ከኢትዮጵያውያን ጋር ሁሉ የማይሰበር የጽናት ጋብቻ እንደመሠረተ ያምናል። ከሞት ወዲያ ሳይሆን ለሞት ወዲህ ስላለው ታላቅ አገራዊ ክብር ይጨነቃል። በሁሉም ስፍራ፣ በየትኛውም አጋጣሚ ለሚፈልጉት ሁሉ “አለሁ” የሚል ኢትዮጵያዊ ነው። ዘረኝነትን፥ ዘውገኝነትን፥ ጎሠኝነትን፥ አጥብቆ ይዋጋል፤ ይጸየፋል። ከዘር ቆጠራና ከቂም የጸዳች ኢትዮጵያን ማየት ህልሙ ነው። የመጨረሻው ግብ!! ፍቅርን የሚሰብክ በመሆኑ አፍቃሪዎቹ ከልብ ይወዱታል። ለእሱ ያላቸው ፍቅርም ሲሞቅ በማንኪያ የሚሉት ዓይነት አይደለም። በቅርቡ የመኪና አደጋ ባጋጠመው ወቅት ለአደጋ የዳረገችውን ሴት ከሞት ተርፎ ሲያጽናናት የተመለከተች እናት እንባ እያነቃት አድናቆቷን ችራዋለች። ኦባንግ ሜቶ!! ዛሬ በሁለት አዳዲስ የህይወት ጅማሮ ላይ ነው። “ማኅተቤ” የሚላት አገሩ ተስፋ ሰጪ በሆነ ሽግግር ላይ ናት ብሎ ያምናል። በዚህም … [Read more...] about “አባ ነቅንቅ” – ኦባንግ ሜቶ ሊሞሸር ነው!!