• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“በፖለቲካ ቂም” የተመሰረተ ክስ ውድቅ ሆነ

October 29, 2012 01:37 pm by Editor 1 Comment

በጋምቤላ ሁለት የጠቅላይ ፍርድ ቤት ዳኞችና ሁለት ጠበቆች “በፖለቲካ ቂም ውሳኔያችንን አናዛባም” በማለታቸው ከስራና ከሃላፊነታቸው መሰናበታቸው ታወቀ። ሁለት የክልሉ የስነ ምግባርና የጸረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃብያነ ህግም በተመሳሳይ ውሳኔ ከሃላፊነታቸው መባረራቸው የተጠቆመ ሲሆን ውሳኔው የክልሉ ፕሬዚዳንት ወንድም የሆኑትን ዓቃቤ ህግ አላካተተም።

በሙስና ወንጀል ተጠርጥረው ክስ የተመሰረተባቸውን ሶስት የጋምቤላ ክልል ባለሥልጣናት የፍርድ ሂደት ያስቻለው የጠቅላይ ፍርድ ቤት ተከሳሾቹን በነጻ የለቀቀው ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ነው። አስራ አንድ አባላት ያሉት የክልሉ አስተዳደር ስድስት ለአምስት በሆነ ውሳኔ የንግድና ኢንዱስትሪ ቢሮ ሃላፊ በነበሩት አቶ ጀምስ ዴንግ፣ ምክትላቸው ኮንግ ጋልዎክና የክልሉ የፖሊስ ኮሚሽነር በነበሩት ኦቲየንግ ኦቻን በሙስና እንዲወነጀሉ ውሳኔ አስተላልፎ እንደነበር በማስታወስ ለጎልጉል መረጃ ያስተላለፉት ክፍሎች እንዳሉት በተጠቀሱት የቢሮ ሃላፊዎች ላይ ክስ የመሰረተው የክልሉ ጸረ ሙስና ኮሚሽን ዓቃቤ ህግ ነበር።

የክልሉ ፕሬዚዳንት ወንድም ኦቦል ኦባንግ የሚገኙበት የኮሚሽኑ አቃቤ ህግ የመሰረተውን ክስ ያስቻለው የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት “ጥፋት አላገኘሁም።የተከሰሱት የንግድ ቢሮ ሃላፊዎችና ፖሊስ ኮሚሽነር የተጨበጠ ማስረጃ አልቀረበባቸውም” በማለት በነጻ እንዲሰናበቱ ወስኗል። የጎልጉል ዘጋቢ በስልክ ያነጋገራቸው የፍርድ ቤት ምንጮች ውሳኔውን ተከትሎ የክልሉ ፕሬዚዳንት አቶ ኦሞት ኦባንግ ውሳኔውን በመቃወም የፍርድ ሂደቱ እንዲቀለበስ ትዕዛዝ አስተላልፈዋል።

“በፖለቲካ ቂም የፍርድ ውሳኔያችንን አንቀይርም” በማለት ኦሞት ኦባንግን የተከራከሩት የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ፕሬዚዳንት አቶ ጆን ዮንግ፣ ምክትላቸው አቶ ዶል ኦኩሪ፣ የጠቅላይ ፍርድ ቤት ጠበቃና የመምሪያ ኃላፊ ኒይንገው ኡጃይና ሌላው ጠበቃ ኦባንግ ኡጁሉ ከሃላፊነታቸውና ከስራቸው መባረራቸው ታውቋል፡፡ ይህ ዜና እስከተጠናከርበት ጊዜ ድረስ የተቀየረ ነገር የለም።

በተመሳሳይ በተካሳሾቹ ላይ ማስረጃ በማሰባሰብ ክስ የመሰረተው የክልሉ የጸረ ሙስና ኮሚሽን አቃብያነ ህግ ኦካች ኦሞድና ኦባንግ አብዱራዛክ “ክሱን በሚገባ አላቀነባበራችሁም” በሚል ከሃላፊነታቸው ተነስተዋል፤ ከስራቸውም ታግደዋል። በተከሳሾቹ ላይ መረጃ በማሰባሰብ ክስ ከመሰረቱት መካከል አንዱ የሆኑት የክልሉ ፕሬዚዳንት ወንድም አቃቤ ህግ ኦቦል ኦባንግ ግን በስራቸውና በሃላፊነታቸው መቀጠላቸው ታውቋል። ጎልጉል ያነጋገራቸው እንዳሉት ውሳኔው በተለያዩ ደረጃ ባሉ የክልሉን የስራ ሃላፊዎችና የአስተዳደሩን ስራ አስፈጻሚዎች መካከል መለያየት ፈጥሯል።

ከዓመታት በፊት ከአራት መቶ በላይ ለሚሆኑ አኙዋኮች መገደልና በሺዎች ለሚቆጠሩት መሰደድ በቀጥታ ተጠያቂ እንደሆኑ ከበርካታ የሰብዓዊ መብት ተቋማት ክስ የሚቀርብባቸውን የክልሉ ፕሬዚዳንት ኦሞት ኦባንግን በሙስናና በመልካም አስተዳደር በጥብቅ በመታገላቸው በፖለቲካ ቂም ሶስቱ የክልሉ ሃላፊዎች ሲታሰሩ የፋይናንስ ቢሮ ሃላፊ የነበሩት አቶ ተስፋዬ ኢሬሳ ከፍተኛ ምስጢር ያላቸውን ሰነዶች በመያዝ ከመታሰራቸው በፊት መሰወራቸውን የሚገልጹት የጎልጉል የመረጃ ምንጮች “የቢሮ ሃላፊው ይዘው የተሰወሩት መረጃ አቶ ኦሞት የፈረሙባቸው ከፍተኛ የገንዘብ ሰነዶችና ሙስና የተከናወነባቸው የኮንስትራክሽንና የተለያዩ መረጃዎች ናቸው። መረጃዎቹ አንድ ቀን ህዝብ ፍርዱን ይሰጥ ዘንድ ይፋ ይሆናሉ” ሲሉ ተናግረዋል።

የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ነጻ የለቀቃቸው ሶስቱ ተከሳሾች ለጊዜው ከእስር ቢለቀቁም ከዛሬ ነገ ተመልሰው ይታሰራሉ የሚል ስጋት እንዳለ ለማወቅ ተችሏል።

ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: News Tagged With: DOL OKURI, Full Width Top, JAMES DENG, JOHN YONG, KONG GALWAK, Middle Column, Obang, obang abdarazak, OKACH OMOD, omot, OTHIENG OCHAN, TESFAE RESO

Reader Interactions

Comments

  1. Moses Anengi Atei says

    October 29, 2012 02:18 pm at 2:18 pm

    any way to work for people, is kindly better to think back under the bed.
    do the best for the sake of people but not for your sake

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “ኤርትራዊ ነን” በማለት የመኖሪያ ፈቃድ ሲቀበሉ የኖሩ የትግራይ ሰዎችን መለየት ተጀመረ April 1, 2021 02:01 am
  • ምርጫ ቦርድ የኦነግን ጥያቄ ውድቅ አደረገ April 1, 2021 01:15 am
  • “እርግጠኛ ሆኜ የምነግራችሁ መንግሥት ኮሮጆ አይሰርቅም” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ April 1, 2021 01:09 am
  • መንግሥት ካልደረሰልን አሁንም ግድያ ይኖራል – ነዋሪዎች April 1, 2021 01:04 am
  • በትግራይ ሊዘረፍ የነበረ የእርዳታ እህል ተያዘ April 1, 2021 12:39 am
  • “በኢትዮጵያ ክብርና ጥቅም ከመጣችሁ አንገቴ ይቀላል እንጂ አልደራደርም” March 24, 2021 01:22 am
  • “ከዚህ በኋላ ህወሓት ማለት በነፋስ የተበተነ ዱቄት ነው” ጠ/ሚ/ር ዐቢይ March 23, 2021 11:28 pm
  • እነ ስብሃት ነጋ ጥያቄያቸው ውድቅ ሆነ March 23, 2021 10:23 pm
  • በርግጥ ኢትዮጵያ ዝናብ አዝንባለች? March 23, 2021 10:15 pm
  • አሜሪካ በሴናተሯ አማካይነት “ለቅሶ” ደረሰች March 21, 2021 08:57 pm
  • ቪኦኤ በወለጋ ሆሮ ጉድሩ ለተጨፈጨፉ ኦነግ ሸኔን ከደሙ ንጹህ አደረገ March 19, 2021 04:32 pm
  • ባልደራስና የአብን የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ March 18, 2021 01:56 pm
  • ኤርሚያስ ለገሰ “የወያኔ የፕሮፖጋንዳ ሰራተኛ እያለ የለመደው የቁጥር ጫወታ አለቀቀውም” March 17, 2021 09:54 pm
  • በትግራይ ሰብዓዊ ድጋፍ በተቀላጠፈ ሁኔታ እየተካሄደ ነው – የተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ፅህፈት ቤት March 17, 2021 04:54 am
  • ምርጫ ቦርድ ከፈቀደለት ኦነግ በምርጫው እንደሚወዳደር አስታወቀ March 17, 2021 04:30 am
  • በዓለምአቀፍ ሚዲያ ዘጋቢዎች ላይ እርምጃ ሊወሰድ ነው March 15, 2021 11:25 am
  • በሲዳማ/ሀዋሳ 128 ቱርክ ሰራሽ ሽጉጥ፤ 2 መትረየስ ከ8,129 ጥይት ጋር ተያዘ March 15, 2021 10:13 am
  • የአክሱም ጅምላ ጭፍጨፋ ተብሎ የተሰራጨው ፎቶ የሐሰት ሆነ March 15, 2021 09:26 am
  • በትግራይ ትምህርት ቤቶች በቅርቡ ሥራ ይጀምራሉ March 15, 2021 09:04 am
  • በማይካድራ የጅምላ መቃብር ተገኘ፤ በህወሓት የተገደሉት ቁጥር ከ1300 እንደሚበልጥ ተነገረ March 15, 2021 08:54 am
  • የጃዋር ቅዠትና የበቀለ የተላላኪነት ፖለቲካ – የለማ ሃዲድ መሳት March 14, 2021 02:53 pm
  • የኬሪያና የጃዋር ድብቁ ግንኙነትና አዲሱ የቤት ውስጥ እስር March 11, 2021 04:27 pm
  • UNDP Memo Echoes Ethiopian Talking Points on Tigray March 10, 2021 10:40 am
  • የልደቱ፤ የትህነግ እና የነጃዋር መጨረሻ March 10, 2021 10:09 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule