በጋምቤላ ሁለት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችና ሁለት ጠበቆች “በፖለቲካ ቂም ውሳኔያችንን አናዛባም” በማለታቸው ከስራና ከሃላፊነታቸው መሰናበታቸው ታወቀ። ሁለት የክልሉ የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃብያነ ህግም በተመሳሳይ ውሳኔ ከሃላፊነታቸው መባረራቸው የተጠቆመ ሲሆን ውሳኔው የክልሉ ፕሬዚዳንት ወንድም የሆኑትን ዓቃቤ ህግ አላካተተም። በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሰረተባቸውን ሶስት የጋምቤላ ክልል ባለሥልጣናት የፍርድ ሂደት ያስቻለው የጠቅላይ ፍርድ ቤት ተከሳሾቹን በነጻ የለቀቀው ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ነው። አስራ አንድ አባላት ያሉት የክልሉ አስተዳደር ስድስት ለአምስት በሆነ ውሳኔ የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ በነበሩት አቶ ጀምስ ዴንግ፣ ምክትላቸው ኮንግ ጋልዎክና የክልሉ የፖሊስ ኮሚሽነር በነበሩት ኦቲየንግ ኦቻን በሙስና እንዲወነጀሉ ውሳኔ አስተላልፎ … [Read more...] about “በፖለቲካ ቂም” የተመሰረተ ክስ ውድቅ ሆነ