተደረገው ግምገማ፣ ግለሰቡ የአበባው አሽከር ነህ ተብሎ ተፈርጇል። ይህን ተከትሎም ከክፍለ ጦር አዛዥነቱ ተነስቶ፣ የዕዙ ማሰልጠኛ ት/ት ቤት አዛዥ ሆኖ ተመድቧል። የጡረታው ጊዜ ሲደርስ “ተጠቅሞ ይውጣ” ተባለና … [Read more...] about ጥቁር ውሃ ላይ አስጨርሶ፣ እንደገና የፈረጠጠው ጄኔራል ከበደ ፈቃዱ ማን ነው?
የትግራይ ጉዳይ፤ በረከተ መርገም!
የኢትዮጵያ መንግሥት ሰኔ 21 ቀን ያወጀውን የትግራይ ክልል የተኩስ አቁም አዋጅ በተመለከተ የተለያዩ ሀሳቦች እየተሠነዘሩ ይገኛሉ። እንደ እውነቱ ከሆነ መንግስት መተቸት ያለበት በመዘግየቱ ነው። የሕግ ማስከበር ዘመቻው በተጠቃለለ በሳምንታት ጊዜ ውስጥ የተኩስ አቁም አዋጁን አውጆ ወደ ፖለቲካዊ መፍትሄ ቢያመራ መልካም ነበር። ምናልባት ግን ከፊት ለፊቱ የነበረው ሐገራዊ ምርጫ ውሳኔውን እንዲያዘገይ እንዳደረገው ይታመናል። የኢትዮጵያ መንግስት ከዚህ በላይ የትግራይን ጉዳይ መሸከም አልነበረበትም። ቀድሞም የተለያዩ የውስጥና የውጭ አካላት ይሄንን ጉዳይ አንስተው ሞግተዋል። አውሮፓና አሜሪካ ጠንካራ ማእቀብ ለመጣል እየተዘጋጁ ነው። ይህ ማእቀብ የኢትዮጵያን ምርቶች እስካለመግዛት የሚደርስ ነው። ይህ ሁኔታ ለኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ከባድ ሸክም ነው። አሜሪካና የአውሮፓ ህብረት የትግራይ ችግር … [Read more...] about የትግራይ ጉዳይ፤ በረከተ መርገም!
ጩኸት ያፈናት ከተማ
የድምጽ ብክለት መጨመር የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን ለምሬት እየዳረገ ይገኛል፡፡ ከመጠን ያለፉት ረባሽ ድምጾች፡- ከንግድ ትርኢቶች፣ ከሐይማኖት ተቋማት፣ ከምጽዋት ጠያቂዎች፣ ከጎዳና ላይ ንግድ፣ ከምግብና መጠጥ ቤቶች፣ ጋራዥ፣ እንጨት ቤት እና ብረት ቤትን ከመሰሉ አገልግሎት ሰጪዎች፣ ከፊልምና ሙዚቃ መሸጫዎች፣ ከተሽከርካሪዎች እና ከመሳሰሉት ይመነጫሉ፡፡ ለመሆኑ የድምጽ ብክለት ማለት ምን ማለት ነው? ምን ጉዳት ያስከትላል? እንዴት መቆጣጠር ይቻላል? የሚለውን ጥያቄ አንስተናል፡፡ በዚህ ጽሑፍ የባለሙያዎች አስተያየት እና የተጎጂዎች ሐሳብ ተካቷል፡፡ "የድምፅ ብክለት መደበኛውን የሕይወታችንን እንቅስቃሴ ይጎዳል፣ ያስተጓጉላል፣ እንቅልፍ ይነሳል፤ ውይይቶቻችንንና መደማመጣችንን ይቀንሣል፣ በአጠቃላይ የአኗኗራችን ሁኔታ የተረበሸ እንዲሆን ያደርጋል።” የሚሉት የቀድሞ የኢትዮጵያ … [Read more...] about ጩኸት ያፈናት ከተማ
ተፈትነን እንጂ ወድቀን አናውቅም
ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን ፈተና ውስጥ ነን። ይሁን እንጂ እንደ ሀገር እና እንደ ህዝብ ተፈትነን እንጂ ወድቀን አናውቅም። “ኢትዮጵያን የመበታተኛው ሰአት አሁን ነው” - ግብጽና ሱዳን። ክፍል አንድ - መነሻ ሀገራችን የአፍሪካ የውሃ ማማ “the water tower of Africa” ይሏታል። ብዙ ሀይቆች አሏት፤ ብዙ ወንዞች አሏት። ምድር የተሸከመችው ትልቁ ወንዝ አባይ አላት። ብዙዎቹ የውሀ ሀብታምነታችንን ሲነግሩን እኛም ስንዘፍንለት፣ ለልጆቻችን በየተረቱና በየጂኦግራፊ ትምህርቱ ስናስተምረው ቆይተናል፤ ኖረናል። “አባይ አባይ፣ የሀገር ሀብት የሀገር ሰላይ” “አባይ ጉደል ብለው፣ አለኝ በትህሳስ፤ የማን ልብ ይችላል፣ እስከዚያው ድረስ።” ስለተፈጥሮ ሀብታችን ስንዘምርና ስንተርት አድገን፣ ሀገራችንን የድርቅና ረሃብ ምሳሌ ሆና መዝገበ ቃላት ውስጥ … [Read more...] about ተፈትነን እንጂ ወድቀን አናውቅም
ኤርሚያስ ለገሰ “የወያኔ የፕሮፖጋንዳ ሰራተኛ እያለ የለመደው የቁጥር ጫወታ አለቀቀውም”
የቀድሞው ኢህአዴግ ካድሬዎች እና የህወሓት ጀነራሎች ሂሳብ አስተማሪው ኤርሚያስ ለገሰ ሆን ብሎ በቁጥር ሊጫወት ሞክሯል፡፡ አላማው ኢዜማ የክልል ምክር ቤት ወንበሮችን ሊያሸንፍ እንደማይችል አስመስሎ መሳል ነው፡፡ ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ ሆኖበት ነው፡፡ ኤርምያስ ሹመት አስቦ የለውጡ ደጋፊ የነበረ ጊዜ የተናገረው የወያኔ የፕሮፖጋንዳ ሰራተኛ እያለ የለመደው የቁጥር ጫወታ አለቀቀውም፡፡ ምናልባት እንዲገባው ከዚህ በፊት ከነበረው የተቃዋሚዎች ዕጩዎች ቁጥር በ11% እድገት አሳይተናል እንበለው ይሆን?? ምንም እንኳን [ለእንደዚ አይነቱ አውቆ አበድ መፍትሄው] ንቆ መተው ቢሆንም ያቀረበውን የተንኮል መረጃ እንደ እውነት ሊወስዱ የሚችሉ ቅኖችን ከስህተት ለማዳን ዝርዝር መረጃውን ከዚህ በታች አቅርቤዋለሁ፡፡ ምርጫ የሚደረገው በዘጠኝ ክልሎች እና በሁለት ከተማ አስተዳደሮች … [Read more...] about ኤርሚያስ ለገሰ “የወያኔ የፕሮፖጋንዳ ሰራተኛ እያለ የለመደው የቁጥር ጫወታ አለቀቀውም”
ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር
እንደምን ሰነበታችሁ! እንኳን በጤና ተገናኘን! “በሚኖሩባት ሰዎች ክፋት የተነሳ ፍሬያማዋን ምድር ጨው አደረጋት” የሚል ቃል በቅዱሱ መጽሀፍ ውስጥ ሰፍሯል።ሕዝብ መቼም ቢሆን ክፉ ሆኖ አያውቅም፤ አይሆንምም። ነገር ግን ከሕዝብ የወጡ ጥቂቶች በዕኩይ ዓላማና ምግባራቸው ምድሪቱን ለጥፋት፣ ሕዝቡንም ለስቃይ ይዳርጋሉ። ይህንን ለማረጋገጥ ባህር ተሻግረን ማሳያ መፈለግ ሳይጠበቅብን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ ነኝ ባይ የነበረውን ትህነግን ማየት ይበቃል። ትህነግ ግማሽ ምዕት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ በሕዝብ ትከሻ ላይ ተንጠላጥሎ፤ በሕዝብ ገላ ላይ እንደመዥገር ተጣብቆ የኢትዮጵያ ሾተላይ ሆኖ ኖሮ ሞቷል።ነጻነት ሳያውቅ ህዝብን ነጻ አወጣለሁ ብሎ ደደቢት ላይ የተፈለፈለው እፉኝት በሞቱ ለኢትዮጵያ ነጻነት ታውጇል። “ቀን ያስጎነበሰውን ቀን ቀና ያረገዋል” እንዲሉ የካቲት 11 ቀን … [Read more...] about ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር