Good Morning to everyone here. First of all, I would like to give my deepest sympathy to the family of Professor Mesfin Woldemariam and the great numbers of Ethiopians who consider him a great friend of the Ethiopian people for many generations. I also thank those who have given me the opportunity to speak today about one of greatest men I have been privileged to meet and know. This giant of a man has played an important and strategic role in my life and that of many others. Most people … [Read more...] about “In Honor and Remembrance of the Life of Professor Mesfin Woldemariam” Obang
prof mesfin
ፕሮፍ ተሸኙ!
የጂኦግራፊ ሊቅ የሰብዓዊ መብት ተሟጋችና ደራሲ መስፍን ወልደ ማርያም (ፕሮፌሰር) (1922-2013) “አንድ ትውልድ ይወለዳል፣ በጊዜው እንደጊዜው ያድጋል፣ ያልፋል፣ በሌላ ትውልድ ይተካል። አዲሱም ትውልድ የተረከበውን ቅርስ ይዞ ይነሳና በራሱ ጥረት አዳዲስ ሥራዎችን ሠርቶ ይጨምርበትና ያድጋል፣ አዲስ ነገርን ትቶ ያልፋል። የቀደመው ትውልድ ተፈጥሮና ኑሮው ከሚያስገድደው በላይ ለሚቀጥለው ትውልድ መስዋዕት መሆን አይችልም፣ አይጠበቅበትምም። በምፅዋትና በሞግዚት አስተዳደር የሚኖር ትውልድ ለሚቀጥለው ትውልድ የሚያስተላልፈው ዕዳ ብቻ ነው፣ ዕዳን በውርስ ተሸክሞ የሚፈጠር ትውልድ ያለምርኩዝ መንቀሳቀስ አይችልም፣ ምርኩዝ ሊሆኑት የሚችሉት እነዚያው የዕዳው ባለቤቶች ናቸው። ስለዚህም ከዕዳና ከምፅዋት አዙሪት አይወጣም።” ይህን ጠሊቅ ዕይታ የትውልድ ቅብብሎሽ አንፃራዊ ገጽታና ትችት … [Read more...] about ፕሮፍ ተሸኙ!
የኔታ መስፍን ወልደ ማርያም የዘመን ዕንቁ! የትውልድ ዋርካ!
መስከረም 20፤ 2013 ዓም የትውልድ ዋርካ፤ የዘመናት ዕንቁ የሆኑትን የኔታ መስፍን ወልደ ማርያም ማረፋቸው ተሰምቷል። ስለ እርሳቸው ብዙ ማለት ይቻላል። ሞት ለማንም የማይቀር ቢሆንም ስለ እርሳቸው ዕረፍት እኛ ከምንናገረው በላይ ራሳቸው ስለ ሞት የተናገሩትን አትመነዋል። ከሁሉ በላይ “ዛሬም እንደ ትናንት” የተሰኘውን የመጨረሻ መጽሐፋቸውን ከሁለት ሳምንታት በፊት አሳትመው ማረፋቸው ለአገራቸው እስከመጨረሻው የተጉ የዘመናችን ዕንቁ! የኔታ መስፍን! የቅኔ ጌታ! የዕውቀት ገበታ! ቢባልላቸው በፍጹም የሚያንስባቸው አይደለም። የዛሬ ሦስት ዓመት ተኩል አካባቢ ጥር/2009 ስለራሳቸው ህይወትና ጻዕረሞት የጻፉትን በድጋሚ በማተም የስንብት ሐዘናችንን እንገልጻለን። ለቤተሰብ፣ ለዘመድ፣ ለወዳጅ፣ ለመላው የአገራችን ሕዝብ መጽናናትን እንመኛለን። ጎልጉል የድረገጽ … [Read more...] about የኔታ መስፍን ወልደ ማርያም የዘመን ዕንቁ! የትውልድ ዋርካ!
መንገዳችን በፍጥነት ይቃና!
በብዙ ዓይነት ወንጀሎች የሚታሙት የወያኔ አዛዦች ሥልጣናቸውን እንደያዙ ከሥልጣን ወረዱ ቢባል ግራ ይሆናል፤ ነገር ግን ሆነ! በሕጋዊ ምርመራ ሳይጣራና ከሳሾቹን በፍርድ ቤት ሳይሞግት የሰው ልጅ እንደከብት ከመንገድ በጉልበተኞች እየተያዘ መታሰር የቀረ መስሎን ነበር፤ አልቀረም አሉ! ጉልበተኞች በወንጀላቸው ክብደት ከሕግ ይከለላሉ ይባል ነበር፤ አሁንም ያው ይመስላል! ያነበብሁትን በትክክል ካስታወስሁት በጥንታውያን ግሪኮች ሰርቀው መያዝ እንጂ መስረቅ ወንጀል አልነበረም (የምታስታውሱ አርሙት)፤ የምንመሳሰለው በጥንታዊነት ብቻ መስሎኝ ነበር! ከዚህ ቀደም ጸጋዬ ገብረ መድኅን (ይመስለኛል) ተረግመናል ብሎ፤ ነበር፤ እኔንም መሰለኝ! ኢትዮጵያውያን መልካቸውን፣ ነብሮች ቆዳቸውን እንዴት ይለውጣሉ ያለው መልካችንን ነበር፣ ወይስ ጠባያችንን ማለቱ ነበር! ነገሬ ሁሉ የጥንቶቹን አባትና እናት … [Read more...] about መንገዳችን በፍጥነት ይቃና!
የኔታ እና ዶ/ር ዐቢይ፤ የኔታ ምን አሉ?!
ከ27 ዓመት በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ በጠቅላይ ሚኒስትር የስብሰባ አዳራሽ የተገኙት ፕ/ር መስፍን ወ/ማርያም፤ ዶ/ር ዐቢይ የዕለቱን የመወያያ አጀንዳ ከገለጹ በኋላ እና የስብሰባው ተሳታፊዎች አሳባቸው እየገለፁ ባሉበት ወቅት ነው፤ የኔታ ወደ መሰብሰቢያ አዳራሽ ውስጥ የገቡት። ዶ/ር ዐቢይን ጨምሮ በአዳራሽ ውስጥ የነበሩ ተሰብሳቢዎች የኔታ የመቀመጫ ወንበራቸውን እስኪይዙ ድረስ የተሰብሳቢው ዓይን በፍቅርና በአክብሮት እሳቸው ላይ ነበር ያረፈው። የተጀመረው ውይይት በተሰብሳቢዎች በሚነሱ ጥያቄዎችና አስተያየት ቀጥሎ ለሻይ ዕረፍት ስብሰባው ተቋረጠ። ሁላችንም ሻይ እና ቡና ወደተዘጋጀበት ቦታ አመራን፤ ዶ/ር ዐቢይ ለሻይ በወጣንበት ወቅት የቱ ጋር እንዳሉ እኔ ልብ አላልኩም፤ ይልቁንም ለየኔታ ትኩስ ነገር ምን ላምጣሎት ብዬ ስጠይቃቸው፤ “አንድ ሲኒ ቡና ትንሽ ስኳር ጨምረ አመጣልኝ፣ ከዚያ … [Read more...] about የኔታ እና ዶ/ር ዐቢይ፤ የኔታ ምን አሉ?!