አብይን የምደግፈው አዎ ለራሴ ስል ነው! ከፀፀት ለመዳን፤ ከህሊና ወቀሳ ለመትረፍ ስል! ዶክተር አምባቸው መኮንን ከተገደለ በኋላ የተሰማኝን ስሜት እኔ ነኝ የማውቀው። የክልሉ ፕሬዝዳንት ሆኖ በሀላፊነት በቆየባቸው ሶስት ወራት ጊዜ ውስጥ በውጥረት ተከቦ በርካታ በጎ ስራዎችን አከናውኗል። ጥሩ ስራ ሲሰራ አንድም በጎ ቃል ትንፍሽ አላልኩም ነበር።ኦሮሚያ ክልል ሄዶ ስለልዩ ጥቅም አወራ ሲባል ግን እሱን ለመተቸት ማንም አልቀደመኝም። አሁን የአምባቸውን ምስል ፌስቡክ ላይ ባየሁ ቁጥር ፀፀቱ ይገርፈኛል። እሱን ተችቼ የፃፍኩትን ፅሁፍ ከፌስቡክ ገፄ አጥፍቸዋለሁ። የጥፋተኝነት ስሜቱ ግን ከህሊናየ ሊጠፋ አልቻለም። ይህ ፀፀቴ በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ እንዲደገም አልፈልግም። ዶክተር አብይ ወደስልጣን ከመጡ በኋላ ተዘርዝረው የማያልቁ በርካታ ለውጦችን ያመጡ ቢሆንም ከምስጋና ይልቅ … [Read more...] about አብይን የምደግፈው ለራሴ ስል ነው!
Opinions
የኔ ሃሳብ
የተሸጠውን ግድብ ዐብይ ገዛው‼
ታታሪው ሰው ነገሮች ሁሉ ከተጠናቀቁ በኋላ መግለጫ ሰጠ። መግለጫ እንዲህ በረከሰበት ዘመን እሱ ገላለጠው!! “የግድቡ የመጀመሪያ ምዕራፍ ሙሌት ተጠናቅቋል። እንኳን ደስ ያለን” አለ። እኔ ግን ከፋኝ!! ቅር አለኝ! ደነገጥኩ!! “ግድቡን የሸጠው ጠቅላይ ሚኒስትር” የሚለው ትንታኔ ተናነቀኝ። ተጽፎ፣ ተነብቦ፣ ተቀርጾ፣ ተቀናብሮ፣ ስምና ባለቤት ኖሮት ለአለም የቀረበው ትንተና ትዝ አለኝ። ዕውቀት ቀፈፈሽ። ስዩም መስፍን ያለቀሰለት ግድብ ትዝ አለኝ። ጌታቸው ረዳ ሲሸጥ ያየው ግድብ ትዝ አለኝ። አሜሪካና አለም ባንክ፤ ግብጽና ጂዳ ተጠቃቅሰው የገዙት ግድብ ትዝ አለኝ። ተደራዳሪዎቹ እየቆራረሱ የቸበቸቡት ግድብ ትዝ አለኝ። ያለ ልምድ፣ ያለ እውቀት እና ያለሀገር ፍቅር የተመራው የድርድር ቡድን አይኔ ላይ ድቅን አለብኝ!! ይሄ ሁሉ የክስ ናዳ፤ ይሄ ሁሉ የትንተና ካብ ስድስት … [Read more...] about የተሸጠውን ግድብ ዐብይ ገዛው‼
“ኦነግ ሸኔ የህወሓት መጠቀሚያ ዕቃ ነው” ታዬ ደንደኣ
የኦሮሞ ሕዝብ ትግል ፍሬ እንዳያፈራ ትልቁ ተግዳሮት የነበረው ኦነግ ሸኔ መሆኑን የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታዬ ደንደኣ አስታወቁ። ህወሓት ኦነግ ሸኔን በአደባባይ እንደ ጠላት እየፈረጀ በተግባር ግን የኦሮሞን ትግል ለማክሰም እንደ መሣሪያ ይጠቀምበት እንደነበረም አመለከቱ። አቶ ታዬ ደንደኣ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ያካሄደው የፍትህ የእኩልነትና የነፃነት ትግል ፍሬያማ እንዳይሆን ኦነግ ሸኔ ከህወሃት ጋር የነበረው ከሕዝብ የተሰወረ ህብረት ዋንኛ ምክንያት ነው ብለዋል። ኦነግ ሸኔ የኦሮሞ ታጋዮች አንድ ወጥመድ ሆኖ ለህወሃት ሲያገለግል እንደነበርም አመልክተዋል። ብዙዎች ኦነግ ሰፊ የሕዝብ ድጋፍ እያለው የዚህ ድርጅት ትግል ለምንድን ነው ወደፊት ገፍቶ የማይመጣው? የሚል ጥያቄ ነበራቸው። … [Read more...] about “ኦነግ ሸኔ የህወሓት መጠቀሚያ ዕቃ ነው” ታዬ ደንደኣ
ህወሓት ይፍረስ፤ ዕልቂት ሰባኪዎች ለፍርድ ይቅረቡ!
“ሃጫሉን የገደሉት ነፍጠኞች ናቸው፤ መላው የኦሮሞ ህዝብ የምኒሊክን ሃውልት አፍርሰህ ወደ ቤተመንግሥት ገስግስ!” ይህንን የዘር ዕልቂት የተናገረው የዶ/ር ዐቢይ የለውጥ ቡድን እነ ጃዋር መሃመድን በቁጥጥር ሥር ከማዋሉ በፊት በሕወሃት የደም ገንዘብ የሚቀለበው ሕዝቅኤል ጋቢሣ አሜሪካ ቁጭ ብሎ ሕወሃት ባደራጀው ዲጂታል ሚድያ በመጠቀም ሲያውጅ ነበር። “በደረሰን መረጃ መሠረት፤ የሃጫሉ ሁንዴሳ ገዳዮች ነፍጠኞ ሳይሆኑ ሥልጠናና ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የመጡ ትግርኛ ተናጋሪ ኤርትራውያን ናቸው፤ እኔ በደንብ አውቃለሁ እነማን እንደገደሉት፤ ምን ዓይነት ሚሊተሪ ፐርሶኔል እንደተሳተፈም አውቃለሁ፤ ኢትዮጵያውያን እንኳን አይደሉም፤ ኤርትራውያን ናቸው" ይህን የተናገረው ደግሞ በጎጥ አስተሳሰብ እጅግ የጠበበው መርዘኛው ፀጋዬ አራርሳ ነው። ፀጋዬ አራርሣ፤ ሃገር መምራት የማይችል ደካማ ነው፤ … [Read more...] about ህወሓት ይፍረስ፤ ዕልቂት ሰባኪዎች ለፍርድ ይቅረቡ!
አርቲስት ሃጫሉ ለምን ተገደለ?
https://www.facebook.com/goolgule16/videos/856526528088415 … [Read more...] about አርቲስት ሃጫሉ ለምን ተገደለ?
ሕልመኛና የቆሰለው አውሬ ጃዋር [እና] ዋኤል ጎኒም
[ጁን 8፤ 2010] ዋኤል ጎኒም (ዕድሜ 28) እንደወትሮው ዜናዎችን ለመቃረም፣ ከዘመድና ወዳጅ ጋር ለመወያየት ዱባይ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ተቀምጦ በፌስቡክ መስኮት ወደ ትውልድ ሀገሩ ግብጽ ዘለቀ፤ በዚያን ዕለት ያነበበው ዜና እና የተመለከተው ፎቶ ስሜቱን አወከው፣ እረፍት ነሳው፣ ዜናው አሌክሳንድሪያ ውስጥ በሙባረክ የጸጥታ ሀይሎች በግፍ ስለተገደለው ካሊድ ሰይድ (ዕድሜ 28) ነበር፡፡ ሶሻል ሚዲያ ላይ ሲዘዋወር የነበረው የካሊድ አስከሬን በዐይን ለማየት ይከብዳል፡፡ “በዛ አሰቃቂ የካሊድ ፎቶ ውስጥ ራሴን አየሁት፣ በካሊድ ቦታ እኔም ልሆን እችል ነበር ብዬ አሰብኩ” ይላል ዋኤል በዚያች ቅጽፈት የተሰማውን ስሜት ሲገልጽ፣ ከቁጭትና ንዴት ባለፈ አንድ ነገር ማድረግ እንዳለበት አሰበ፤ ጊዜ ሳያጠፋ ማንነቱን ደብቆ "We are all Khaled Said/ሁላችንም ካሊድ ሰይድ ነን" … [Read more...] about ሕልመኛና የቆሰለው አውሬ ጃዋር [እና] ዋኤል ጎኒም
ዘረኛ ፋሺስቶችን ለፍርድ እናቅርብ
የፋሽስታዊው አመለካከት ያላቸው (ethno-fascists) የጸጋዬ አራርሳ፣ የህዝቄል ገቢሳ፣ መሰሎቻቸው፣ እንዲሁም የትግራይ ሚዲያ ሀውስ መርዘኛ፡ ሃሰተኛ ቅስቀሳዎችና ትርክቶች የብሄር ለብሄር፣ የዘር ፍጅት (ጄኖሳይድ) ከማድረሳቸው በፊት በአለም ዙሪያ የሚገኙ ሀገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን ሁሉ በጋራ ሆነው የተደራጀ፣ የተቀናጀ፣ የተናበበ ስራ መስራት ይገባል። ባልተናበበና በተበታተነ ሁኔታና እንቅስቃሴ ውጤት ለማምጣት እጅግ አዳጋች ይሆናል፣ ሁሉም ባለው መሰለፍ ይገባል፣ የመጣውን ኣደጋ ለመከላከል እንደ ኢትዮጵያውያን ዜጎች በጋራ መቆም የግድ ነው። የፖለቲካ አመለካከት ወደ ጎን አድርጎ በአንድ ላይ፣ በጋራ መቆም ወሳኝ ይመስለኛል። የሁላችንም ሀገር የሆነችው ቤተሰብ፣ ዘመድ፣ አዝማዶች፣ ወገኖችና፣ ባጠቃላይም ህዝባችን የሚኖርባት ሀገረ ኢትዮጵያ ውስጥ እየሆነ ያለው ሁኔታ ፍጹም ወደ … [Read more...] about ዘረኛ ፋሺስቶችን ለፍርድ እናቅርብ
እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እንደ ስያሜው የኢትዮጵያዊያን ነው። ከአቶ ተፈራ ደግፌ 1956 ዓ.ም. እስከ አቶ በቃሉ ዘለቀ 2010 ዓ.ም. በትውልድ ቅብብሎሽ ዘር ሳይለይ፣ ጎሳ ሳይመርጥ የኢትዮጵያና የኢትዮጵያዊያን ሆኖ የዘለቀ አንጋፋ ባንክ። አቶ ተፈራ ደግፌ መጋቢት 12 ቀን 1956 ዓ.ም. ባንኩን ከመረከባቸው በፊት፣ ባንኩ ለኢትዮጵያዊያንና ለአገራችን እምብዛም ግድ በማይሰጣቸው ለራሳቸው ጥቅምና የኢኮኖሚ ዕድገት በሚታትሩ የውጭ አገር ዜጎች ይመራ ነበር። ህንዳዊያን፣ አርመኖች፣ ግብፆችና አውሮፓዊያን አቶ ተፈራ ወደ ሥልጣን ከመምጣታቸው በፊት ባንኩን የኢትዮጵያ መንግሥት ባንክ በሚል ስያሜ ያስተዳድሩ የነበሩ ናቸው። ይህን የተረዱት አፄ ኃይለ ሥላሴ ጣሊያን አገራችንን ከለቀቀ በኋላ ኢትዮጵያዊያን የባንክ፣ የኢንሹራንስና የሕግ ዕውቀቶችን እንዲያዳብሩ ወደ ተለያዩ የአውሮፓ … [Read more...] about እየተፈረካከሰ ያለው አንጋፋው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥
ኢትዮጵያ ስንት ልጆች ወለደቸ፤ ስንቱን አስተማራቸ፤ ስንቱን አቋቁማ ለአቅመ ዓዳም አበቃች፤ ስንት ጉድስ ተሸከመች። ቆጥረን ስለማንዘልቀው ቤቱ ይቁጠረው ብለን ብናልፈው ይበቃል። ብዙ ጉድ እንደተሸከመች ብናውቅም ብዙ ልጆቿ ሸክሟን ለማቅለል፤ ችግሯን ለመቅረፍ፤ እድገቷን ለማፋጠን ብዙ ጥረውላታል። በእውቀታቸው፤ በጉልበታቸውና በሃብታቸው ባቻ ሳይሆን ሕይወታቸውን ጭምር ገብረውላታል፤ እየገበሩም ይገኛል። በአንፃሩ በሃብቷ ተምረው ስሟን ያጎደፉ፤ ሕልውናዋን የተፈታተኑ ከሃዲዎች መኖራቸውን ስናይ እናዝናለን። እነዚህን የመሰሉ ልጆቿ ሃገሪቱን አመድ አፋሽ አርገዋታል። ይህ የቅርብ ጊዜ ክስተት ብቻ ሳይሆን በሶስት ሽህ ዘመን ጉዞዋ ሁሉ ሲከሰት የኖር ለመሆኑ ታሪክ ይነግረናል። ያአሁኑን ከጥንቱ ለየት የሚአደርገው ያለንበት ሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን መሆኑ፤ ልጆቿ ዘመናዊ ትምህርት … [Read more...] about ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥
ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል?
የዛሬ ሃምሳ ዓመት ገደማ መሰለኝ የያኔው ወጣት የዩኒቬርሲቲ ተማሪው ኢብሳ ጉተማ “ኢትዮጵያዊው ማን ነው?” በሚል ርዕስ አንድ ጽሁፍ አቅርቦ ለውጥ ፈላጊውን የዩኒቬርሲቲውን ማህበረሰብ ጥም ለማርካት የሞከረው። አብዛኛው የዩኒቨርሲቲው ተማሪ የፊውዳል ሥርዓቱ አገሪቷን ወደፊት እንዳትራመድ ጠፍንጎ የያዛት መሆኑን የተረዱና ሥርዓቱ ካልተለወጠ የሕዝቦቿ አብሮነት ውሎ አድሮ መሸረሸሩ አይቀሬ መሆኑን ተገንዝበው ኢትዮጵያንና ኢትዮጵያዊነትን ለማናበብ መላ ይመቱ ነበርና የዚህ ንቁ ተማሪ ግጥም ጊዜውን ጠብቆ የመጣ ነበር። በዚሁ ጊዜ ነበር ከተማሪው እንቅስቃሴ መሪዎች አንዱ የነበረው ዋለልኝ መኮንን የብሄር ጥያቄን አስመልክቶ ታሪካዊውን ጽሁፍ ያቀረበው። አንዳንዶች ያኔም ሆነ ዛሬ እነዚህን ጽሁፎችን አስመልክቶ ሁለቱን ንቁ የተማሪው ማህበረሰብ አባላትን አገሪቷን ለመበታተን ሆን ብለው … [Read more...] about ኢትዮጵያዊ ምን ይመስላል? በምንስ ይመሰላል?