• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ኦባንግ ሜቶ ከከፋ አደጋ ተረፉ!

April 29, 2017 04:52 am by Editor 9 Comments

  • “ዳግም የመኖር እድል ተሰጠኝ፤ ተማርኩበት፤ እናንተም ተማሩ”

“ጥቁሩ ሰው” ኦባንግ ሜቶ በሁሉም ስፍራ፣ በየትኛውም አጋጣሚ ለሚፈልጋቸው ሁሉ “አለሁ” የሚሉ ኢትዮጵያዊ ናቸው። ዘረኝነትን፥ ዘውገኝነትን፥ ጎሠኝነትን አጥብቀው ይዋጋሉ። ይጸየፉታል። ከዘር ቆጠራና ከቂም የጸዳች ኢትዮጵያን ማየት ህልማቸውና የመጨረሻ ግባቸው ነው።

ሰብዓዊነት ለአፍታም ከአንደበታቸው የማይለይ፣ በሚያውቋቸው ሰዎች ሁሉ የሚወደዱ፣ ግልጽ ተናጋሪነታቸው ልዩ የሚያደርጋቸው ኦባንግ በዚሁ ባህሪያቸው “አባ ነቅንቅ” የሚል ስም ተሰጥቷቸዋል። በስደት ለሚሰቃዩ የኢትዮጵያ ልጆች /እሳቸው ቤተሰቦቼ የሚሏቸው/ በጠሯቸው ቦታና ሁሉ በመገኘት ለሚያሳዩት ትጋት አቻ የላቸውም። ኢትዮጵያን በመወከል በከፍተኛ ቦታዎች የሚሟገቱ፣ ያዘነውን የሚጎበኙ፣ ለሴት እህቶቻችን ቀድመው የሚደርሱ እኚህ ውድ ሰው በድንገተኛ የመኪና አደጋ ተዓምር ሊባል በሚችል አጋጣሚ ከሞት የመትረፋቸው ዜና ስንሰማ ደንገጠናል። እርሳቸው ብቻ ሳይሆኑ አብሯቸው የነበረ ባልደረባቸውም ከዚህ ዘግናኝ አደጋ አምልጧል።

ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ሚያዚያ 14 2009ዓም /22.04.2017 ከዋሽንግተን ዲሲ ወጣ ብሎ የደረሰባቸውን የመኪና አደጋ አስመልክቶ “ዳግም የመኖር ዕድል ተሰጠኝ፤ ተማርኩበት፤ እናንተም ተማሩበት። ዜናው የእኔ ከአደጋ መትረፍ ሳይሆን በቅጽበት የምትሰናበተውን ህይወታችንን በሚገባ ልንጠቀምበት እንደሚገባ መማሩ ላይ ነው” ሲሉ ነበር የገለጹት።

“አዎ” አሉ ጥቁሩ ሰው። “አዎ! ሞትን ለቅጽበት አየሁት። እንዳልወሰደኝ ስረዳ ሰዎች በቅጽበት ታሪክ እንደሚሆኑ በመረዳት በህይወት ዘመናቸው ደግ ለመስራት ለራሳቸው አለመማላቸው አሰብኩ” ሲሉ መልዕክታቸውን የጀመሩት ኦባንግ “እንኳን ነገ፣ በደቂቃዎች ምን እንደምንሆን ማስተማመኛ በሌለበት ሁኔታ ሰዎች ስለበቀልና ሌላውን ስለማጥፋት ስልት እየነደፉ ለመኖር መምረጣቸው አሳዘነኝ”።

ይህንን ሲናገሩ “የሚጸጽተዎ ነገር አለ እንዴ?” የሚል ጥያቄ ሰንዝረን ነበር። ኦባንግ ግን መልሳቸው ሌላ ነው። “እኔ ጸጸት ብሎ ነገር አላውቅም። የምጸጸትበት ነገርም ስለመፈጸሜ አስቤ አላውቅም። ነገር ግን ለወገኖቼ መሥራት የሚገባኝን እንዳልሰራሁ አስባለሁ። በተለያዩ ምክንያቶች ያስብኩትን ያህል አልተጓዝኩም። ይህ ከጸጸትም በላይ ነው። ምክንያቱም ዘረኝነትን ረግጠንና ቀብረን መጓዝ አለመቻላችን መድሃኒት የሌለው የቅዠት ተስቦ በሽተኛ አድርጎናል” ብለዋል። በውል የማይታወቅ ዘመን ወደኋላ በመሄድ ለአሁኑ ትውልድና ለአገራችን በማይጠቅም ጉዳይ ላይ ጉልበት፣ ሃብትና ጊዜ እየባከነ መሆኑንን የጠቆሙት ጥቁሩ ሰው “ከዚህ አዙሪት ሳንወጣ ሞት ይወስደናል፥ ለትውልድ የማይድን ቁስል ትተን፥ ትውልዱን መርዝ ወግተን እናልፋለን” ይላሉ።

