“ላለፉት ሶስት ዓመታት ማንም ሳያውቀን ታስረናል። አሁን ጉዳያችን ለዓለም መድረሱን ሰማን።የተፈታን መስሎናል” የሚሉት እስራኤል ራምሌ በሚባ እስርቤት ከሶስት ዓመት በላይ ታስረው ያሉት ወገኖች ናቸው። ይህ የሆነው የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (አኢጋን) ዋና ዳይሬክተር በርዕስ ለእስራኤል ጠ/ሚኒስትር በግልባጭ ደግሞ ከጉዳዩ ጋር አግባብ ላላቸው ለተለያዩ የአገሪቱ ባለስልጣናት፣ ዓለም አቀፍ ድርጅቶች፣ ሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችና የመገናኛዎች አውታሮች ያሰራጩትን ደብዳቤ ተከትሎ በእስር ላይ ያሉት ኢትዮጵያዊያን ጉዳይ በመንቀሳቀሱ ነው። በእስራኤል የኢትዮጵያን እናድን አንድነት ማኅበር ሊቀመንበር አቶ ሳሙኤል አለባቸው አድማሱ ለጎልጉል እንዳስታወቁት ከእስር ቤት በስልክ ያነጋገሯቸው ወገኖች የደብዳቤውን መልዕክት ሰምተው አስታዋሽ በማግኘታቸው ደስታቸውን ገልጸዋል። አቶ ኦባንግ ሜቶ … [Read more...] about ከሲና የተረፉት የሲኦል ነዋሪዎች ጩኸት!!