Good Morning to everyone here. First of all, I would like to give my deepest sympathy to the family of Professor Mesfin Woldemariam and the great numbers of Ethiopians who consider him a great friend of the Ethiopian people for many generations. I also thank those who have given me the opportunity to speak today about one of greatest men I have been privileged to meet and know. This giant of a man has played an important and strategic role in my life and that of many others. Most people … [Read more...] about “In Honor and Remembrance of the Life of Professor Mesfin Woldemariam” Obang
Obang
“ድንቁርና እና ዘረኝነት ሲደባለቅ እሳት ነው፤ አገር ያፈርሳል”
“ኢትዮጵያ የሚለው መጠሪያ እንዲያስፈራ ተደርጎ ተሰርቷል” በአሁኑ ጊዜ በኢትዮጵያ የሚገኙት የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር አቶ ኦባንግ ሜቶ ሐምሌ 26/2011ዓም ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋዜጠኛ ምህረት ሞገስ ጋር ቃለምልልስ አድርገዋል። “ድንቁርና እና ድህነት እሳት ነው፤ አገር ያቃጥላል” በሚል ርዕስ የወጣውን ቃለምልልስ ከዚህ በታች አስፍረነዋል። በዚህ ጥያቄና መልስ አቶ ኦባንግ ወሳኝ በሆኑ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ መልሶችን ሰጥተዋል፤ ጎሰኝነትን፣ ብሔረተኝነትን፣ ኢትዮጵያዊነት፣ ወዘተ በመሳሰሉ ርዕሶች ላይ ሊነበብ የሚገባው መልሶችንና ዕምነታቸውን ተናግረዋል። አዲስ ዘመን፡– የካናዳ የትምህርት ህይወት እንዴት … [Read more...] about “ድንቁርና እና ዘረኝነት ሲደባለቅ እሳት ነው፤ አገር ያፈርሳል”
አቶ ኦባንግ ለምን በይፋ አምባሳደራችን አይሆንም?
አሁን ኢትዮጵያ ልትጓዝበት እየተጠረገ ያለው መንገድ ከቀደሙት ሁሉ የተለየ ይመስላል። አዲሱ መንገድ ጥላቻን በመስበር የኢትዮጵያን ህዝብ ያለ ልዩነት በፍቅር ተጋምዶ እንዲጓዝበት ታስቦ የሚዘጋጅ ነው። ይህ የሆነበት ዋና ምክንያት የሩቁን ትተን ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት የተኬደበት የጥላቻ፣ የዘረኝነት፣ የቂም፣ የመለያየት፣ የጎጠኝነት ድምሩ አጠቃላይ አገራዊ አደጋ በማስከተሉ ነው። ይህ እውነት ሊካድ በማይችል መልኩ የታየ በመሆኑ አዲሱን ጥርጊያ ማበጀት ብቸኛው አማራጭ ሆኗል። እያደር እየከረረና እየፋመ የመጣው የዘረኛነት በሽታ፣ ስርዓቱ የቆመበትን የጎጥ አስተሳሰብ ለማስጠበቅ የሚከተለው መንገድ የፈጠረው ጥላቻ፣ በስርዓቱ ውስጥ በስልትና በዕቅድ የተፈጠረው ሃብት የማጋበስ በሽታ፣ የፍትህ ዝቅጠት፣ የርትዕ መጓደል፣ የሰው ልጆች መሰረታዊ መብቶች መሞት፣ ድህነት፣ ችጋር፣ ጠኔ፣ ረሃብ፣ … [Read more...] about አቶ ኦባንግ ለምን በይፋ አምባሳደራችን አይሆንም?
“አባ ነቅንቅ” – ኦባንግ ሜቶ ሊሞሸር ነው!!
ከኢትዮጵያውያን ጋር ሁሉ የማይሰበር የጽናት ጋብቻ እንደመሠረተ ያምናል። ከሞት ወዲያ ሳይሆን ለሞት ወዲህ ስላለው ታላቅ አገራዊ ክብር ይጨነቃል። በሁሉም ስፍራ፣ በየትኛውም አጋጣሚ ለሚፈልጉት ሁሉ “አለሁ” የሚል ኢትዮጵያዊ ነው። ዘረኝነትን፥ ዘውገኝነትን፥ ጎሠኝነትን፥ አጥብቆ ይዋጋል፤ ይጸየፋል። ከዘር ቆጠራና ከቂም የጸዳች ኢትዮጵያን ማየት ህልሙ ነው። የመጨረሻው ግብ!! ፍቅርን የሚሰብክ በመሆኑ አፍቃሪዎቹ ከልብ ይወዱታል። ለእሱ ያላቸው ፍቅርም ሲሞቅ በማንኪያ የሚሉት ዓይነት አይደለም። በቅርቡ የመኪና አደጋ ባጋጠመው ወቅት ለአደጋ የዳረገችውን ሴት ከሞት ተርፎ ሲያጽናናት የተመለከተች እናት እንባ እያነቃት አድናቆቷን ችራዋለች። ኦባንግ ሜቶ!! ዛሬ በሁለት አዳዲስ የህይወት ጅማሮ ላይ ነው። “ማኅተቤ” የሚላት አገሩ ተስፋ ሰጪ በሆነ ሽግግር ላይ ናት ብሎ ያምናል። በዚህም … [Read more...] about “አባ ነቅንቅ” – ኦባንግ ሜቶ ሊሞሸር ነው!!
