
መውጫው እንደመግቢያው ቀላል አልሆነም። በትግሬ ልሂቃን እብደት፣ ማኅበራዊ መሠረታቸው ላይ የእሳት ቀለበት ሰርተዋል። በእያንዳንዱ የትግሬ ጎጆ የመከራ ዜና፣ የመርዶ መልዕክት ገብቷል። በጦርነቱ እና ከጦርነቱ ጋር ተያያዥ በሆኑ ምክንያቶች አራት መቶ ስድሳ ሺህ ትግሬዎች ረግፈዋል። ይህን እኔ ሳልሆን ያልኩት የሳልሳዊ ወያኔ (ሳወት) መሪ ተስፋ ኪሮስ ሳህለ ነው። ያለምንም ጥርጥር ጦርነቱ በሕዝባቸው ላይ የትውልድ ክፍተት ፈጥሯል። ምናልባትም አንድ ወንድ አምስት ሴቶችን እንዲያገባ በልዩ ሁኔታ የቤተሰብ ሕጉ ካልተሻሻለላቸው በስተቀር የትውልድ ክፍተቱን በቀላሉ አይሞሉትም።
ወያኔ ራሱ በለኮሰው እሳት “እወክለዋለሁ” የሚለውን ሕዝብ የእሳት ቀለበት ውስጥ አስገብቶታል። ከዚህ ጦርነት የሚተርፍ ቢኖር እንኳ በርካታ የትግራይ ከተሞችና መንደሮች የአዛውንት እና የሕጻናት ስብስብ ከመሆን ውጭ አማካኝ ዕድሜ ላይ የሚገኝና አልሚ ጉልበት ያለው ወጣት ቁጥሩ አነስተኛ መሆኑ አይቀርም። ወጣቱ በጦርነት እየረገፈ ነው፤ ከጦርነት ቢያመልጥ እንኳ በስደት ከቀየው መራቁ ተገማች ነው።
ወያኔ በቀደመ የአገዛዝ፣ የዘረፋ እና የጨፍጫፊነት ባሕሪውና የዚህ ማኅበራዊ መሠረት በመሆኑ የተነሳ ትግሬ በመላ የኢትዮጵያ ሕዝብ ተይዞበት ከነበረው ቂም በከፋ ሁኔታ የጥቅምት 24ቱ ክህደቱና አሁናዊ የሽብር፣ የጦር ወረራ፣ ጭፍጨፋ፣ ውድመትና የዘረፋ ተግባራቱ የተነሳ የኢትዮጵያን ሕዝብ አስቆጥቷል። አንቅሮ ያልተፋው ብሔር የለም። ሀገር ነው የተባበረ ክንዱን ያስወነጨፈው፤ በሰማይና በምድር በሚዘንበው እሳት ጠላት እየረገፈ ነው። የአማራ እና የአፋር ተራሮችም በጥንብ አንሳ ተሞልተዋል (በጎልጉል የተጨመረ፤ ሰሞኑን ጠቅላዩ በአንድ ግምባር ሲናገሩ ይሰማ የነበረውን የቁራ ድምፅ ማስታወሱ በቂ ነው)።
በዚህ ጦርነት ኢትዮጵያ ማሸነፏ እርግጥ ነበር፤ እየሆነ ያለውም ይኼው ነው። የነገው የትግራይ ሁኔታ ግን የተለየ ገጽታ መላበሱ አይቀርም። ዙሪያውን በእሳት ካብ የታጠረ ማኅበረሰብ በምንም አይነት ተዓምር ጤናማ የገበያ ትሥሥር፣ የመሠረተ-ልማት ዕድል እና የማኅበራዊ አገልግሎት አያገኝም። ተከዜን መሻገር ቀርቶ አሳ ማጥመድ መቻልም ዕድለኝነት ነው።
ጦርነቱን ተከትሎ በደረሰበት መከራ እና ማኅበረሰባዊ ውድቀት (societal collapse) የተነሳ በቀጣይ የቱንም ያሕል ቢደክም የተረጋጋ ማኀበረሰብ መፍጠር አይችልም። ወንዱ የሚበረግግ ህሊና (paranoid) ሴቷ ደግሞ በምግብ መቀንጨር ማህጸኗ የተጎዳ መሆኗ አይቀርም። በዚህ መሀል የሚወለዱ ልጆች ከሌላው ኢትዮጵያዊ ህፃናት ጋር የማይወዳደሩ ጤናቸው የታወከ ይሆናል።
ከዚህ መዓት የሚያመልጥ ቢኖር እንኳ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር የቀደመው ማኅበራዊ ወረቱ ሊቀጥል አይችልም። በተለይም ከጎረቤቶቹ አማራ እና አፋር ጋር ደም የተቃባ በመሆኑ፣ አልፎም ከኤርትራ ጋር ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ቅራኔ ውስጥ የገባ መሆኑ በደሴት ውስጥ የሚኖር ተነጣይ የዱር እንስሳት ዕጣ ያጋጥመዋል። የደቀቀ ኢኮኖሚ ታቅፎ በድንጋያማ መሬት ትርፍ ማምረት የተሳነው ተመጽዋች ይሆናል። በዚያ ክልል (በትግ-ሴቶ) ከ49 ኪሎ በላይ የሆነ ሰው ማየት ብርቅ ይሆናል።
በሁሉም መመዘኛዎች ከታየ ትግራይ በቀጣይ ጊዜ የጨነገፈ ትውልድ ይዛ መንገታገቷ ከሀቅ የራቀ አይደለም። በትግራይ ልሂቃን እብደት የተነሳ፣ በቀጣይ እያንዳንዱን ዋይታና የመከራ ዘመን በነፍስ-ወከፍ የሚኖረው የትግሬ ሕዝብ “የጎረቤት ያለህ” በሚል ሲንከራተት መኖሩ አይቀሬ ነው። ወያኔ በክህደት ባህሪው የተነሳ ትላንት የድርጅት አጋርነት ውድቀት ታሪኩ “የአጋር ያለህ” አሰኘው፤ ዛሬ የሁኔታዎች ድምር ውጤት የገዛ ሕዝቡን “የጎረቤት ያለህ” እያሰኘው ነው።
ከትላንት የቀጠለው የዛሬ ሰይጣናዊ ድርጊታቸው በውል ሕዝቡን የተጠላ ነገድ እንዲሆን አድርጎታል። ይህ ጦርነት ደግሞ ራቁታቸውን አስቀርቷቸዋል። ትግሬ እንደሕዝብ በኢትዮጵያ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ቦታዎችን ማጣቱ ርግጥ ሁኗል። ከእንግዲህ እንኳንስ ሀገር፣ ዕድር እና እቁብ የመምራት ዕድል አያገኙም። የዳር ሀገር መናኛ ሕዝብ የመሆን ጉዞውንም ከወዲሁ ጀምሯል። ለዚህ ተጠያቂው የትግሬ ልሂቅ እንጅ ኢትዮጵያዊያን አይደሉም።
የስንብት ሃረካት…
አሁን እየሆነ ያለው አንድ የነሱ ሰው ከወራት በፊት “ሁሉም ትግሬ ጦርነት ውስጥ ነው” እንዳለው ነው። ወይ ሞኞ! ለዚህ አፀፋው “ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሀገሩን ለመታደግ ጦርነት ውስጥ ነው”። በየትም ቦታ በምንም ሁኔታ ያሉ የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጆች የእናት ሀገራቸው ዘብ ሆነው ተሰልፈዋል። ከትግሬ ወራሪ ጋር የሚጠፋፋ እንጅ የሚስተሃቀር ፍላጎት የላቸውም። በነገዋ ኢትዮጵያ አንድ የትግሬ ለማኝ ከመቀሌ ተነስቶ ለልመና በመላ ኢትዮጵያዊያን በር ቢዞር አኮፋዳውን ስለመሙላቱ እጅጉን እጠራጠራለሁ!!
የሆነው ሆኖ ጠላት በጦርነቱ እንደማያሸንፍ ያውቀዋል። ፍላጎቱ (የኮሪደሩን ቅዥት እርሳውና) በቻለው መጠን አማራንና አፋርን ማጥፋት፣ ከሆነለት በኢትዮጵያ የውጭ ጠላቶች ተንጠልጥሎ ሀገር ማፍረስ ነው። “አቻ መውጣት” ነው። ጠላት ትግራይ ተስፋ ቢስ ነች የሚል ግምገማ ከያዘ ቆይቷል፣ አሁን የሞት ሽረቱን “አቻ ለመሆን” ነው ገቢረ-ጉንዳን የሆነው። ግና የዛለ ክንድ ያለው በመሆኑ ዕድሜው የጉንዳን እግር ያህል እንኳ አይረዝምም። በአጠረ ጊዜ ቃታ የመሳብ አቅም ጨርሶ አይኖረውም። ያኔ ከዛሬ በከፋ ለነገ ማኅበራዊ ውርደት ቋሚ የሕይወት ምዕራፉ ይሆናል። ሂሳቡም እጥፍ እንደሚወራረድ አትርሳው!!
የትግሬ ልሂቅ ሆይ! የመረጥከውን መኖር ተፈጥሯዊ መብትህ ነው። ተፈጥሮ ግን ሕግ አላት፤ የእጅህን ታገኛለህ! በመከራም ሆነ በዋይታ ውስጥ ስትኖር ያንተ ብቻ ሳይሆን የነገ የትውልድ ዕጣ ፈንታህን በጨፈገገ የህይወት ምዕራፍ ውስጥ መመልከትህ አይቀሬ ነው። ይህን ለማረም ደግሞ ጊዜው ረፍዷል!! ምናልባትም ማረም የሚችሉት ሲበደሉ የኖሩት ቋንቋና ኃይማኖት የማይለያያቸው መላ ኢትዮጵያዊያን ናቸው። ኢትዮጵያዊያን ደግሞ የህልውና ዘመቻ ላይ ናቸው። ከሆነልህ ባለህበት እጅ ስጥ! እምቢ ካልክ የሲዖል ትኬት ይቆረጥልሃል።
ዘላለማዊ ክብርና ሞገስ ኢትዮጵያን ብለው የማይተካ ሕይወታቸውን ለገበሩ የቁርጥ ቀን ልጆች!
ሙሉአለም ገ/መድህን (ርዕስ፤ ሲያንስህ ነው!!)
ይህንን መልእክት የማቀርበው፤ በጥያቄ ሥልት ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት፡፡
እንደ አጋጣሚ፤ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት አማካኝነት፤ በለሶቶ፤ የፖስታ፤ ቴሌኮሙኒኬሽንና የሲቪል አቭዬሽን ዋና ዲሬክተር፤ ከዚያ በኋላ ደግሞ፤ የለሶቶ የሥራ ሚኒስቴር ዋና ተጠሪ (Permanent Secretary) በመሆን አገልግዬ ነበር፡፡ ዝርዝሩን ለማወቅ፤ “My Journey with the United Nations and Quest for the Horn of Africa’s Unity and Justice for Ethiopia” የተሰኘውን መጽሐፌን መመልከት ይቻላል፡፡
ለሶቶ በስፋት ትንሽ ብትሆንም፤ ራሷን ከእንግሊዞች ቅኝ ግዛት ማዳን የቻለች፤ ለሰላምና ለልማት በመታገል ብርቱ የሆነች ሐገር ናት፡፡ ሌላው፤ ለሶቶን፤ በተለይ የሚያስመሰግናት፤ ከደቡብ አፍሪካ በየዓመቱ $50 ሚሊዮን እያስከፈለች፤ ባላት ከፍተኛ የውሀ ህብት መብቷ እየተጠቀመች ለመሆን መቻሏ ነው፡፡
ታዲያ፤ “ትግ_ሶቶ” ማለት ምን ለመጠቆም ይሆን? በተለይ “ሞኝ ቤት ፊት ሞፈር ይቆረጣል” ከሚያሰኝ ሰፈር!
ኪዳኔ ዓለማየሁ፡፡
Kidane Alemayehu
በጽሁፉ ላይ በግልጽ ተቀምጧል፤ ይህቺን አንቀጽ ካላነበቧት ድጋሚ ተመልከቷት
“ከዚህ መዓት የሚያመልጥ ቢኖር እንኳ ከሌላው ኢትዮጵያዊ ጋር የቀደመው ማኅበራዊ ወረቱ ሊቀጥል አይችልም። በተለይም ከጎረቤቶቹ አማራ እና አፋር ጋር ደም የተቃባ በመሆኑ፣ አልፎም ከኤርትራ ጋር ከትውልድ ትውልድ የሚሸጋገር ቅራኔ ውስጥ የገባ መሆኑ በደሴት ውስጥ የሚኖር ተነጣይ የዱር እንስሳት ዕጣ ያጋጥመዋል። የደቀቀ ኢኮኖሚ ታቅፎ በድንጋያማ መሬት ትርፍ ማምረት የተሳነው ተመጽዋች ይሆናል። በዚያ ክልል (በትግ-ሴቶ) ከ49 ኪሎ በላይ የሆነ ሰው ማየት ብርቅ ይሆናል።”
አርታኢ
መቼም በሕይወቴ ሙሉ እንደ ዘንድሮ አዝኜ አላውቅም በተለይ የተማረኩትን ትናንሽ ልጆች አይ ያስለቅሳል ግን ሕወአት በእውነት ድርጅት ነው? ይሄን ሁሉ አፀያፊ የሆነ ነገር ለምን በምስኪን ወንድሞቹና እህቶቹ ላይ ማድረግ ፈለገውን? እንደው የነጮቹ ትዕዛዝስ በገንዘብ አደረገው ቢባልም የሕወአት ሰዎችን ዓለምን የሚያናጋ ገንዘብ አላቸው አይደለም እንዴ? ወይስ እንደሚባለው የሠይጣን ናቸው በዚህም አለ በዚያ የትግራይ ሕዝብ መከራ አላበቃም አለ ከዘመን ዘመን የአሁኑ ግን በክፍለ ዘመኑ መጨረሻ ላይም የሚያበቃም አይመስልም።
ውድ አርታኢ (ቦርኬና)፤
ሰላም፡፡ የጠቀሱትን “አንቀጽ” ተመለከትኩት፡፡ ለሶቶ የውሀ ብቻ ሳይሆን የዓልማዝም የታታሪ ሕዝብ እሴት ያላት ሐገር በመሆኗ፤ በጽሑፉ በቀረበው ዓይነት አስተሳሰብ ልትዘቅጥ አይገባትም፡፡
Kidane Alemayehu
የጽሁፉ ዐውድ ሌሶቶን ከማዝቀጥ አኳያ ሳይሆን ትግራይን በካርታ ደረጃ በሌሶቶ ቅርጽ ከማስቀመጥ ነው። ይህ ደግሞ ጽሁፉ በግልጽ የተቀመጠ ሃቅ ነው።
ተጨማሪ ጥያቄ ወይም ተቃውሞ ካለዎት በሞጋች ጽሁፍ (rebuttal or rejoinder) መልኩ ቢያቀርቡ ለአንባቢ እንዲደርስ እናደርጋለን። ወይም ጸሐፊውን ለማግኘት ከፈለጉ ስሙ ላይ ባለው ሊንክ ተጠቅመው በፌስቡክ ሃሳብዎን ሊገልጹለት ይችላሉ።
በዚህ አጋጣሚ “ቦርኬና” በማለት የጻፉትን ቃል ትርጉም እንዲገልጹልን በአክብሮት እንጠይቃለን።
አርታኢ
ብሩካን፤
“ቦርኬና” ያልኩት በስሕተት ነው፡፡ ይቅርታ፡፡
እኛም አዲስ ቃል ስለሆነብን ለመማር ብለን ነው የጠየቅነው፤
ክብረት ይስጥልን