• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የኔታ መስፍን ወልደ ማርያም የዘመን ዕንቁ! የትውልድ ዋርካ!

September 30, 2020 02:13 am by Editor Leave a Comment

መስከረም 20፤ 2013 ዓም የትውልድ ዋርካ፤ የዘመናት ዕንቁ የሆኑትን የኔታ መስፍን ወልደ ማርያም ማረፋቸው ተሰምቷል። ስለ እርሳቸው ብዙ ማለት ይቻላል። ሞት ለማንም የማይቀር ቢሆንም ስለ እርሳቸው ዕረፍት እኛ ከምንናገረው በላይ ራሳቸው ስለ ሞት የተናገሩትን አትመነዋል። ከሁሉ በላይ “ዛሬም እንደ ትናንት” የተሰኘውን የመጨረሻ መጽሐፋቸውን ከሁለት ሳምንታት በፊት አሳትመው ማረፋቸው ለአገራቸው እስከመጨረሻው የተጉ የዘመናችን ዕንቁ! የኔታ መስፍን! የቅኔ ጌታ! የዕውቀት ገበታ! ቢባልላቸው በፍጹም የሚያንስባቸው አይደለም።  

የዛሬ ሦስት ዓመት ተኩል አካባቢ ጥር/2009 ስለራሳቸው ህይወትና ጻዕረሞት የጻፉትን በድጋሚ በማተም የስንብት ሐዘናችንን እንገልጻለን።

ለቤተሰብ፣ ለዘመድ፣ ለወዳጅ፣ ለመላው የአገራችን ሕዝብ መጽናናትን እንመኛለን።

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

ጻዕረ ሞትና መስፍን ወልደ ማርያም

አንደኛ፣ ገና በልጅነቴ አሥር ዓመት ግድም ሲሆነኝ አንድ በድቀድቂት ከእንጦጦ ወደታች የሚወርድ ኢጣልያዊና እኔ ተጋጠምን፤ እሱ በዚያ በጥቁር ድንጋይ ኮረት በረበረበበት መንገድ ላይ ሲጓዝ ወደ እንጦጦ የሚወጣ ወታደሮችን የጫነ ከባድ መኪና ቆሞ ነበር፤ በዚያ መኪና ላይ አንድ ዝንጀሮ ነበር፤ የኔ አትኩሮት በዚህ ዝንጀሮ ላይ ነበር! እንደሚመስለኝ ዝንጀሮውን እያየሁ ስሮጥ ከድቅድቂቱ ጋር ተገናኘን፤ እኔ ከስር በተረበረበው የጥቁር ድንጋይ ኮረት ላይ፣ ድቅድቂቱ ደግሞ የእኔን ራስ ጨፍልቆ! ምኒልክ ሀኪም ቤት ከስንት ቀኖች በኋላ የካቶሊክ መነኮሳት አስታማሚዎች ከነመለዮአቸው አልጋዬ አጠገብ ቆመው በትልቅ የበሽተኞች ድንኳን ውስጥ በአንዱ መደዳ ውስጥ ተኝቼ ነቃሁ፤ መድኃኔ ዓለም ማንን ልኮ የእኔን ጭንቅላት ከድንጋዩና ከድቅድቂቱ መክቶ እንዳዳነኝ አላውቅም።

ሁለተኛ፣ ከሶደሬ መውጫ ላይ በመቶ ሰባ ኪሜ የሚሽከረከር መኪና ተገልብጦ ከመኪናው በጣራው በርሬ ወጥቼ የጥቁር ድንጋይ ሰፈር በሆነበት አሸዋ ተነጥፎልኝ ሳልፈነከት በጭንቅላቴ አረፍሁና በጸጉሬ አሸዋ አፍሼ ተነሣሁ።

ሦስተኛ፣ በፓሪስ በአንድ ዓለም-አቀፍ ስብስባ ላይ የተጠናወተኝ ሕመም እስከሎንዶን ተከትሎኝ፣ ወደ አዲስ አበባ ለመመለስ አንድ ወዳጄ አውሮጵላን ጣቢያ ወሰደኝ፤ እኔ ከሆቴል ከወጣሁ በኋላ ምንም የማስታውሰው ነገር የለኝም፤ ጻዕረ ሞት እያለሳለሰ ይዞኝ በመሄድ ላይ ነበረ፤ በሦሰተኛው ቀን በሆስፒታል ውስጥ ነቃሁ፤ አሥራ ሦስት ቀን በሀኪም ቤት ስታከም ቀይቼ ወጣሁ።

አራተኛ፣ በቃሊቲ የወያኔ እስረኛ ሆኜ ጻዕረ ሞት ጎበኘኝ፤ ደበበ እሸቱ ደረሰበትና በወያኔ መልካም ፈቃድ በላንድሮቨር ወደ ፖሊስ ሆስፒታል ዶ/ር ሰይፉ ተረከበኝ፤ ለሦስት ቀናት ያህል ራሴን አላውቅም ነበር።

አምስተኛ፣ ተወልጄ ያደግሁበት አዲስ አበባ በድንገት ላንተ አይሆንም የተባለ ይመስል ኦክሲጄን እያነሰብኝ ትንፋሽ ያጥረኝ ጀመረ፤ አዋሳ ሄጄ አንድ ወር ያህል በሰላም ቆየሁ፤ ከዚያ በኋላ አገሩ ሁሉ በፉከራ፣ በጭስና በእሳት ታፈነና በአገሬ መሄጃ አጣሁና ወደህንድ መጣሁ፤ ለአሥር ቀናት ያህል ሰላም አገኘሁ፤ ከዚያ ጻዕረ ሞት ተቆጥቶ መጣ! እጄንና እግሬን ይዞኝ ታገልን! የእውነት ትግል ነበር፤ የሆቴሉን ስልክ አንሥቼ እያቃሳትሁ ወደ ሀኪም ቤት የሚወስደኝን መኪና (አምቡላንስ) እንዲያስመጡልኝ ጮህኩኝ! ኦክሲጅንና ሌላም ነገር እያማጉኝ በዚያ ሰውና መኪና፣ ድቅድቂት እየተጋፋ እየተዳፋ በሚሄድበት መንገድ ለረጅም ጊዜ እየተንገጫገጭሁ ተጓዝሁ፤ ነፍስ ውጪ-ነፍስ-ግቢ ክፍል አስገቡኝ፤ ጻዕረ-ሞት ተናድዶ እየዛተ ጥሎኝ ሄደ።

እሱም አይቀር! እኔም ማምለጫ የለኝ!

ፕ/ር መስፍን ወልደ ማርያም
ጥር/ 2009

(ምንጭ: Mesfin Wolde-Mariam Blog)

Filed Under: Editorial, Right Column Tagged With: mesfin, prof mesfin

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule