• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኢንተርፖል፤ የህወሃት ሳምሪዎች የማይካድራ ጭፍጭፋ ከቦኮሃራም የከፋ ነው

February 4, 2021 11:10 am by Editor 2 Comments

በማይካድራ ሳምሪ በተሰኙ የተደራጁ ወጣቶች የተፈጸመው የጅምላ ጭፍጨፋ ቦኮሀራም ናይጄሪያ ላይ በተመሳሳይ ወር ከፈፀመው ወንጀል የበለጠ እንደሆነ ኢንተርፖል አስታወቀ።

ዓለም አቀፉ የፖሊስ ትብብር ተቋም ኢንተርፖል በፈረንጆቹ የዘመን አቆጣጠር በወርሃ ህዳር 2020 ዓ.ም በመላው ዓለም የተፈፀሙ 10 አስከፊ  የሽብር ጥቃት አስመልክቶ ሪፖርቱን አውጥቷል።

እንደዚህ ሪፖርት ከሆነ በህወሃት ቡድን አደራጅነት ማይካድራ ላይ የተፈፀመው የጅምላ ግድያ ቦኮሃራምና ሌሎች የሽብር ቡድኖች በተለዩ ሀገራት ከፈፀሟቸው አሰቃቂ ጭፍጨፋዎች በመብለጥ በርካታ ንፁሃን ሰዎች ህይወታቸውን ያጡበት ኢሰብዓዊ ድርጊት ነው፡፡

የህወሃት ቡድን አስታጥቆ እንዳሰማራቸው በተገለጸው ሳምሪ የተሰኙ የወጣቶች የጥቃት ቡድን በማይካድራ በፈፀሙት ማንነትን መሰረት ያደረገ የጅምላ ጭፍጨፋ 600 ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውን በኢንተርፖል የሽብር ወንጀል መከላከል ዳይሬክቶሬት ያወጣው መረጃ ያሳያል።

ከሶስት ወራት በፊት በህዳር ወር ላይ ብቻ በተፈፀሙ የሽብር ወንጀሎች አፍሪካ ቀዳሚ ስፍራ ላይ መቀመጧን የጠቀሰው የኢንተርፖል መረጃ ንፁሃን ላይ ባነጣጠሩ የጅምላ ግድያ ወንጀሎች በርካታ ህይወት መቀጠፉን አስገንዝቧል።

የሽብር ቡድኖቹ ከሰብዓዊ ፍጡር በማይጠበቅ መልኩ ጭካኔ የተሞላባቸውን የጅምላ ጭፍጨፋዎች መፈፃማቸው የተገለፀ ሲሆን ከአፍሪካ በመቀጠል ደቡባዊ የእስያ አካባቢና ምስራቃዊ የሜዲትራኒያን ቀጠና የዚህ ሽብር ወንጀል ሰለባ መሆናቸው ተጠቁሟል።

ባለፈው የፈረንጆች ዓመት ወርሃ ህዳር ላይ ብቻ በተፈፀሙና በርካቶች በአሰቃቂ ሁኔታ ህይወታቸውን ባጡባቸው የሽብር ወንጀል ድርጊቶች ላይ ትኩረቱን ያደረገው የኢንተርፖል መረጃ በኢትዮጵያ ማይካድራ ላይ የተፈፀመው የጅምላ ጭፍጨፋና ናይጄሪያ ውስጥ ሜይጉዱሩ ተብሎ በሚጠራው ስፍራ ቦኮሃራም ያካሄደው ግድያ በሰብዓዊነት ላይ ከተፈፀሙ ከባድ የሽብር ወንጀሎች ቀዳሚ ተርታ ላይ መሰለፋቸውን ያሳያል።

“የማይካድራ ጭፍጨፋ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ሰብዓዊ፣ ስነልቦናዊ ቀውስና ጥልቅ ሀዘን ያስከተለ ነው” – ዶ/ር ዳንኤል

የተለያዩ ኢሰብዓዊ ዓላማዎችን ይዘው የሚንቀሳቀሱ የሽብር ቡድኖች በንፁሃን ላይ የሚፈፅሟቸው ግድያዎች አሳሳቢ መሆናቸው በመረጃው ተጠቅሷል።

ከሶስት ወራት በፊት የንፁሃንን ህይወት የቀጠፉ የሽብር ወንጀሎች ከተፈፀሙባቸው ሀገራት መካከል ኢትዮጵያን፣ ናይጄሪያን፣ ሞዛምቢክን፣ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎን፣ ሶማሊያን፣ ቡርኪናፋሶንና ቻድን የያዘችውን አፍሪካን በቀዳሚነት ጠቅሷል።

ከሌሎች የአለም ክፍሎች ደግሞ ከደቡብ እስያ አፍጋኒስታን፣ ከምስራቅ ሜዲትራኒያን ሶሪያን እንዲሁም ኢንዶኔዥያንና ኦስትሪያን አካቷል።

የሽብር ቡድኖ ቹ በእነዚህ ሀገራት በፈፀሟቸው አሰቃቂ የጅምላ ግድያዎች እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በህዳር ወር 2020 ዓ.ም ብቻ አንድ ሺ የሚጠጉ ንፁሃን ዜጎች መገደላቸውን ኢንተርፖል ያወጣው መረጃ ይጠቁማል።

ኢንተርፖል ያሰባሰበው የመረጃው ግኝት እንደሚያሳየው መንግስታዊ ባልሆኑ ታጣቂ ቡድኖች ከተፈፀሙ ጥቃቶች አራቱና በከፍተኛ ሁኔታ የንፁሃንን ህይወት የቀጠፉ የሽብርተኝነት ወንጀሎች በአፍሪካ፣ በደቡብ እስያ (በዋናነት በአፍጋኒስታን) በባህረ ሰላጤ አካባቢ ሀገራት በዋነኝነት በየመንና በምስራቅ ሚዲትራኒያን (በሶሪያ) የተፈፀሙ መሆናቸውንም አመላክቷል።

በኢትዮጵያ ሳምሪ የተሰኙ የህወሃት ቡድን ያደራጃቸው ሃይሎች ማይካድራ ላይ የፈፀሙትና በናይጄሪያ ቦኮሀራም የተፈፀሙት ኢ-ሰብአዊ ጭፍጨፋዎች ከሁሉም የከፋ እልቂት የተመዘገበባቸው የሽብር ወንጀሎች መሆናቸውን የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ኢንተርፖል የላከለትን መረጃ ዋቢ አድርጎ አድርሶናል፡፡ (ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, News Tagged With: boko haram, mia cadra, my cadra, operation dismantle tplf, tplf

Reader Interactions

Comments

  1. Mai-Kdra Man says

    February 5, 2021 03:15 pm at 3:15 pm

    Please provide a link to the interpol report – your interpretation is not enough – to verify if it said what you said then so you should have no problem. If it just reported on mai-kadra massacare but didn’t hold any party responsible, which I suspect, then you are bending the truth. Interpol would’t say what you said, it just reported it for it would have provided evidnce as to who committed this crime.

    Reply
  2. Tesfa says

    February 11, 2021 03:00 pm at 3:00 pm

    በተደጋጋሚ እንዲህ ብዬ ነበር። ወያኔ ማለት እባብ ነው። ሰውነቱ ተቆራርጦ ለየብቻ የሚንቀሳቀስ የአካል ክፍል ያለው እባብ ነው። አሁን በየሥፍራው የትግራይ ህዝብና ወያኔ አንድ አይደለም የሚሉ ሾተላዮች ቃላቸውን በየጊዜው እየሰለቀጡት ነው። ለእኔ ሁሉም ባይሆን ይበልጡ የትግራይ ህዝብ አውቆም ሆነ ሳያውቅ ወያኔን ይደግፋል። አሁን በመቀሌ የሚደረጉት የሥራ ማቆም አድማ፤ የወረቀት መበተን፤ የሴቶች መደፈር፤ ዝርፊያ ሁሉ የወያኔ የ 45 ዓመት የፓለቲካ ሴራው ሽራፊ አካል ነው። ወያኔ ለሰው ልጆች የማይገደው በሰው ደም ነጋዴ እንደሆነ በሰሜን ጦር ላይ የፈጸመው ደባ ሳያሻማ ጭካኔአቸውን ያሳያል። በማይካድራ የተሰራው እልቂት በሌሎች ክልሎችም የሆነና አሁንም በመፈጸም ያለ የክልልና የዘር ፍጅት ነው። ተራበ ተፈናቀለ ወዘተ የሚባለውም የትግራይ ህዝብ ብቻ አይደለም ይህ መከራ የሚዘንብበት ከትግራይ መፈናቀል በፊት ሜዳ ላይ የወደቁ እልፎች አሉ። ለእነርሱ ብዙም ኡኡታ አይሰማም። በሬ ወለደ በተባለ የፓለቲካ ትርክት እኔን እዩኝ ሌላውን ተውት እየተባለ ለዛሬ ደርሰናል። ታዲያ ኢንተርፓል ስለ ማይካድራው ጉዳይ እንዲህ ብሎ ከሆነ እልፍ ሰው በሌሎች ከተሞች አንገቱ ሲታረድና ቤቱ ሲቃጠል ለምን ዝም አለ? ግን ይህችን እወቁ ነጩና አረቡ አለም ከመካከል ቆሞ እሳት እያቀበለ እኛ እርስ በእርሳችን እንድንተላለቅ ለዘመናት ተንኮል ሽርቧል፤ አድርገውታል፤ እያደረጉትም ነው። ፓለቲካው የማጣጣት ፓለቲካ ነው። አንድ ሲታሰር ሌላው ይፈታል። አንድ ሲሞት ሌላው ቋሚ ነኝ ይላል። ያዙሪት ፓለቲካ። አበዳሪዎቹ እነርሱ፤ አስታጣቂዎቹ እነርሱ፤ ዞር ብለን ራሳችንን መመልከት እስካልቻልን ድረስ የውጭ ሃይሎች መጠቀሚያ፤ ለጊዜአዊ ጥቅም ወገንን የምናሳድድ፤ በእህትና በወንድማችን አስከሬን ላይ የምንጨፍር የድር አራዊቶች ነን። ሞት ለማንም አይቀርም። ግን በዘር ተሰልፎ ሌላውን ገድሎ እኔ እሰነብታለሁ ማለት የዝንብ እድሜን መሸመት ነው። መስሎህ ነው እንጂ አትኖርም። አሁን ማን ይሙት የወያኔ 45 ዓመት የፓለቲካ እድሜ እረጅም ነው። ጭራሽ። ያን ያህል እድሜ ያላቸው በራሪ ወፎች አሉ። የተንኮልና የመጠላለፍ ፓለቲካ ስለሆነ ሁልጊዜም የሚሰላው በጥቅማ ጥቅም ዙሪያ ላይ በመሆኑ ነጻ እናወጣሃለን የተባለውም ህዝብ፤ ለሃገር ግንባታ ቆመናል ብሎ የተለፈፈለትም ወገን ሁሉም ከዘመናት በህዋላ በአለበት ሲረግጥ ማየት እንዴት ይዘገንናል። በአውሮፓ፤ በሰሜን አሜሪካ በሌሎችም የዓለም ክፍል በየምክንያቱ ከሃገር ወጥተው የተሸጎጡ የስማ በለው የፓለቲካ አዳማቂዎች እባካችሁ ከሆነላችሁ እቃቹሁን ጠቅላቹሁ ለምታምኑበት እዚያው ቦታው ላይ ሂዳችሁ ተፋለሙ። በፈጠራ ወሬ ህዝባችን አታጫርሱ። አሁን ማን ይሙት ለትግራይ ህዝብ ከኢትዮጵያ ህዝብ የበለጠ የሚያስብለት ይኖራል? ፍጽም። ግን ያው 45 ዓመት ሙሉ በወያኔ የተዘራው የፈጠራ ፓለቲካ እውነቱን በውሸት የለወጠ፤ የቆመን አፍርሶ የራሱን ሃውልት ያቆመ፤ የሌለ ታሪክ ጽፎና ከፍሎ ያጻፈ በመሆኑ ከዚህ የፓለቲካ ትብታብ ለመውጣት ጊዜ ይፈጃል። ከላይ እንዳልኩት ለትግራይ ህዝብም ሆነ ለወያኔ አፍቃሪዎች ለአመጽ ወረቀት ከመበተን፤ ጠበንጃ ይዞ በየበረሃው ከመንከራተት በጠራ ዲሞክራሲ የትግራይ ህዝብ ራሱ በመረጠው ወገን እንዲተዳደርና የዲሞክራሲ አሰራር እንዲጎለብት መስራቱ መልካም ነው። በወያኔ ላይ የቀለድበት ሱዳንና ግብጽ ናቸው። በአንድ ቀን ጦርነቱን ለመክፈት አብረው ተማምለው (የስዪም መስፍን የመጨረሻ ቃለ መጠየቅ መረጃ ይሰጣል) ወያኔ ቸኩሎ መግደል ሥራው በመሆኑ በብዙ ሺ የሰራዊቱ አባላትን በመጨፍጨፉ ከሞት የተረፈው አብሮ አይቀጡ ቅጣት ሰጥቷቸዋል። ግን አልሞቱም። የት አለ ዶ/ር ደብረጽዪን፤ የታለ ጌታቸው ረዳ? የት ጌታቸው አሰፋ? ጄኔራሎቹ ሁሉ የት አሉ። አሁን ስልክም መብራትም በትግራይ ውስጥ አገልግሎት ስለጀመረ፤ መቀሌ ላይ ቁጭ ብሎ በዚህ መንገድ እንዲህ ያህል ወታደር እየተንቀሳቀስ ነው በማለት ለበረሃ ጓዶቻቸው ወሬ ነጋሪ ሆነው ስንት ወታደሮች ነው በቅርብ የሞቱት? ስለሆነም የትግራይ ጉዳይ ገና ያለየለት ብዙ ስር ግብ የቀረው እንደሆነ ያሳያል? ለመሆኑ ማን ነው ለወታደሩ ምግብ የሚያቀርበው? ከየትስ ነው የሚገዛው ወያኔ ሰውን በመመረዝ የተካነ ነው። ይታሰብብት። ብዙ ጉድ አለ ያልተባለ። በቃኝ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ባልደራስ የአገርን ደኅንነት አደጋ ላይ በመጣል ሊጠየቅ ይገባዋል ተባለ July 1, 2022 09:23 am
  • “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ June 29, 2022 03:30 am
  • “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ June 28, 2022 01:07 pm
  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am
  • ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን May 26, 2022 09:18 am
  • “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች” May 26, 2022 08:19 am
  • ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ May 25, 2022 01:57 am
  • የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች May 19, 2022 09:37 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule