• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“አባ ነቅንቅ” – ኦባንግ ሜቶ ሊሞሸር ነው!!

June 13, 2018 10:24 pm by Editor 10 Comments

ከኢትዮጵያውያን ጋር ሁሉ የማይሰበር የጽናት ጋብቻ እንደመሠረተ ያምናል። ከሞት ወዲያ ሳይሆን ለሞት ወዲህ ስላለው ታላቅ አገራዊ ክብር ይጨነቃል። በሁሉም ስፍራ፣ በየትኛውም አጋጣሚ ለሚፈልጉት ሁሉ “አለሁ” የሚል ኢትዮጵያዊ ነው። ዘረኝነትን፥ ዘውገኝነትን፥ ጎሠኝነትን፥ አጥብቆ ይዋጋል፤ ይጸየፋል። ከዘር ቆጠራና ከቂም የጸዳች ኢትዮጵያን ማየት ህልሙ ነው። የመጨረሻው ግብ!!

ፍቅርን የሚሰብክ በመሆኑ አፍቃሪዎቹ ከልብ ይወዱታል። ለእሱ ያላቸው ፍቅርም ሲሞቅ በማንኪያ የሚሉት ዓይነት አይደለም። በቅርቡ የመኪና አደጋ ባጋጠመው ወቅት ለአደጋ የዳረገችውን ሴት ከሞት ተርፎ ሲያጽናናት የተመለከተች እናት እንባ እያነቃት አድናቆቷን ችራዋለች። ኦባንግ ሜቶ!!

ዛሬ በሁለት አዳዲስ የህይወት ጅማሮ ላይ ነው። “ማኅተቤ” የሚላት አገሩ ተስፋ ሰጪ በሆነ ሽግግር ላይ ናት ብሎ ያምናል። በዚህም ይደሰታል። የሚቻለውን ሁሉ እሱም ሆነ የሚመራው ድርጅትና አጋሮቹ ከደጋፊዎቻቸው ጋር በመሆን ይህንን የለውጥ ጊዜ በማስዋብ ሥራ ለመሳተፍ ላይ ታች ይላል።

የመኪናው አደጋ

በአብዛኞች ዘንድ “ጥቁሩ ሰው” በግልጽ ተናጋሪነቱ “አባ ነቅንቅ” በሚል ውድ ስም የሚታወቀው ኦባንግ ሜቶ ለሚቀርብለት አድናቆት ምስጋና ቢኖረውም፣ መልሱ ሁሌም አንድ ነው። ሁሌም የሚያስበው አንድ ነገርን ነው። ሁሌም የሚመክረው አንድ ትልቅ ጉዳይን ነው። “እኔ” ይላል ጥቁሩ ሰው “እኔ ስራዬን፤ ድርሻዬ ነው የሠራሁት፣ ሁሉም መሥራት የሚገባውን ድርሻ ይሥራ”።

“ዳግም የመኖር ዕድል ተሰጠኝ፤ ተማርኩበት፤ እናንተም ተማሩበት። ዜናው የእኔ ከአደጋ መትረፍ ሳይሆን በቅጽበት የምትሰናበተውን ህይወታችንን በሚገባ ልንጠቀምበት እንደሚገባ መማሩ ላይ ነው” በማለት አምና በሚያዚያ ወር ከመኪና አደጋ ከተረፈ በኋላ የተናገረው ኦባንግ የመትረፉ ዜና ይፋ ሲሆን የጎረፈለት የደስታ መግለጫ አስደንግጦት እንደነበር በወቅቱ ተናግሯል። በርካቶች አንብተው ደስታቸውን ገልጸውለታል። በሲቃ ድምጽ በመትረፉ የተሰማቸውን ስሜት አካፍለውታል።

“… የተረሳሁ ነበርኩ፤ የደረሰብኝ ግፍ ጠባሳ የሚያልፍ መስሎ አይታየኝም ነበር። ግን ብርሃን ሆነልኝ። በየትኛውም ወቅት ልረሳው የማልችለው ኦባንግ ሜቶ ችግሬን ዝቅ ብሎ አደመጠኝ። ና ባልኩት ቦታ ሁሉ ፈጥኖ እየደረሰ ፍትህ ደጅ እንድቆም ረዳኝ። ስለ እሱ ለመናገር ቃላት የሉኝም። ከሁለት ዓመት በፊት ያለመድሃኒት አልተኛም ነበር። ዛሬ መድሃኒት ከመቃም ተገላግያለሁ። በሴትነቴ የደረሰብኝ በደል ቁስሉ ከህሊናዬ ባይጠፋም ታሪኬ ተቀይሯል” ስትል ልባዊ ምስጋና ያቀረበችለት እህት ልብን በሚሰብር አኳኋን ስትኖር ከጥቁሩ ሰው ኦባንግ ሜቶ በስተቀር ማንም አላሰባትም ነበር።

ኦባንግ በደቡብ ኮሪያ በስቃይ የሚኖሩትን ለመታደግ በሴዑል ከተማ

እንደ አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ በየአገሩ የታሰሩትን ኢትዮጵያውያንን የሚታደግ መሪ ከመምጣቱ በፊት በሜክሲኮ፣ በእስራኤል፣ በአውሮፓ፣ በጃፓን፣ በአሜሪካ … ለተዘጋባቸው ኦባንግ ብርሃን ሆኗል። የተቀረቀረባቸውን በር አስከፍቶ አዲስ ህይወት እንዲጀመሩ አድርጓል። ጥቁሩ ሰው ይህንን ሁሉ ሲያደርግ ሁሌም ከጀርባው ላሉት ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ አመራሮችና የልብ ደጋፊዎች ክብር ይሰጣል።

ከመኪና አደጋው የሞት ሽውታ በኋላ፣ “አዎ” አለ ጥቁሩ ሰው። “አዎ! ሞትን ለቅጽበት አየሁት። እንዳልወሰደኝ ስረዳ ሰዎች በቅጽበት ታሪክ እንደሚሆኑ በመገንዘብ በህይወት ዘመናቸው ደግ ለመስራት ለራሳቸው አለመማላቸው አሰብኩ” በዚሁ ስሜት “እንኳን ነገ፣ በደቂቃዎች ምን እንደምንሆን ማስተማመኛ በሌለበት ሁኔታ ሰዎች ስለበቀልና ሌላውን ስለማጥፋት ስልት እየነደፉ ለመኖር መምረጣቸው አሳዘነኝ” ሲል ተጣራ!! ግን በጸጸት አልነበረም።

“እኔ ጸጸት ብሎ ነገር አላውቅም። የምጸጸትበት ነገርም ስለመፈጸሜ አስቤ አላውቅም። ነገር ግን ለወገኖቼ መሥራት የሚገባኝን እንዳልሰራሁ አስባለሁ። በተለያዩ ምክንያቶች ያሰብኩትን ያህል አልተጓዝኩም። ይህ ከጸጸትም በላይ ነው። ምክንያቱም ዘረኝነትን ረግጠንና ቀብረን መጓዝ አለመቻላችን መድሃኒት የሌለው የቅዠት ተስቦ በሽተኛ አድርጎናል” ሲል። በውል የማይታወቅ ዘመን ወደኋላ በመሄድ ለአሁኑ ትውልድና ለአገራችን በማይጠቅም ጉዳይ ላይ ጉልበት፣ ሃብትና ጊዜ እየባከነ መሆኑንን፣ “ከዚህ አዙሪት ሳንወጣ ሞት ይወስደናል፥ ለትውልድ የማይድን ቁስል ትተን፥ ትውልዱን መርዝ ወግተን እናልፋለን” ሲል ፍርሃቻውን አመላከተ።

“የማውቃቸውም ሆነ የማላውቃቸው በርካታ ወዳጅ ቤተሰቦች እንዳፈራሁ አውቃለሁ። ይህን ዜና ሲሰሙ እንደሚያዝኑ እረዳለሁ። ከዜናው በላይ ግን ለሚሰሙ ትምህርት እንዲሆን ይህንን መልዕክት ለማስተላለፍ ስል መናገርን መርጫለሁ። ዳግም የመኖር ዕድል ስለተሰጠኝ የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን ስል ከሞት መልስ የተማርኩትን አካፍያለሁ። ለሚሰማ ትልቅ ጉዳይ ነው” በማለት ሞትን ከተራመደ በኋላ የተናገረው አባ ነቅንቅ፣ ዛሬ አዲስ ቀን ላይ ነው።

የዛሬ ሠላሳ ዓመት በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከሚያውቃት ወይዘሪት አቻላ ቻም ጋር በትዳር ሊጣመር ቀናት ቀርተዋል። በጁን 16 ሜኖሶታ የሠርግ ዝግጅቱን የሚያደርገው ጥቁሩ ሰው የልጅነት ጓደኛውን በትዳር ይጎዳኛል። አባ ነቅንቅ “ጋብቻዬ ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ነው። ከመላዋ ኢትዮጵያ ጋር ነው” ይላል። ግን የህይወት ትሥሥሩን ከውዱ ጋር ያደርጋል።

በአኙዋክ ንጹሃን ላይ የጅምላ ጭፍጨፋ ከተካሄደ በኋላ ራዕዩን አስፍቶ “ሁላችንም ነጻ ካልወጣን ማንም ብቻውን ነጻ መሆን አይችልም” በሚለው መርህ ለኢትዮጵያውያን ሁሉ የቃል ኪዳን ቀለበት ያሰረው ጥቁሩ ሰው ይሞሸራል።

በጣም ጥቂት ቃላትን የምትናገረውና ከፖለቲካ በርቀት የምትገኘውን ሙሽሪት አቻላን በስልክ የማነጋገር ዕድል ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ አግኝቶ ነበር። “ከኢትዮጵያ ሕዝብ ጋር ተጋብቻለሁ ለሚለው ባለቤትሽ ምን ትያለሽ? የጋብቻ ያህል ግንኙነት የመሠረተን ሰው አግብቶ መኖር አይከብድም ትያለሽ?” ለሚለው ጥያቄ እሷም ክብደቱን አልካደችም፤ “በርግጥ ነው ይከብዳል፤ እኔ ደግሞ በብዛት የምታወቅ ሰው አይደለሁም፤ እንዲያውም የእርሱ ተቃራኒ ነኝ፤ ነገር ግን የልጅነት ወዳጄን ከልቤ ስለምወደው ለእርሱ ራሴን አሳልፌ ሰጥቻለሁ፤ ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ሁሉ እወድለታለሁ፤ ከጎኑ ሆኜ የስኬቱ ምክንያት መሆን እፈልጋለሁ፤ አዳምጠዋለሁ፤ አግዘዋለሁ፤ ከእርሱ መማር የሚገባኝን እማራለሁ፤ እኔም በቤተክርስቲያን አካባቢ በርካታ ኃላፊነቶችን በመውሰድ የሠራኋቸው ስላሉ ያንን እና ያለኝን ሁሉ ለእርሱና ለቤተሰቤ አውለዋለሁ፤ ከአንድ ስኬታማ ወንድ ጀርባ ያለችውን ጠንካራ ሴት እሆንለታለሁ” ብላለች።

“ኦባንግ ለአንቺ ምንድነው? ወይም በምን መልኩ ትገልጪዋለሽ?” ለሚለው ጥያቄ አቻላ በሳቅና ፈገግታ በታጀበ ምላሽ “የምወደው ባሌ፣ የትምህርት ቤት ጓደኛዬ፣ የልቤ ወዳጄ፣ የምርጦች ሁሉ ምርጥ ወንድሜ፣ ሁሉ ነገሬ ነው” በማለት ምላሽ ሰጥታለች።

በቅርብም ይሁን በሩቅ ላሉ አፍቃሪዎቹ፣ ወዳጆቹ፣ አክባሪዎቹና አድናቂዎቹን ሁሉ በአንድ ታዛ ስር ሰብስቦ የደስታው ቀን ተካፋይ ማድረግ ባለመቻሉ ኦባንግ ይቅርታ ጠይቋል። መሞሸሩን ሰምተው ከጎኑ ለሆኑት ሁሉ ምስጋናውን አቅርቧል። ወደፊትም ደስታቸውን ለሚገልጹለት ኢትዮጵያውያን ቤተሰቦቹ ሁሉ ምስጋናው ወደር እንደሌለው ተናግሯል።

ከዚህ ሌላ በሜኖሶታ አካባቢ የሚገኙ የኦባንግ ወዳጆች በጥንዶቹ ስም የከፈቱት የፔይፓል ሒሳብ ቁጥር አለ፤ እነዚሁ አስተባባሪዎች ለጎልጉል በላኩት መልዕከት መሠረት “የፍቅር ድጋፋችሁን ለአዲሶቹ ተጋቢዎች ለመግለጽና ይህንንም ለማድረስ ለምትፈልጉ ሁሉ በሚከተለው የPayPal ሒሳብ በቀጥታ ማስተላለፍ ትችላላችሁ፤ ስጦታችሁ በቀጥታ ለአቶ ኦባንግ እና ለወ/ት አቻላ ነው የሚደርሰው” በማለት የአስተባባሪዎቹ ኃላፊ ብርሃን ፀሐይ (Email: berhan.tsehai@gmail.com) አስታውቀዋል።

https://www.paypal.com/pools/c/84IwJV3n76

መልካም የትዳር ዘመን!

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Social Tagged With: #ObangAchala, achala, Full Width Top, Middle Column, Obang

Reader Interactions

Comments

  1. sergute selassie says

    June 14, 2018 04:56 pm at 4:56 pm

    እልልልልልልልልልልልልልል
    ተመስገንንንንንንንንንንንንንን
    እሰይ አሰይ እሰይ አስይ
    ይሁንልንንንንንንንንንንን
    ይደረግልንንንንንነንን
    ዶር ኦባንግ ኢትዮጵያ ሜቶ ሊሞሸር ቸር ወሬ ያሰማልኝ። እንዴት ደስ የሚል ዜና ነው። እልልልልልልልልልል
    የእኛ ሰው ፈጣሪ አምላክ የተሳካ የሐሤት ዘመን ይሁንልህ ኑርልንንንን ብቻ ሳይሆን ኑሩልንንንንንንንን

    Reply
    • Muba says

      June 19, 2018 02:00 pm at 2:00 pm

      Anchi Ashqabac mashofish #surgute

      Reply
  2. Ali guangul says

    June 14, 2018 07:55 pm at 7:55 pm

    Wish you happy & prosperous marriage! Praising & acknowledging good doers would help create many other good doers! Great job goolgul!

    Reply
  3. Alem says

    June 15, 2018 12:56 am at 12:56 am

    Brother Obang Metho,
    You don’t know what an inspiration you are to us. You have kept our feet to the fire through your untiring advocacy. May the Lord bless you and Ms. Cham as you begin your life together.

    Reply
  4. Tewodaj says

    June 15, 2018 06:29 am at 6:29 am

    እንኩን ደስ አለህ ኦባንግ አባ ነቅንቅ ???

    Reply
  5. Ezira says

    June 16, 2018 03:09 pm at 3:09 pm

    it is a good news and i wish you a happy and prosperous marriage Obang Metho ! god bless you

    Reply
  6. Mesfin says

    June 26, 2018 11:19 am at 11:19 am

    Dear Obang Metho , our next “Abiy” !!!!

    Congratulations on your wedding and may our Lord, the kind , bless your marriage in abundance.

    BETAM,BETAM INWEDIHALEN !!
    YETEBAREKENA YETEKEDESE TIDAR YIHUN !!!
    Mesfin G.
    from Addis Ababa.

    Reply
  7. daniel says

    July 4, 2018 11:35 pm at 11:35 pm

    ኦባንግ, የምትናገራቸው ቃላቶች ጥሩና አስተማሪም ናቸው አምላክ ከሞት እንዳተረፈህ ሁሉ አሁንም እረዥም እድሜ ይስጥህ መልካም ጋብቻ ይሁንላቹ፡

    Reply
  8. daniel says

    July 4, 2018 11:46 pm at 11:46 pm

    መላካም ጋብቻ

    Reply
  9. daniel says

    July 4, 2018 11:47 pm at 11:47 pm

    መልካም ጋብቻ

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am
  • በአዲስ አበባ 1 ሺህ 98 የብሬን እና 2 ሺህ 162 የክላሽ ጥይት ተያዘ May 16, 2022 10:10 am
  • በአዲስ አበባ ከተማ በግለሰብ መኖሪያ ቤት ከ5 ሺህ በላይ የአሜሪካ ዶላርና የተለያዩ አገራት ገንዘቦች ተያዙ May 16, 2022 09:53 am
  • አገር አፍራሹ ትህነግ ለቀለብ፣ መድኃኒትና ሥራ ማስኬጃ 76 ቢሊዮን ብር ቀርጥፏል May 16, 2022 08:30 am
  • እየተባባሰ ከመጣው የማህበራዊ ሚዲያ አጭበርባሪዎች ዜጎች ራሳቸውን እንዲጠብቁ ተጠየቀ May 15, 2022 09:38 am
  • የትህነግና ሸኔ መሠልጠኛ የምትባለው ዩጋንዳ መከላከያ ሚ/ር ከኤታማዦር ሹሙ ጋር ተወያዩ May 13, 2022 09:55 am
  • በትግራይ የውጊያ ምልመላው ጉዳይ May 11, 2022 02:37 am
  • መከላከያ በተጨማሪ ድሮን፣ በሥልጠና፣ በዝግጅት ራሱን አብቅቷል May 11, 2022 01:35 am
  • ትህነግ ለሌላ ውጊያ እየተዘጋጀ ነው ተባለ May 10, 2022 01:04 pm
  • ኤርትራ 8 ሩስያ ሠራሽ ድሮኖችን ተረክባለች May 10, 2022 12:37 am
  • ሙስሊምና ክርስቲያን በአንድነት የሚያከብረው የአኾላሌ ባሕላዊ ጭፈራ May 9, 2022 01:46 pm
  • በወልዲያ ፋኖዎች ተመረቁ May 9, 2022 12:51 pm
  • “ሠራዊታችን ድልን በአስተማማኝ መልኩ ማምጣት በሚችል ቁመና ላይ” ጀኔራል ጌታቸው May 9, 2022 11:57 am
  • ዋጋው 64 ሚሊዮን ብር የሚሆን (16 ኪሎ) ሕገወጥ ወርቅ ተያዘ May 9, 2022 11:51 am
  • አብን ክርስቲያን ታደለን ለመጨረሻ ጊዜ አስጠነቀቀ፤ 10 አባላቱን አገደ May 9, 2022 08:58 am
  • ራሱ አቡክቶ፣ ራሱ አሟሽሾ፣ ራሱ ጋግሮ በሰዓት 460 እንጀራ የሚያወጣ ፈጠራ May 9, 2022 08:17 am
  • በህገ ወጥ መንገድ 19 ህጻናትን ሲያዘዋወሩ የነበሩ 6 ሴቶች ተያዙ May 8, 2022 12:39 am
  • በአርሲ ሙስሊሞች ለቤ/ክ ማሠሪያ 3 ሚሊዮን ብርና 20 የቀንድ ከብት ሰጡ May 6, 2022 09:35 am
  • በአዲስ አበባ የሚኖረው የትህነግ ደጋፊ ማንነት በማስረጃ May 4, 2022 11:04 pm
  • ሙስሊም ወንድማማች የቤ/ክ ዘራፊዎችን በቁጥጥር ሥር አዋሉ May 4, 2022 09:04 am
  • ከ6 ሺህ የዓሳ ጫጩት ወደ 80 ሺህ May 4, 2022 08:57 am
  • ተስፋቢሱ ቴድሮስ May 3, 2022 12:16 pm
  • ከሽፏል! April 6, 2022 11:58 am
  • “ሩሲያ ዩክሬይንን ወረረች” እየተባለ ስለሚነዛው ወሬ ጥቂት እውነታዎች March 8, 2022 11:30 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule