አሁን ኢትዮጵያ ልትጓዝበት እየተጠረገ ያለው መንገድ ከቀደሙት ሁሉ የተለየ ይመስላል። አዲሱ መንገድ ጥላቻን በመስበር የኢትዮጵያን ህዝብ ያለ ልዩነት በፍቅር ተጋምዶ እንዲጓዝበት ታስቦ የሚዘጋጅ ነው። ይህ የሆነበት ዋና ምክንያት የሩቁን ትተን ላለፉት ሃያ ሰባት ዓመታት የተኬደበት የጥላቻ፣ የዘረኝነት፣ የቂም፣ የመለያየት፣ የጎጠኝነት ድምሩ አጠቃላይ አገራዊ አደጋ በማስከተሉ ነው። ይህ እውነት ሊካድ በማይችል መልኩ የታየ በመሆኑ አዲሱን ጥርጊያ ማበጀት ብቸኛው አማራጭ ሆኗል። እያደር እየከረረና እየፋመ የመጣው የዘረኛነት በሽታ፣ ስርዓቱ የቆመበትን የጎጥ አስተሳሰብ ለማስጠበቅ የሚከተለው መንገድ የፈጠረው ጥላቻ፣ በስርዓቱ ውስጥ በስልትና በዕቅድ የተፈጠረው ሃብት የማጋበስ በሽታ፣ የፍትህ ዝቅጠት፣ የርትዕ መጓደል፣ የሰው ልጆች መሰረታዊ መብቶች መሞት፣ ድህነት፣ ችጋር፣ ጠኔ፣ ረሃብ፣ … [Read more...] about አቶ ኦባንግ ለምን በይፋ አምባሳደራችን አይሆንም?