• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“የማይካድራ ጭፍጨፋ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ሰብዓዊ፣ ስነልቦናዊ ቀውስና ጥልቅ ሀዘን ያስከተለ ነው” – ዶ/ር ዳንኤል

December 2, 2020 02:42 am by Editor 1 Comment

በህወሓት ጁንታ ቡድን ላይ ህግ የማስከበር ዘመቻ መጀመርን ተከትሎ በማይካድራ በሰላማዊ ዜጎች ላይ የተፈጸመው እልቂት በነዋሪዎች እና በተመልካች ላይ አስከፊ የስነ ልቦና ቀወስ ሊያስከትል እንደሚችል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር (ኢሰመኮ) ዶ/ር ዳንኤል በቀለ አስታወቀዋል።

ዶክተር ዳንኤል የማይካድራ ጭፍጨፋ አስመልክቶ በተለይ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፣ በማይካድራ የተፈጸሙ ግፍ በቁጥር ከሚገለጸው ሪፖርት ባሻገር በነዋሪዎች ላይ ሰብዓዊ እና ስነልቦናዊ ቀውስ እንዲሁም ጥልቅ ሀዘን አስከትሏል።

በማይካድራ አማራ እና በወልቃይት ተወላጆች ላይ ያነጣጠረውን ጥቃት ተከትሎ ቤተሰቦች መበታተናቸውንና ሕፃናት ለስነልቦና ቀውስ መዳረጋቸውን የተናገሩት ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል፤ የጭፍጨፋው ሰለባ ቤተሰቦች ህይወታቸውን እንደቀድሞ ለማስቀጠል አዳጋች እንደሚሆንባቸው ተናግረዋል። በመሆኑም ኢኮኖሚያቸው እንዲያንሰራራ እና ስነ ልቦናዊ ቀውስን መቋቋም እንዲችሉ ብዙ ሊሰራ እንደሚገባ ጠቁመዋል።

ተጎጂዎቹ አስቸኳይ ድጋፍና እንክብካቤ የሚፈልጉ መሆናቸውን የጠቆሙት ኮሚሽነሩ፣ መንግሥት እና ዓለም አቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅት በአካባቢው የሚገኙ ተጎጂዎችን መልሶ ለማቋቋም በሚደረገው ጥረት እገዛ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የማይካድራ ጥቃት ቀላል የወንጀል ድርጊት አይደለም፣ አስቀድሞ የታቀደና በጥንቃቄ የተቀናጀ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰት ነው ያሉት ዶ/ር ዳንኤል፤ የአካባቢው የፀጥታ መዋቅር ለጥቃቱ ተጠያቂ ከሆነው ሳምሪ ከሚባለው ቡድን ጋር ተባብሮ ንጹሃንን ከጉዳት ከመጠበቅ ይልቅ ጥቃቱን መደገፉንና በጥቃቱ መሳተፉን አስረድተዋል።

ወንጀሉ በአካባቢው በነበረው ሚሊሻዎችና ፖሊሶች ድጋፍና ተሳትፎ የተፈጸመ ነው ያሉት ዶ/ር ዳንኤል፤ ለወንጀለኞች ድጋፍ ያደረጉ እና የተሳተፉ የአካባቢው የፖሊስ እና ሚሊሻ አባላት በሕግ ፊት ተጠያቂ መሆን አለባቸው ብለዋል።

ኮሚሽነሩ አክለውም፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ከዚህ ቀደም ተፈጽሞ የማይታወቅ አይነት ጭካኔ የተሞላበት የወንጀል ድርጊት እንዴት እንደተፈጸመና እንደተቀነባበረ ተጨማሪ ምርመራዎችን ማካሄድ እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል።

የቅድሚያ ሪፖርቱ በቁጥር እና በጉዳት መጠን ላይ ትኩረት ተደርጎ የተዘጋጀ መሆኑን ያብራሩት ዶክተር ዳንኤል፤ ጭፍጨፋው ያስከተለው የስነልቦና-ማህበራዊ ተፅእኖው እንዲሁም ወንድም ወንድም ላይ እንዴት እንዲህ አይነት ጭካኔ የተሞላበት ግፍ ሊፈጽም እንደቻለ የዘርፉን ባለሙያዎች ትንታኔ እና አካታች ጥናት እንደሚፈልግ ጠቁመዋል። (ኢፕድ)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, Social Tagged With: mia cadra, my cadra, operation dismantle tplf, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Tesfa says

    December 3, 2020 07:30 am at 7:30 am

    የጨነቀለት ጦሩ በወያኔ ካሃዲዎች ተከቦ ከበባውን ሰብረው ጦሩን እንዲተነፍስ ያደረጉት የአማራ ልዪ ሃይል፤ ሚሊሻና ፋኖዎች የማህል ሃገር ሚዲያዎች ስለ ጀግንነታቸው ዝም ይበሉ እንጂ ስራቸው ጎልቶ ታይቷል። እልፍ ህዝብ የጨረሰውና ነገርን ሁሉ ለራሱ ብቻ የሚያስበው የወያኔ የጥፋት ሃይል ዛሬም በተለያየ ስምና የፓለቲካ አባዜ ገና ከጅምሩ የትግራይ ህዝብ ተጎዳ በማለት ሲጮሁ መስማት ያማል። ማንም የአማራ ህዝብ የትግራይን ህዝብ በማይካድራ እንደተፈጸመው አይጨፈጭፍም። ወያኔና የእነርሱ ርዝራዦች አውሬዎች ናቸው። አንድ የሰራዊቱ አባል እንዳለው በሬሳችን ላይ ነው ታንክ የነድበት ብሎአል። የኢትዮጵያ መንግሥት ለወያኔ ትራፊዎችና የድብቅ አድናቂዎች በምክር ቤትም ሆነ በሌሎች የሃገሪቱ መድረኮች ምላሽ ለመስጠት ከመሞከር ይልቅ የሰሩትን ግፍ ለዓለምና ለኢትዮጵያ ህዝብ ማሳወቁ ተገቢ ነው። በቅርቡ ጠ/ሚሩ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች ጋር በነበራቸው ቆይታ የአረናው ተወካይ ያነሳውን ነጥብ መስማት ያማል። እነዚህ ሰዎች በምንም መልኩ ከዘራቸው ውጭ መተንፈስ አይችሉም። ተለክፈዋል። ስንት ህዝብ አልቆ፤ የሃገር መከላከያ ተክዶና ተገድሎ እሱ የአማራ ህዝብ ቆርቆሮ ነቀለ ይለናል። ደንቆሮ። ለምን በትግራይ የነበሩ የአረና አባላት የት ደረሱ ብሎ አልጠየቀም? እኔ መንግስትም ሆነ ቀሪው የኢትዮጵያ ህዝብ ትግራዋይ የሆኑትን ሁሉ በጡጦ ማባበል ቢቀር መልካም ይመስለኛል። 45 ዓመት ሙሉ የሃገሪቱን ንብረት ስዘርፍና ህዝባችን ሲገድል የነበረ ድርጅት ደጋፊና የስራ አስፈጻሚ የነበሩ ሁሉ ሊፈተሹ ይገባል። ስንቶች ናቸው ምድሪቱን ለጠላት አሳልፈው የሰጡት? ስንቶች ናቸው ከማህል ሃገር ታፍነው ትግራይ በርሃ ውስጥ ተገድለው የተጣሉ። የጠ/ሚሩ የመለማመጥ ፓለቲካ አይሰራም። ቆራጥ አመራር አስፈላጊ ነው። የወያኔ ትራፊዎች ከፈለጉ ተመልሰው በረሃ ይግቡ። ዛሬም ትላንትም ዝርፊያና ግድያ ነው ተግባራቸው። የተለወጠ እይታ የላቸውም። በተንኮል የተካኑ ናቸው። ምናቸውም አይታመንም። በሃይለስላሴ ዘመን፤ በደርግ ጊዜ ሁሉ ከሥር ሆነው ወገኖችን ሲያስገድሉና ሲገሉ የነበሩ ለመሆናቸው መረጃዎች አሉ። ሌላው ቀርቶ በስደት ዓለም እንኳን እሱ/እሷ አማራ ናት ኦሮሞ ነው ብለው ከሰፈር የሚያስባርሩ፤ የውሸት ወሬ በማናፈስ ግጭት የሚፈጥሩ፤ በደቦ ሰውን የሚደበድቡ፤ ሰዎች ከሥራ እንዲባረሩ የውሸት ሴራ የሚሸርቡ ናቸው። ጥላቻቸው ውስጥ ዘልቆ የገባ ከእውነት ጋር የተጋጨ በመሆኑ አሁን እንሆ እንደ ህጻን አስበው የሮም አወዳደቅ ወደቁ። ስለሆነም ጠ/ሚሩ የትግራይ ተወላጆችን ማባበል ቢቀርባቸው ይሻላል። ያኔም የእንደመር ልመናቸው ነው እዚህ ያደረሰን። እንዴት እልፍ ህዝብ ሲገል የነበረ የአጋዚ ጦር መሪ የሰሜን እዝ የመገናኛ የሬዲዪ ሃላፊ አድርጎ ይሾማል። የሚገርም ነው። የሚያሳዝን።
    ይህ የአረና ተወካይ ነኝ ባይ በማይካድራ ወያኔ የፈጸመውን ወንጀል፤ በሁመራ በየሆስፒታሉ ሞተው የተገኙ ወገኖች፤ በሁመራ አየር ማረፊያ ግቢ ተረሽነው ስለተገኙ አማራዎች፤ ተክደው ስለተገደሉ የሃገሪቱ ወታድሮች አይገደውም። ጭኾቱ አሁንም እቃ እቃ ጫወታ ነው። 45 ዓመት መርዝ ለመንቀል ገና ብዙ ረጅም ጊዜ ይጠይቃል። በውጭ ሃገር፤ በሰፈራ ጣቢያ በሃገሪቱ መ/ቤቶችና ወታደራዊ ተቋማት ወዘተ… የዘረጉት መረብ መመንጠር አለበት። ይህ ሴራ ታልሞ ከስራ እስከዋለበት ድረስ አንድም የወያኔ የሴራ ተካፋዪች ትንፍሽ አላሉም። ሃገር ወዳድ የሰው ልጅ ህይወት ቢገዳቸው ኑሮ ቀኑ ከመድረሱ በፊት አንዳቸው ለመንግስት ሹክ ባሉ ነበር። ለዚህ ነው በዘራቸውና በቋንቋቸው የሰከሩ የሰው ባህሪ የሌላቸው ጉዶች ናቸው የምንለው። አማራ ጠላትህ ነው እየተባለ ለዘመናት የተሰበከለት የትግራይ ህዝብ ሊነቃ ይገባል። አማራ የትግራይ ህዝብ ጠላት ሆኖ አያውቅም። ወያኔና ጭፍራዎቹ ግን ያኔም ዛሬም የአማራ ህዝብ አንድነትና ሰላም ጠላቶች ናቸው። የማይካድራው ግድያ የወያኔ የመጨረሻው ጭፍጨፋ እንደሆነ አርገው የሚመለከቱ ሁሉ ተሳስተዋል። አሁንም ጊዜ እና እድል ካጋጠማቸው የበለጠ ጉዳት ያደርሳሉ። የአጥር ፈረሰብኝ የአረና ተወካዪ ጥያቄም ከዚህ ደባ ጋር አብሮ ሊታይ ይገባል። ሁሌ ተበደልኩ እያሉ መጮህ ይቁም! እኛም ሰሚ እናግኝ! በቃኝ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ February 6, 2023 02:03 am
  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule