እንደምን ሰነበታችሁ! እንኳን በጤና ተገናኘን! “በሚኖሩባት ሰዎች ክፋት የተነሳ ፍሬያማዋን ምድር ጨው አደረጋት” የሚል ቃል በቅዱሱ መጽሀፍ ውስጥ ሰፍሯል።ሕዝብ መቼም ቢሆን ክፉ ሆኖ አያውቅም፤ አይሆንምም። ነገር ግን ከሕዝብ የወጡ ጥቂቶች በዕኩይ ዓላማና ምግባራቸው ምድሪቱን ለጥፋት፣ ሕዝቡንም ለስቃይ ይዳርጋሉ። ይህንን ለማረጋገጥ ባህር ተሻግረን ማሳያ መፈለግ ሳይጠበቅብን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጭ ነኝ ባይ የነበረውን ትህነግን ማየት ይበቃል። ትህነግ ግማሽ ምዕት ዓመት ለሚጠጋ ጊዜ በሕዝብ ትከሻ ላይ ተንጠላጥሎ፤ በሕዝብ ገላ ላይ እንደመዥገር ተጣብቆ የኢትዮጵያ ሾተላይ ሆኖ ኖሮ ሞቷል።ነጻነት ሳያውቅ ህዝብን ነጻ አወጣለሁ ብሎ ደደቢት ላይ የተፈለፈለው እፉኝት በሞቱ ለኢትዮጵያ ነጻነት ታውጇል። “ቀን ያስጎነበሰውን ቀን ቀና ያረገዋል” እንዲሉ የካቲት 11 ቀን … [Read more...] about ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር
my cadra
“የማይካድራ ጭፍጨፋ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ሰብዓዊ፣ ስነልቦናዊ ቀውስና ጥልቅ ሀዘን ያስከተለ ነው” – ዶ/ር ዳንኤል
በህወሓት ጁንታ ቡድን ላይ ህግ የማስከበር ዘመቻ መጀመርን ተከትሎ በማይካድራ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመው እልቂት በነዋሪዎች እና በተመልካች ላይ አስከፊ የስነ ልቦና ቀወስ ሊያስከትል እንደሚችል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር (ኢሰመኮ) ዶ/ር ዳንኤል በቀለ አስታወቀዋል። ዶክተር ዳንኤል የማይካድራ ጭፍጨፋ አስመልክቶ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፣ በማይካድራ የተፈጸሙ ግፍ በቁጥር ከሚገለጸው ሪፖርት ባሻገር በነዋሪዎች ላይ ሰብዓዊ እና ስነልቦናዊ ቀውስ እንዲሁም ጥልቅ ሀዘን አስከትሏል። በማይካድራ አማራ እና በወልቃይት ተወላጆች ላይ ያነጣጠረውን ጥቃት ተከትሎ ቤተሰቦች መበታተናቸውንና ሕፃናት ለስነልቦና ቀውስ መዳረጋቸውን የተናገሩት ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል፤ የጭፍጨፋው ሰለባ ቤተሰቦች ህይወታቸውን እንደቀድሞ ለማስቀጠል አዳጋች እንደሚሆንባቸው … [Read more...] about “የማይካድራ ጭፍጨፋ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ሰብዓዊ፣ ስነልቦናዊ ቀውስና ጥልቅ ሀዘን ያስከተለ ነው” – ዶ/ር ዳንኤል
በማይካድራ 18 ሰው በጉድጓድ ተጥሎ፤ 57 ደግሞ በጎርፍ ማፋሰሻ ቦይ ተገድለው ተገኙ
ጥቅምት 30/2013 ዓ.ም በንጹኃን የአማራ ብሔር ተወላጆች ላይ ዘርን መሠረት ያደረገ ጥቃት በማይካድራ ከተማ መፈፀሙ ይታወቃል። ይህን አስነዋሪ ተግባር የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በቦታው በመገኘት ባደረገው ጥናት እና ይፋ ባደረገው መረጃ የሟቾች ቁጥር በትንሹ 600 እንደሆነ ገልጾ ነበር። ግድያውም ዘርን መሠረት ያደረገና በተለይም የአማራ ተወላጆች ላይ ያነጣጠረ ጅምላ ጭፍጨፋ መሆኑን ገልጿል። ይሁን እንጂ የሟቾች ቁጥር በትንሹ 600 ነው ተብሎ የተገለጸው በማይካድራ ከተማ በየቤቱ ህይወታቸው አልፎ የተገኙ እና በቤተክርስቲያን ውስጥ የተቀበሩትን ብቻ መሠረት ያደረገ ነው። የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ጥናት አድርጎ ከተመለሠ በኃላ ከማይካድራ ከተማ ወጣ ባሉ የገጠር አካባቢዎች በርካታ የጅምላ መቃብሮች መገኘታቸውን የአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ጋዜጠኞች በቦታው … [Read more...] about በማይካድራ 18 ሰው በጉድጓድ ተጥሎ፤ 57 ደግሞ በጎርፍ ማፋሰሻ ቦይ ተገድለው ተገኙ