1. መግቢያ፣ አዲስ አበባ ብዙ ዋጋ ተከፍሎባታል ሲባል ነገር ለማጣፈጥ የተነገረ ወሬ ሳይሆን በተጨባጭ የሆነና የተደረገ መሆኑን እኔ በህይወቴ ያየሁትን እንዲት ገተመኝ እንደ ምሳሌ ልጥቀስ። ስሜ ደረጀ ተፈራ ይባላል ተወልጄ ያደኩት አዲስ አበባ ፊትበር ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው። ሰፈራችን ለታላቁ ቤተመንግስት (ምኒልክ ቤ/መ) ቅርብ በመሆኑ የደርግ ቅልብ ወታደሮችም ሆኑ የወያኔ አጋዚ ጦር የአካባቢውን ጸጥታ ለማስከበር ብቻ ሳይሆን ኮረዶችንም ለማሽኮርመም እኛ ሰፈር አይጠፉም ነበር። በደርግም ሆነ በወያኔ አገዛዝ ዘመን አንድ ነገር ኮሽ ባለ ቁጥር ከቤተ መንግስት፣ የደርግ ቅልቦችና የወያኔ አጋዚ ጦር፣ ከውጭ ጉዳይ ሚ/ር አና ከፓሊስ ገራዥ ደግሞ ፌዴራል ፖሊሶች ክላሻቸውን እያንቀጫቀጩ መጀመሪያ የሚመጡት እኛ ሰፈር ነበር። በዚህ ላይ ኮ/ል መንግሥቱ … [Read more...] about አዲስ አበባ ብዙ ዋጋ የተከፈለባት ከተማ
Opinions
የኔ ሃሳብ
የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ወቅታዊ መግለጫ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ካቢኔ መስከረም 15/2013 ዓ.ም ባካሄደው ሁለተኛ መደበኛ ስብሰባው፣ በከተማዋ የተጀመረውን ትምህርት ተሞክሮ እና አገልግሎቶች በአካታች ልማት (inclusive development) መርህ መሰረት አዲስ አበባ ዙሪያ ልዩ ዞን ወይም የኦሮሞ ብልጽግና “የፊንፊኔ ልዩ ዞን” በሚል መጠሪያ ባካተታቸው አካባቢዎች በሚገኙ 346 ትምህርት ቤቶች ውስጥ ለሚማሩ አንድ መቶ ሃምሳ ሁለት ሺህ(152,000) ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ፣ የተማሪ ደንብ ልብስ፣ጫማ እና የትምህርት ቤት ምገባ አገልግሎት ለማቅረብ የሚያስችል 669,210,780 (ስድስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ ሚልዮን ሁለት መቶ አስር ሽህ ሰባት መቶ ሰማንያ ብር) በጀት በመመደብ ለእርዳታ አገልግሎቱ እንዲውል በልዩ ሁኔታ ውሳኔ አሳልፏል። ፓርቲያችን ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በአዲስ አበባ ከተማ ዙሪያ … [Read more...] about የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ወቅታዊ መግለጫ
“In Honor and Remembrance of the Life of Professor Mesfin Woldemariam” Obang
Good Morning to everyone here. First of all, I would like to give my deepest sympathy to the family of Professor Mesfin Woldemariam and the great numbers of Ethiopians who consider him a great friend of the Ethiopian people for many generations. I also thank those who have given me the opportunity to speak today about one of greatest men I have been privileged to meet and know. This giant of a man has played an important and strategic role in my life and that of many others. Most people … [Read more...] about “In Honor and Remembrance of the Life of Professor Mesfin Woldemariam” Obang
ኤርሚያስ ለገሰ፤ “ለምኖ ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል”
የኢህአዴግ ካድሬና እያለቀሰ ስለኢህአዴግ ይሰብክ የነበረው የበረከት ስምዖን የጡት ልጅ ኤርሚያስ ለገሠን በተመለከተ ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ “አልቃሻው ሚኒስትር ደኤታ” እና “የኤርምያስ ለገሰ ቪዲዮዎች ፉከራ ሲጋለጥ” በሚል ሁለት የአስተያየት ጽሁፎችን አቅርቦ ነበር። በወቅቱ እነዚህን ጽሁፎች በማተማችን ከፍተኛ ተቃውሞ ደርሶብናል። የተሰጡትንም አስተያየቶች አሁንም በጽሁፎቹ ግርጌ ማግኘት ይቻላል። ኤርምያስ ለረጅም ጊዜ እንደ ትልቅ ነገር አድርጎ ሲያወራው የነበረው ቪዲዮ የኔታ ቲዩብ ይፋ አድርጎታል። አበበ ገላው ደብቆ ያስቀመጠውና ስለ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የሚናገር ትልቅ ምሥጢር የያዘ የድምጽ ቅጂ አለ በማለት ኤርምያስ ቅጂው አንዲወጣ አበበን ባደባባይ ይገዳደር ነበር። አሁን በወጣውና ኤርምያስ ምሥጢር ሲለው በነበረው ድምጽ ቅጂ ውስጥ ግለሰቡ … [Read more...] about ኤርሚያስ ለገሰ፤ “ለምኖ ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል”
ብር የመለወጡ ቀጥተኛ ጥቅም
ብዙ ሰዎች በተደጋገሚ ብሩ በመለወጡ በቀጥታ ኢኮኖሚው ላይ የሚመጣውን ጥቅም ንገረን ብለው ጠይቀውኛል! ብር በመለወጡ የሚገኙት የአጭር ግዜ እና የረጅም ግዜ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች የሚከተሉት ናቸው! የአጭር ግዜ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታዎች፡- በሀገራችን ከ113ቢሊዮን ብር በላይ ጥሬ ገንዘብ ከፋይናንስ ገበያው ቁጥጥር ውጪ አለ! ስለዚህ የገንዘብ ለውጡ ይህንን ገንዘብ ወደ ብሄራዊ ባንክ የመለወጥ እድል ይፈጥራል! ለምሳሌ፡- ምንጩ ያልታወቀ በመሆኑ ወደ ባንክ ሳይመጣ ከሚበላሸው፤ ከሀገር ውጪ በጎረቤት ሀገር በመሸሹ ከማይመለሰው፤ የመቀየሪያ ወቅቱ ከሚያልፍበት፤ በጎርፍ፤ በቃጠሎ፤ ወዘተ ከወደመው ውጪ 100 ቢሊዮን ብር እንኳን ወደ ህጋዊ የባንክ ስርዓት ቢመጣ ከፍተኛ ገንዘብ ከገበያ የመሰብሰብ እድል ስለሚፈጠር የዋጋ ንረት በሚታይ መልኩ የመቀነስ አቅም ይኖረዋል! ምንጩ … [Read more...] about ብር የመለወጡ ቀጥተኛ ጥቅም
ይቅርታና ምህረት አድራጊው ይወገዳል! የተደረገለትም ይሞታል!
መሃል ሰፋሪ አሊያም ገለልተኛ ይመስል የነበረው የኦሮሞ አክቲቪስቶች በሙሉ የጃዋር ግልገል መሆናቸው የምታውቀው፤ ልክ እንደ አይን-አፋር ሴት እየተቅለሰለሱ፣ እንደ ሽምግሌ ምሳሌ እያበዙ ከሄዱ በኋላ በማጠቃለያው ላይ “ጃዋር መሃመድ በይቅርታ ከእስር ቢፈታ ለሀገርና ህዝብ ይጠቅማል!” ሲሉ ነው። በእርግጥ በእስር ላይ ያለ ሰው እንዲፈታ ማሰብ፣ አማላጅ መላክ ወይም Lobby ማድረግ በተለይ እንደ ኢትዮጵያ ባለ ሀገር ውስጥ የተለመደ ነው። በዚህ ረገድ በሰኔ15ቱ ግድያ ተጠርጥረው የታሰሩ ሰዎች መፈታታቸው በተደጋጋሚ እንደ ማሳያ ተጠቅሷል። ነገር ግን በሰኔ 15ቱ ግድያ የተሳተፉ አካላት በስልጣን ሽኩቻና አለመግባባት ምክንያት የተፈጠረ ነው። በዚህ ምክንያት የተጎዱ ሰዎች መኖራቸው እርግጥ ነው። ነገር ግን በአማራ ክልል የሚገኙ አማራዎችን ወይም ሙስሊሞችን ለማጥፋት ታቅዶ የተፈፀመ … [Read more...] about ይቅርታና ምህረት አድራጊው ይወገዳል! የተደረገለትም ይሞታል!
ከሚገድለኝ ሰይጣን ይልቅ የሚሰድበኝ ባለስልጣን ይሻለኛል! ሽመልስ የተናገረው በወቅቱ ትክክል ነው‼️
አቶ ሽመልስ አብዲሳ “በትላንትናው እለት የተናገረው ነው” ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ከሰባት ወር በፊት የብልፅግና ፓርቲ ገና በምስረታ ሂደት ላይ እያለ የተናገረው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። በወቅቱ የድርጅቱን አባላትና አመራሮች በኦቦ ለማ መገርሳ፣ ወ/ሮ ጠይባ እና በዶ/ር ሚልኬሳ ከሚመራው ብሔርተኛ ቡድን ለመነጠልና በድርጅቱ ውስጥ ተፈጥሮ በነበረው የኃይል ሹኩቻ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት በሚደረግ ጥረት የተናገረው እንደሆነ ተረጋግጧል። አቶ ሽመልስ የተናገረበት ግዜና ቦታ ምን ያህል የተለያየ ቢሆንም አዲስ አበባን አስመልክቶ የተናገረው ነገር መቼም፥ እንዴትም ትክክል አይሆንም። ይሁን እንጂ በወቅቱ ድርጅቱ ውስጥ የጃዋር መሃመድ ጉዳይ አስፈፃሚ የነበሩት ከላይ የተጠቀሱት የኦዴፓ አመራሮች ከኮዬ_ፈቼ ኮኖደሚኒዬም ጋር በተያያዘ ሲያራምዱት የነበረው አቋምና ጉዳዩ በብሔርተኞቹ ዘንድ … [Read more...] about ከሚገድለኝ ሰይጣን ይልቅ የሚሰድበኝ ባለስልጣን ይሻለኛል! ሽመልስ የተናገረው በወቅቱ ትክክል ነው‼️
ሺቅዳ ሺመልስ፤ “ኦሮሞ ኦሮሞን አይገድልም” የሚለው አባባል “ዲና ነፍጠኛን” ግደል ማለት ነው!
በሃገራችን በሁለት የከተማ አስተዳደሮች እና በአስር ክልሎች ተከፋፍላ ትተዳደራለች። ከአስሩ ክልሎች ውስጥ ከኦሮሚያ ክልል በቀር ዘጠኙ ክልሎች ከሞላ ጎደል አንፃራዊ ሰላም ውስጥ የሚገኙ ናቸው። ሆኖም እነዚህ ዘጠኝ ክልሎችም አለፍ አለፍ ብሎ የፀጥታ መደፍረስ፣ ዘውግ ተኮር ግጭት፣ የባለስልጣናትን ሞት የጨመረ ፖለቲካዊ ምስቅልቅል ውስጥ ገብተው ያውቃሉ፤ ወደፊትም እንዲህ ያለ ነገር ሊገጥማቸው ይችላል። ክልሎቹ የገጠማቸውን ፈተና ጠቅልሎ ማጥፋት አይቻልምና በአጭር ጊዜ ውስጥ ችግሩ እንዲቃለል ግን አደርገዋል። ይህ የሆነው በዋናነት በክልሎቹ አመራሮች ኢትዮጵያን የማዳን ቁርጠኝነት ነው። እነዚህ ክልሎች ኢትዮጵያን ለማዳን የሚሰሩት የዘውጋቸው ሰው “ስልጣን በቃኝ” እስከሚል ዙፋን ላይ ተቀምጦ ስለኖረ ወይም የህዝባቸው ጥያቄም ሙሉ በሙሉ ስለተመለሰ አለያም በክልላቸው ሁሉ ሙሉ ሁሉ ዝግጁ … [Read more...] about ሺቅዳ ሺመልስ፤ “ኦሮሞ ኦሮሞን አይገድልም” የሚለው አባባል “ዲና ነፍጠኛን” ግደል ማለት ነው!
አብይን የምደግፈው ለራሴ ስል ነው!
አብይን የምደግፈው አዎ ለራሴ ስል ነው! ከፀፀት ለመዳን፤ ከህሊና ወቀሳ ለመትረፍ ስል! ዶክተር አምባቸው መኮንን ከተገደለ በኋላ የተሰማኝን ስሜት እኔ ነኝ የማውቀው። የክልሉ ፕሬዝዳንት ሆኖ በሀላፊነት በቆየባቸው ሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ በውጥረት ተከቦ በርካታ በጎ ስራዎችን አከናውኗል። ጥሩ ስራ ሲሰራ አንድም በጎ ቃል ትንፍሽ አላልኩም ነበር።ኦሮሚያ ክልል ሄዶ ስለልዩ ጥቅም አወራ ሲባል ግን እሱን ለመተቸት ማንም አልቀደመኝም። አሁን የአምባቸውን ምስል ፌስቡክ ላይ ባየሁ ቁጥር ፀፀቱ ይገርፈኛል። እሱን ተችቼ የፃፍኩትን ፅሁፍ ከፌስቡክ ገፄ አጥፍቸዋለሁ። የጥፋተኝነት ስሜቱ ግን ከህሊናየ ሊጠፋ አልቻለም። ይህ ፀፀቴ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እንዲደገም አልፈልግም። ዶክተር አብይ ወደስልጣን ከመጡ በኋላ ተዘርዝረው የማያልቁ በርካታ ለውጦችን ያመጡ ቢሆንም ከምስጋና ይልቅ … [Read more...] about አብይን የምደግፈው ለራሴ ስል ነው!
የተሸጠውን ግድብ ዐብይ ገዛው‼
ታታሪው ሰው ነገሮች ሁሉ ከተጠናቀቁ በኋላ መግለጫ ሰጠ። መግለጫ እንዲህ በረከሰበት ዘመን እሱ ገላለጠው!! “የግድቡ የመጀመሪያ ምዕራፍ ሙሌት ተጠናቅቋል። እንኳን ደስ ያለን” አለ። እኔ ግን ከፋኝ!! ቅር አለኝ! ደነገጥኩ!! “ግድቡን የሸጠው ጠቅላይ ሚኒስትር” የሚለው ትንታኔ ተናነቀኝ። ተጽፎ፣ ተነብቦ፣ ተቀርጾ፣ ተቀናብሮ፣ ስምና ባለቤት ኖሮት ለአለም የቀረበው ትንተና ትዝ አለኝ። ዕውቀት ቀፈፈሽ። ስዩም መስፍን ያለቀሰለት ግድብ ትዝ አለኝ። ጌታቸው ረዳ ሲሸጥ ያየው ግድብ ትዝ አለኝ። አሜሪካና አለም ባንክ፤ ግብጽና ጂዳ ተጠቃቅሰው የገዙት ግድብ ትዝ አለኝ። ተደራዳሪዎቹ እየቆራረሱ የቸበቸቡት ግድብ ትዝ አለኝ። ያለ ልምድ፣ ያለ እውቀት እና ያለሀገር ፍቅር የተመራው የድርድር ቡድን አይኔ ላይ ድቅን አለብኝ!! ይሄ ሁሉ የክስ ናዳ፤ ይሄ ሁሉ የትንተና ካብ ስድስት … [Read more...] about የተሸጠውን ግድብ ዐብይ ገዛው‼