አሁንም ይፈለጋል!
የህወሃት ፍጹም ታማኝ ነበር። በተለያዩ ሃላፊነቶች በህጻናት፣ በወንድሞቹ፣ በእህቶቹ፣ በእናቶቹ፣ በአባቶቹ አጠቃላይ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ በሰራው ወንጀል በህግ ይፈለጋል፣ በህግ የሚፈልጉት ኢትዮጵያዊያን ብቻ ሳይሆኑ ዓለም አቀፍ የፍትህና የመብት ተሟጋቾች ናቸው። ህወሃትን ክዶ በስደት ከሚገኝበት አገር እጁን እንዲሰጥ ጥሪ ቀርቦለታል። ይህ “ሰው” በጋምቤላ ክልል የፖሊስና የጸጥታ ሃላፊ የነበረ። የደህንነት አመራር ነበረ። ክልሉን በፕሬዚዳንትነት ለዓመታት የመራ፣ በጅምላ ለተጨፈጨፉት የአኝዋክ ንጹሃን ደም ቀዳሚ ተጠያቂ ነው – ኦሞት ኦባንግ !! ኦሞት የዛሬ 14ዓመት በዴሰምበር 13/2003 በጅምላ ጄኖሳይድ ለተፈጸመባቸው ከ424 በላይ የአኙዋክ ንጹሃን ዜጎች፣ በአስር ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች ስደት፣ መሬታቸው በግፍ ለተነጠቁና በጠመንጃ ለተፈናቀሉ ዜጎች ግንባር ቀደም ተጠያቂ መሆኑን … [Read more...] about አሁንም ይፈለጋል!
“በፖለቲካ ቂም” የተመሰረተ ክስ ውድቅ ሆነ
በጋምቤላ ሁለት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችና ሁለት ጠበቆች “በፖለቲካ ቂም ውሳኔያችንን አናዛባም” በማለታቸው ከስራና ከሃላፊነታቸው መሰናበታቸው ታወቀ። ሁለት የክልሉ የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃብያነ ህግም በተመሳሳይ ውሳኔ ከሃላፊነታቸው መባረራቸው የተጠቆመ ሲሆን ውሳኔው የክልሉ ፕሬዚዳንት ወንድም የሆኑትን ዓቃቤ ህግ አላካተተም። በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሰረተባቸውን ሶስት የጋምቤላ ክልል ባለሥልጣናት የፍርድ ሂደት ያስቻለው የጠቅላይ ፍርድ ቤት ተከሳሾቹን በነጻ የለቀቀው ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ነው። አስራ አንድ አባላት ያሉት የክልሉ አስተዳደር ስድስት ለአምስት በሆነ ውሳኔ የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ በነበሩት አቶ ጀምስ ዴንግ፣ ምክትላቸው ኮንግ ጋልዎክና የክልሉ የፖሊስ ኮሚሽነር በነበሩት ኦቲየንግ ኦቻን በሙስና እንዲወነጀሉ ውሳኔ አስተላልፎ … [Read more...] about “በፖለቲካ ቂም” የተመሰረተ ክስ ውድቅ ሆነ
ከሲና የተረፉት የሲኦል ነዋሪዎች ጩኸት!!
“ላለፉት ሶስት ዓመታት ማንም ሳያውቀን ታስረናል። አሁን ጉዳያችን ለዓለም መድረሱን ሰማን።የተፈታን መስሎናል” የሚሉት እስራኤል ራምሌ በሚባ እስርቤት ከሶስት ዓመት በላይ ታስረው ያሉት ወገኖች ናቸው። ይህ የሆነው የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር በርዕስ ለእስራኤል ጠ/ሚኒስትር በግልባጭ ደግሞ ከጉዳዩ ጋር አግባብ ላላቸው ለተለያዩ የአገሪቱ ባለስልጣናት፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና የመገናኛዎች አውታሮች ያሰራጩትን ደብዳቤ ተከትሎ በእስር ላይ ያሉት ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ በመንቀሳቀሱ ነው። በእስራኤል የኢትዮጵያን እናድን አንድነት ማኅበር ሊቀመንበር አቶ ሳሙኤል አለባቸው አድማሱ ለጎልጉል እንዳስታወቁት ከእስር ቤት በስልክ ያነጋገሯቸው ወገኖች የደብዳቤውን መልዕክት ሰምተው አስታዋሽ በማግኘታቸው ደስታቸውን ገልጸዋል። አቶ ኦባንግ ሜቶ … [Read more...] about ከሲና የተረፉት የሲኦል ነዋሪዎች ጩኸት!!