ተፈጥሮ በጥድፊያ ወደ ሞት እየገፋችን ባለበት ሰዓት ሰው ሌላውን ስለመበቀልና ስለማጥፋት ዕቅድ ይዞ መስራቱ ከምንም ነገር በላይ ልብ የሚሰብር እንደሆነ ኦባንግ በሃዘኔታ ነው የገለጹት። “የማውቃቸውም ሆነ የማላውቃቸው በርካታ ወዳጅ ቤተሰቦች እንዳፈራሁ አውቃለሁ። ይህን ዜና ሲሰሙ እንደሚያዝኑ እረዳለሁ። ከዜናው በላይ ግን ለሚሰሙ ትምህርት እንዲሆን ይህንን መልዕክት ለማስተላለፍ ስል መናገርን መርጫለሁ። ዳግም የመኖር ዕድል ስለተሰጠኝ የዕድሉ ተጠቃሚ ለመሆን ስል ከሞት መልስ የተማርኩትን አካፍያለሁ። ለሚሰማ ትልቅ ጉዳይ ነው” ሲሉ ማሳሰቢያ አዘል መልክታቸውን ኦባንግ አስተላልፈዋል።

ከዘርና ከዘረኛነት ቋት ወጥተው “ከጎሳ በፊት ሰብዓዊነት” በሚል አዲሲቷ ኢትዮጵያ ልትተከልበት የሚገባውን መርህ የሚያቀነቅኑት ኦባንግ “መለስ ሲነገረው ቢሰማና ለአንድ ቀን ቀና ሰው ስለመሆን ቢያስብ፣ ብለን ብንመኝ ቢያንስ በቅርቡ ያለቁትን በሺህ የሚቆጠሩ ወገኖቻችንን ነፍስ ማትረፍ፣ እየሰፋ የመጣውን የጎሳ በሽታ መቀነስ በቻልን ነበር። ግን ያሳዝናል በተቃራኒው ነው የሆነው። ያለመውንና ያሰበውን ሳያይ ህይወቱ በጥላቻና በዘረኝነት እንደመረረች ሄደ” ሲሉ የቀናነት እጥረት በሽታ ክፋት ያስረዳሉ።

የኮምፒውተር እቃ ለመግዛት አንድ መደብር ደረሰው ሲመለሱ የ18 ዓመት ወጣት ሴት በፍጥነት እያሽከረከች ሊያመለጡት በማይችሉበት ሁኔታ ተምዘግዝጋ ኦባንግ የሚያሽከረክሩትን መኪና በሳቸው በኩል ጎኑንን መታችው። ወጣቷ በከፍተኛ ፍጥነት ላይ ስለነበረች የኦባንግ መኪና ምቱ እንዳረፈባት ወደ ጎን ተገለበጠች። በመጨረሻም የአውራ ጎዳናው ጠርዝ መኪናዋን ያዛትና በቋፍ ተደግፋ እግሯን ሰቅላ ተገልብጣ ቆመች። የመውጫ በሮቹ በሙሉ ተቀርቅረውና ተጨረማምተው ስለነበር ዕርዳታ ሰጪዎች ባደረጉት ድጋፍ ኦባንግና ባልደረባቸው በኋለኛው በኩል ባለው የእቃ መጫኛ በር ሾልከው እንዲወጡ ተደረገ።

አደጋው ከደረሰ በኋላ አካባቢው ላይ የነበሩ ሰዎች እያነቡ ውስጥ የነበሩት እነ ኦባንግ ሲወጡ ሰላም መሆናቸውን ሲመለከቱ መገረማቸውን መስክረዋል። ፖሊስም ያለ አንዳች ጭረት፣ ደም፣ ስብራት፣ … ኦባንግና ባልደረባቸው መትረፋቸው “ድንቅ” ተብሎ ሊገለጽ እንደሚችል ሁኔታዎች ከተረጋጉ በኋላ ተናግሯል። እንደ ፖሊስ ገለጻ መኪናዋ ከተመታቸበት ቦታ ትንሽ ወደ አሽከርካሪው ተጠግቶ ቢሆን ኖሮ ዛሬ ኦባንግ “ከሞት መልስ ተማርኩ” ለማለት እንደማይበቁ ይሆኑ ነበር። ይህንኑ አስመልክቶ ጥቁሩ ሰው “በፈጣሪ ኃይል ከሞት ተረፍኩ፣ ዳግም የመኖር ዕድል ተሰጠኝ ያልኩት ለዚህ ነው” ብለዋል።

አያይዘውም በቀናነት፣ በታማኝነት፣ በጸዳ ህሊና፣ በሃቅ፣ በመታመን፣ ለአገርና ለህዝብ ከመስራት የበለጠ የሚያኮራ ነገር እንደሌለ ተናገረዋል። በዘርና በጎሳ ተቧድነው፣ ጥላቻን መነሻ መሠረታቸው አድርገው፣ ሌላውን ለማጥፋትና ለመበቀል ዝግጅት እያደረጉ ላሉ፣ ዘመኑ በውል በማይታወቅ ጊዜ ወደኋላ ተመልሰው ቂምን የሚያራግቡና የክፋት ዘርን የሚረጩ ሁሉም ቆም ብለው በማሰብ ራሳቸውን ወደ መግዛት ብልኃትና ጥበብ እንዲመለሱ ጥሪ አስተላልፈዋል።

እሳቸው ከሞት አፋፍ መልስ የተማሩት ይህንን ነውና በግላቸው ከቀድሞው በላይ ራሳቸውን ለህዝብ እንደሚያስረክቡም ቃል ገብተዋል። ዜናውን አስቀድማ የነገረችን ምስክር “ኦባንግን ማጣት እንደ አገር ክስረት ነበር የሚሆነው። ኦባንግ ጀርባቸው የጸዳ፣ ለሚፈለገው ዓይነት ኃላፊነት የሚታመኑ፣ ታላቅ ራዕይ ያላቸው፣ ከነፈሰው ጋር የማይነፍሱ፣ ራሳቸውን ሆነው በነጻነት የሚኖሩ፣ የአንደበት ሳይሆን የተግባር ሰው የሆኑ … ኢትዮጵያዊ” ስትል ገልጻቸዋለች። አያይዛም “ከሚሠሩት ከፍተኛ ሥራ 10 በመቶውን ብቻ አደባባይ የሚያወጡ፣ ጊዜና ትውልድ በሰዓቱ ክብር የሚሰጣቸው ሰው እንደሆኑ አምናለሁ። የተረፉትም ለዚሁ ዓላማ ነው” ስትል ይህንን የተናገረችው የሚሰሩትን ሥራ ሁሉ በቅርብ ጠንቅቃ ስለምታውቅ መሆኑንንም አመልክታለች።

ኢትዮጵያን አስመልክቶ በከፍተኛ ቦታዎች በዝግ ስለሚሠሩት ሥራ ለምን በአደባባይ እንደማይገልጹ በተደጋጋሚ ኦባንግ ተጠይቀው “ገና ምን ሰራን፣ ሥራው ራሱ ሲገልጸው ማየት ይሻላል” የሚል መልስ በዚሁ ገጽ ላይ መመለሳቸው አይዘነጋም።

የመኪናውን አደጋ ያደረሰችው የ18 ዓመት ወጣት ምንም ጉዳት እንዳልደረሰባት ለመረዳት ተችሏል። የመኪና አደጋ ሲደርስ ሰዎች በአብዛኛው እርስበርስ ሲካሰሱና ሲሰዳደቡ በተደጋጋሚ የታየ ቢሆንም በዚህ አደጋ ወቅት ኦባንግ ልጅቷን በማረጋጋትና በማጽናናት የፈጸሙት ተግባር የልጅቷን ቤተሰቦችና ባካባቢው የነበሩትን ሁሉ ያስደመመ እንደነበር በቦታው የነበሩ የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡

የዝግጅት ክፍላችን ለአቶ ኦባንግ፣ ለባልደረባቸውና ለልጅቷ፣ እንዲሁም ለወዳጆቻቸው ሁሉ እንኳን ደስ አላችሁ ይላል።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Mekdes tiruneh says

    April 29, 2017 07:37 am at 7:37 am

    እግዚአብሔር እንኳን አተረፈህ

    Reply
  2. Adam says

    April 29, 2017 02:28 pm at 2:28 pm

    Our GOD is saved his life!! Jesus is Lord

    Reply
  3. Muhiden Ali says

    April 30, 2017 10:17 am at 10:17 am

    ሰሰማ ሰውነኛ በጣም ደነገጥኩ:: ነገ ግን “ትምህት ነው ተማሩብት” ሲል ከኣስራ ሶስት ዓመት በላይ ያለኝን የሱን የመልካም ሰውት ፍቅር በጅጉ ጨመረልኝ ተደሰትኩም: የፈጠረኝ አምላክ አላህን በፅኑ አመሰገኩ:: አይዞህ!!! በመልካም ሰውነትህ አንተ የማታውቀንብዙወገኖቾ እለን:: ለወገኖቾህ የምታስበው እንድሳካ የዘወትር ዱዐዪ ነው::

    ሙህዲን አሊ

    Reply
  4. Lemma says

    April 30, 2017 11:42 pm at 11:42 pm

    Enkuan terefk. Ethiopia anten maTat atichilim. Yandin sew maninetina mininet yebeleTe yeminiredaw
    endih kiw sinil kehone lante yalen kibir ahun kef, yebeleTe kef ale.

    Reply
  5. ehapa4eve says

    May 1, 2017 08:15 pm at 8:15 pm

    Golagul,

    So the second has a proud label ‘golgule dire getse gazeta’ where as the first doesn’t. An editorial lapse or a pattern?

    Reply
    • Editor says

      May 1, 2017 11:32 pm at 11:32 pm

      ehapa4eve

      የመጀመሪያውም ፎቶ ተመሳሳይ ጽሁፍ አለበት። ክስ ከማቅረብና ለማላገጥ ከመቸኮል በጥንቃቄ መመልከቱ ይበጃል። ወይስ ይህ ዓመል ብዙ ዓሥርተ ዓመታትን የተሻገረ ኣባዜ ይሆን?

      የጎልጉል አርታኢ

      Reply
  6. Tese-man says

    May 2, 2017 03:29 pm at 3:29 pm

    God put you somewhere for reasons. GOD won’t lose his allies and servants therefore he always keeping you save. I am not surprised that much that you have been survived or saved from horrified deadly accident. God always there, you are the messenger one of his servants been sent to save Ethiopians and Ethiopia unity with love. Go back read the bible GOD has his ways the way he deals with his own ppls. Glad that you been saved and taught us LOVE & UNITY are mean something rather than hate. YOU ARE THE WITNESS WHAT THE TRUE LOVE MEAN. MAY GOD KEEP YOU SAFE AGAIN AND AGAIN AND AGAIN AND AGAIN. …..

    Reply
  7. Eunetu Yeneger says

    May 2, 2017 04:54 pm at 4:54 pm

    የተከበሩ ወንድሜ ኦባንግ!
    በደማስቆው የግድያ ጎዞው ላይ ለወንጌል ሥራው ጌታ በፍቅሩ የማረከው ሳውል በኋላ ጳውሎስ እኔ ብሄድ ይሻለኝ ነበር፤ መኖሬ ለእናንተ ይጠቅማችኋል ካለው ሕያው ቃል ጋር ሲያዛምዱት በእውነት የእርስዎ መትረፍ ለራስዎ ምን አስተማረዎት?ሰውን ሁሉ ለሚፈውሰው ለእግዚአብሔር መንግሥትስ ምን አዲስ ራእይ ይዘው ተረፉ?የሚያልፈውን በመናቅ ለማያልፈው ሕይወት የቱን ያህል ጨክነው፡ የፈሮን የልጅ ልጅ ላለመባልስ ለክፉው እምቢ ለማለት ወሰኑ???ይህን ሁለተኛ እድል ለበለጠ መልካም ሥራ የሰጠዎት መሃሪ አምላክ ለዘላለም ይመስገን? ለሰው ሁሉ በፍቅር መኖር የሚያስችለውና በክርስቶስ የመስቀል ላይ ሥራ ክርስቲያን የተባልንበትን እውነተኛ ክርስትና ለመኖር ሁላችንን ይርዳን!!! ለችግሮቻችን ሁሉ መፍትሄው ይህ ብቻ ነውና!!!!

    Reply
  8. tesfu says

    May 6, 2017 03:16 am at 3:16 am

    Enkwan Fetari aterefeh….

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule