መውጫው እንደመግቢያው ቀላል አልሆነም። በትግሬ ልሂቃን እብደት፣ ማኅበራዊ መሠረታቸው ላይ የእሳት ቀለበት ሰርተዋል። በእያንዳንዱ የትግሬ ጎጆ የመከራ ዜና፣ የመርዶ መልዕክት ገብቷል። በጦርነቱ እና ከጦርነቱ ጋር ተያያዥ በሆኑ ምክንያቶች አራት መቶ ስድሳ ሺህ ትግሬዎች ረግፈዋል። ይህን እኔ ሳልሆን ያልኩት የሳልሳዊ ወያኔ (ሳወት) መሪ ተስፋ ኪሮስ ሳህለ ነው። ያለምንም ጥርጥር ጦርነቱ በሕዝባቸው ላይ የትውልድ ክፍተት ፈጥሯል። ምናልባትም አንድ ወንድ አምስት ሴቶችን እንዲያገባ በልዩ ሁኔታ የቤተሰብ ሕጉ ካልተሻሻለላቸው በስተቀር የትውልድ ክፍተቱን በቀላሉ አይሞሉትም። ወያኔ ራሱ በለኮሰው እሳት “እወክለዋለሁ” የሚለውን ሕዝብ የእሳት ቀለበት ውስጥ አስገብቶታል። ከዚህ ጦርነት የሚተርፍ ቢኖር እንኳ በርካታ የትግራይ ከተሞችና መንደሮች የአዛውንት እና የሕጻናት ስብስብ … [Read more...] about ቀጣይዋ ትግራይ = “ትግ-ሶቶ”