• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ብሔራዊ መግባባት አጀንዳ ባለቤት አገኘ”

February 24, 2016 12:25 pm by Editor Leave a Comment

በአቶ ኦባንግ ሜቶ የሚመራው ሰሞኑን በአሜሪካን ሲልቨር ስፕሪንግ ከተማ በጠራውና “ለመተማመን እንነጋገር” የሚል መሪ መፈክር በያዘው ስብሰባ ላይ ለመገኘት እድሉ አጋጥሞኝ ነበር፡፡ ስብሰባው የጀመረው ከተባለበት ሰዓት “በባሕላችን መሠረት” አንድ ሰዓት ዘግይቶ ቢሆንም ስብሰባው ላይ የተካሄዱት ቁምነገራም ሀሳቦች የስብሰባውን አርፍዶ መጀመር አላስታወሰኝም።

በስብሰባው ላይ ለመሳተፍ ከአውሮፓ ከአውስትራሊያና ከአሜሪካ የተለያዩ ግዛቶች የመጡ ኢትዮጵያውያን አሁን ሀገራችን የምትገኝበት እጅግ አሳሳቢ ሁኔታ እንቅልፍ ያሳጣቸውና የበኩላችንን ማድረግ አለብን ብለው የቆረጡና ኢትዮጵያ የምንላት ሀገራችንን ከሞላ ጎደል የሚወክሉ ተሳታፊዎች ነበሩ። በርግጥም ኢትዮጵያ ያለችበትን ሁኔታና በውስጧ ያለውን ውስብስብ ችግር ያለምንም አድርባይነትና አስመሳይነት የሚታያቸውን መግለጽ የሚችሉ “ከዘረኝነት ይልቅ ሰውነት ይቅደም” Humanity Before Ethnicity የሚለውን ትልቅ መሪ ቃል በስብዕናቸው ያነገቡ ኢትዮጵያውያኖች ነበሩ።

ለዚህም መገለጫው እያንዳንዱ ተናጋሪ ስሜቱን በእልህ በቁጭት በዕንባ አጅቦ ሲያቀርበው መታየቱና በተለይም የዝግጅቱ አስተባባሪ አቶ አባንግ ሜቶ ዛሬ በሀገራችን በአምባገነኑ መንግስት እየተካሄደ ያለውን የንጹሃን ዜጎች እልቂት እያንዳንዳችን የራሳችን ወንድም እህት አጎት አክስት ቢሆኑ ኖሮ ምን ይሰማን ይሆን ብለው በጥቁር ፊታቸው ላይ ይፈስ የነበረውን እንባ የተመለከተ ታዳሚ፤ እንዲሁም “እናቶች ወንድሞች እህቶች ትውልድን እናድን፤ በሀገራችን ደም መፋሰስ ይብቃ! ብላ በሰሞኑ ግድያ ልጇን እንዳጣች እናት እንባዋን ያጎረፈችውን ወ/ሮ ሰዋሰውን የተመለከተ ወይም ያዳመጠ ሰው የሆነ ሰው በውስጡ ያላለቀሰ ያለ አይመስለኝም።

ስብሰባው የፖለቲከኞች ስብሰባ አልነበረም ወይም “ድርጅቴ ነጻ ያወጣችሁዋል” ብሎ ተስፋ የሚሰጥ ተናጋሪ ያለበት አልነበረም ወይም ሥልጣን ላይ ያለውን መንግስት ጥዬ ዲሞክራሲ በኢትዮጵያ አሰፍናለሁ የሚል አልነበረም። የተለያየ የፖለቲካ አስተሳሰብ ያላቸው ሰዎች ግን ነበሩ። ስብሰባውን ለየት የሚያደርገውም የተለያየ የፖለቲካ አመለካከት ያላቸው ግለሰቦች ለአንዲት ሀገር ኢትዮጵያ ጥቅም ለህዝቦቹ ደህንነት ፍትህና እኩልነት የራሳቸውን አመለካከት ለሀገር ጥቅም አንበርክከው የተገኙበት መድረክ ነበር።

የብዙዎች የተቃዋሚ ፖለቲከኞቻችን ከአምባገነኑ መንግስት ጋር ካላቸው ቂም በተጨማሪ እርስ በርሳቸውም ከሚያናቁራቸውና እልባት ያልተገኘለት መከፋፈል የፖለቲካ ስልጣን ጥያቄና የወቅቱ የፖለቲካ ጦርነት በኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነት ዙሪያ በማንነት ጥያቄዎች ላይ መሆኑን የየተገነዘቡት እነዚህ ተሳታፊዎች ሃሳባቸውን በፍቅርና በመነጋገር በመወያየት ማንነትን ያከበረ ኢትዮጵያችንን በሚገባ ስለዋታል።

ከተናጋሪዎቹ አስተያየቶች ውስጥ ለአብነት ከላስቬጋስ የመጣው አቶ ሮባ “ታሪክን ለባለታሪኮች ለባለሙያውች መተውና ነገር ግን ዛሬም ባለንበት ሁኔታ እኛ የምንሠራው ታሪክ ነገ በትውልድ ተወቃሽ እንደሚያደርገንና አባቴም እናቴም ለኔ ያወረሱኝን የእርስ በርስ ትግልን እኔም ነገ ለልጄ ትግል አውርሼ እንዳላልፍ መሆን አለበት። ነጻነት የሚለውን ቃልና ትርጉም የምናይበት እይታችን መሰፋት አለበት። አንዱን ጥሎ ስልጣን መያዝ አልያም ለብቻ የሚባል ነጻነት የለም” ነበር ያሉት።

የሀረሪ ብሔረሰብ ተወላጅ የሆኑትና በሙያቸው ጠበቃ የሆኑት ዶ/ር አባድር የታሪክ ሰዎች መግባባትን ለመፍጠር መነሻ ናቸው። ምክንያቱም መግባባትን ለመፍጠር ካለፈው መጥፎውን የምንሰማው ለወደፊቱ ትምህርት እንዲሆነን ነው። የእኛ ታሪክ (Culture of Resistance) ነው፤ የአሸናፊ ተሸናፊ ፖለቲካ ነው የፖለቲካ ባህላችን። ይህ ማብቃት አለበት፡ ሁላችንም በአሸናፊነት ልንወጣ የምችልበት መንገድ መኖር አለበት። ችግሩን ለመፍታት መንግስት ወይም የፖለቲካ ድርጅቶችን ብቻ የምንጠብቅ ሳይሆን ሕዝብ ችግሩን እንዲፈታ የህዝብ አጀንዳ ተደርጎ መቅረብ አለበት ብለዋል፡፡

በአቀራረብም ሆነ መድረክ ላይ ሲታይ ለብዙዎች ኢትዮጵያዊያኖች አለባበስ ጭምር ለየት የሚልና አማርኛ ቋንቋን እንደ ሱዳናዊው ሰይድ ከሊፋ “ጤና ይስጥልኝ እንደምናቹ” ብሎ የጀመረው ከአውስትራሊያ የመጣው የቤኒሻንጉሉ ናስር ማንነት በኢትዮጵያዊነት እንዴት ይመዘናል? የሚለውን በራሱ እይታና በሕይወት ታሪኩ ጭምር ያጋጠመውን ገልጾ እስካሁን የተጓዝንበት ኢትዮጲያዊነት መንገድ ሊፈተሸ ይገባል፡ ለኔ ኢትዮጲያ ኩራቴ ነች የበለጠ እንድኮራባት ግን የአስተሳሰብ ለውጥ በሁላችንም እንዲሁም የሥርዓት ለውጥ ያስፈልጋል ብሏል።

በመቀጠልም በወጣትነት እድሜ ውስጥ የምትገኘዋ ሳምራዊት አሁን የያዝኩትን አመለካከት እዚህ ስብሰባ ላይ ከማቅረቤ በፊት ያለሁበት ከተማ ዲሲ በመሆኑና የዲሲንም ፖለቲካ ስለማውቀው ምን ይሉኛል ብዬ ብዙ ተጨንቄአለሁ ነገር ግን ለሃገሬ ከምጨነቀው በላይ አያስጨንቀኝም። ከሁሉ በላይ በተለያየ መልኩ ጭቆናና በደል በኢትዮጵያ ውስጥ እንደነበረና አሁንም እንዳለ መረዳት ወሳኘና የሌሎችን ብሶቶች በማዳመጥ ብቻ ነው ከበሽታችን መፈወስ የምንችለው በሽታችን ላይ መተማመን አለብን ይህ እስካልሆነ ደግሞ መፍትሔ ልናመጣ አንችልም ነበር ያለችው።

ከሜኒሶታ የመጣው ነጌሶ ደግሞ “አብዛኛዎቹ ፖለቲከኞች አብዛኛውን የሚያወሩት ስለራሳቸው ነው ወይም እራሳቸውን ስለማስተዋወቅ ነው። ዛሬ በEthnic empowerment የሀገራችን ፖለቲካ ችግር አይፈታም Civic political transition ያስፈልገናል። አሁን ካለው ሁኔታ አንፃር የሚታገለው እየታገለ ዲሲፒሊንድ በሆነ process ብቻ ነው ለውጥ ማምጣት የምንችለው፤ በሥልጣን ላይ ያለው መንግስት ስልጣኑን ላይ ከማቆየት ማንኛውንም አይነት አደገኛ ካርዶችን ተጠቅሞአል። የኢህአዴግ ስትራቴጂም ከአንዱ ጋር ሀውልት እየሰራ ሌላውን መግደል ነውና ይሄንን መገንዘብ ይኖርብናል” ብለዋል።

አቶ ነጋሲ የትግራይ ተወላጅ በበኩላቸው የቆየ አባባል ቢሆንም የተቃራኒ ባልና ሚስት ወግን በምሳሌነት አስቀምጠው ባጭሩ ሚስትየው ሁልጊዜ ተቃራኒ መልስ ወይም ድርጊት ማድረግ ስለምትወድ አንድ ቀን ወራጅ ጎርፍ ሲወስዳት ለማዳን የተሰበሰበውን ህዝብ ወንዙ ወደሚፈስበት ሳይሆን ሽቅብ ወደላይ ነው የምትሄደው ብሎ ፈላጊዎቹን ወደተቃራኒው አቅጣጫ መራቸው በማለት እልከኝነት ሀገራችንን እያጠፋ ነው በቅርቡም በኦሮሚያ የተካሄደው የመሬት መፈናቀል ጥያቄ በሁሉም ኢትዮጵያ ግዛቶች ውስጥ መሆኑንና በትግራይም ሕዋሓት እግረሃረግ የሚባል አካባቢን ወደ መቀሌ ለማካለል ጥረት ሲያደርግ ሕብረተሰቡ ተቃውሞ በማሰማቱ የእንቅስቃሴው መሪዎች ናቸው የሚባሉ 15 ሰዎች ከ 3 ዓመት እስከ 15 ዓመት ተፈርዶባቸው በእስር ላይ ይገኛሉ። ስለዚህ ትግሉ የጋራ ነው። ከማለት በተጨማሪ TPDM (ደሚት) የሚባለው የታጠቀ ተቃዋሚ ቡድን በአሸባሪነት ሳይፈረጅ በእስክሪፕቶ የሚታገለውን ኦባንግ ሜቶን አሸባሪ ብሎ የፈረጀ ጉደኛ መንግስት ነው ስልጣን ላይ ያለው በማለት ታዳሚውን አስቀውታል።

flyerየትውልድ እልቂት ነው የያዝነው ባለፉት 40 አመት የሃገራችን እናቶች ሰቆቃ ሊያበቃ ይገባል በሰለጠነው አገር የእሳት አደጋና አምቡላንስ የድመትና የውሻን ሕይወት ለማዳን ምን ያህል እንደሚደክሙ እያየን ዛሬ በሀገራችን ዜጎቻችን በጥይት በአውላላ ሜዳ ላይ ተዘርግተው ማየት ለኛ ለእናቶች በተለይም ያለፉት 40 ዓመታት እናቶች የእለት እይታችን ሆኗል። እስከመቼ ነው ይሄ የሚቀጥለው? ስለዚህም ሁላችንም መጮህ አለብን በተለይ የእምነት አባቶች ፖለቲካ ውስጥ አንገባም እያልን አምላካዊ ክቡር ህይወትን ለማዳን እጃችንን አጣጥፈን መቀመጡ እምነታችንን ጥያቄ ውስጥ ይከተዋል በሀገራችን መግባባት እንዲፈጠር ድምጻችንን ማሰማት አለብን በማለት ከኖርዌይ የመጣችው ወ/ሮ ሰዋሰው በጉንጮችዋ ከሚወርደው እንባ ጋር መልዕክቷን አስተላልፋለች።

በመቀጠልም በስብሰባው ላይ ተገኝተው ሀሳባቸውን ያካፈሉት ታዋቂው ምሁርና genocide watch ፕሬዝዳንት የሆኑት ዶ/ር ግሪጎሪ ስታንተን ነበሩ። ዶ/ር ግሪጎሪ በተለያዩ አገራት የዘር ማጥፋትን በሚመለከት ሰፊ ጥናት በማካሄዳቸውም ካነሱዋቸው ምሳሌዎች እንደሩዋንዳ አይነቶችንና በኢትዮጵያ ወስጥም በአኙዋክ ላይ የተፈጠረውን ዳስሰው በአጠቃላይ በኢትዮጵያ የዘር ማጥፋት ወንጀል ወደፊት ሊፈጠር ሚችልበት ሁኔታ አለ ወይ? ለዚህስ ቅድመ ሁኔቶች አሉ ወይ የሚለውን ጥያቄ አንስተው ከዚህ ቀደም በተደረጉ ጥናቶች ቅድመ ሁኔታዎች ናቸው የሚባሉትን 10 ደረጃዎችን አስረድተዋል ከእነዚህ ደረጃዎች አብዛኛዎቹ እየታዩ ናቸው በማለትም ገለጻ ሰጥተዋል። (አንባቢ ይህን ለማወቅ The 8 stage of Genocide የሚለውን በጎግል ማየት ትችላላችሁ።) በመሆኑም ኢትዮጵያዊያኖች ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርጉ ይገባል፤ በስልጣን ላይ ያሉ ግለሰቦችን ወደ እልህ የሚያስገባ ፖለቲካ መጫወት አደጋ እንዳለው በተለይም ሙስናና ዘር ማጥፋት ወንጀል ተመጋጋቢ መሆናቸውን አስረድተዋል።

የስብሰባው መቋጫ የሆነውንና በስፋት ለ3 ቀናቶች በመድረኩ ተሳታፊዎች ቀንና ማታ ተወያይተውበት የደረሱበትን የመፍትሔ ሀሳብ ያቀረቡት ከአትላንታ የመጡት ቄስ ተጋ ነበሩ። እሳቸውም ገና ወያኔ/ኢህአዴግ ስልጣን ሲይዝ ለሀገራችን የመግባባትና የእርቅን አስፈላጊነት ያነሱ ወገኖች እንደነበሩ አስታውሰው አሁንም ሰው ባወቀው መጠን እንደሚቀጣ የእግዚአብሔርም ቃል ይህንኑ እንደሚያስረዳ አመልክተው ይህንን የተገነዘብን ሰዎች በሀገራችን እርቅና ፍትሕ እንዲሰፍን የእርቅና የፍትህ ጉባኤ አቋቁመናል ብለዋል።

የጉባኤው አላማም፤

– ሁሉን የሚያካትት ሁሉ አብሮ የሚጓዝበት

– ከህሊና ክስ ነጻ የሚያወጣ

– በሁሉም ኢትዮጵያዊያን ዘንድ ፍትህ እኩልነት ርትእ የሚያመራ

– የኢትዮጵያ ብሔር ብሄረሰብ የባሕል የቋንቋ ልዩነት ደምቆ የሚወጣበት

– በነጻነትና በሰላም መግባባትን የሚፈጠርበት

– ከሀይማኖችና ማህበራዊ ተቋሞች ጋር ግንኙነት መፍጠርን

– የእርቀ ሂደት እንዲደረግ የሚታገሉ ቡድኖችን ማስተባበርን እንደሚያጠቃልል ገልጸዋል።

በመጨረሻም ስብሰባውን የጠቀለሉት ለአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ (SMNE) መሪ አቶ አባንግ ሜቶ “ጥቁሩ ሰው” በእያንዳንዱ ነጥብ ላይ የተነሱትን ሀሳቦች አሰባስበው እነሆም ሀገራችንን ከክፋ አደጋ ውስጥ ለማዳን የሚያስችል አንድ ወሳኝ እንቅስቃሴ ላይ ደርሰናል፤ ለዚህም ድርጅታችን ከእንግዲህ የብሔራዊ መግባባትንና እርቅን አጀንዳ በባለቤትነት እናንቀሳቅሰዋለን፤ ማንኛውም ለዚህ ዝግጁ የሆነ ኢትዮጵያዊ ቡድን አብሮን ለመስራት በሩ ክፍት ነው ብለዋል።

እውን ኢትዮጵያ አደጋ ውስጥ ናት? የግል ማጠቃለያ ሃሳብ

ከላይ የእያንዳንዱ ተናጋሪ ሀሳብ ቀንጨብ ያደረግኩት ያለምክንያት አይደለም ሁሉም የወቅቱን የሀገራችንን ፖለቲካ ሁኔታ የሚዳስስና በብዙዎችም ቀደም ሲል የተነገረ ቢሆንም ከመናገር አልፎ ወደ ተግባር ሊያመጣ የሚችል ሀሳብን ስላቀፈ ነው ዛሬ ሀገራችን ስለምትገኝበት ሁኔታ ፖለቲከኛው አክቲቪስቱ የሀይማኖች መሪዎች ምሁራን ሁሉም አንዳንድ የሥርዓቱን ሰዎች ጨምሮ የሚሰማቸው ኢትዮጵያ ከምንጊዜውም የበለጠ አደገኛ ሁኔታ ውስጥ መግባቷ ነው።

ከፍተኛ የፖለቲካ የኢኮኖሚ የድህነት የረሀብ ችግር ተደቅኖብናል። የፖለቲካ ስልጣን የሚኖረው ሀገርና ሕዝብ ሲኖር ነው። ከሁሉም በላይ አይጥና ድመት ጨዋታ በፖለቲካ ውስጥ ያለ ቢሆንም ከዘር ፖለቲካ ጋር ከተያያዘ ግን አይጧም ድመቷም አይተርፉም ምክንያቱም የድመት ዘር ያልሆነ ሁሉ አይጥ ሲጠፋ ነግ በኔ ስለሚል ከድመት ጋር መጠፋፋቱን ይቀጥላል። ማብረጃውም ቀላል አይሆንም።

ባለፉት 25 ዓመታት የዘር የፖለቲካ አቀንቃኞች ቁጥር እየቀነሰ የመጣ ቢመስልም አሁን በአዲስ መልክ እያገረሸ ነው። አንዳንድ ወገኖቻችን የብሄር ጥያቄ ነው ለምን የዘር ፖለቲካ ትላላችሁ የሚል አስተያየት ወይም ነቀፌታ ያቀርባሉ ወይም የዘር ፖለቲካ ያለውን ሁሉ የአንድ ዘር ሰው ለማድረግ ይሞክራሉ። እኔ በግሌ አማራ ነኝ ኦሮሞ ነኝ ትግሬ ነኝ ስላለ ወይም ትግሬነቴ አማራነቴ ኦሮሞነቴ ሊታወቅልኝ ይገባል ያጣሁትን ፍትህና እኩልነት ማግኘት አለብኝ ብለው የተነሱ ወንድሞችና ወገኖቼን በዘረኝነት ጭራሽ አላስባቸውም። ያጡትን ነገር እንዲያገኙ እኔም የጎደለኝን አብረውኝ እንዲያሟሉ መታገል ተገቢ ነው ብዬ አምናለሁ ሁላችንም ሳንፈልገው ወይም ሳንታገልበት በተፈጠርንበት ዘር መጠራትን መጥላት የተፈጥሮ ማንነታችንን መጥላት ይሆናል።

ዘረኝነት ከፖለቲካ ስልጣን ጋር የተያያዘና ወይም በራሱ ዘር ላይ ለመንገስ የሚፈልግ ፖለቲካ አቀንቃኝነት ነው። ይህ ደግሞ በይበልጥ በድህነትና በኋላ ቀርነት ላይ ላለ ህብረተሰብ የፖለቲካ መጫወቻ አይነተኛ ካርድ ነው። በሕብረተሰብ እድገት ቤተሰብ ሠፈር መንደር አካባቢ ክልል ሀገር እያደጉ የመጡ ተቋሞች ናቸው። ሰው ለጥቅሙ ሲል አንዳንዶችም በተፈጥሮ አስገዳጅነት ያቋቋማቸው ተቋማት ናቸው።

የዘረኝነት ፖለቲካ አቀንቃኞች ደግሞ በአንድ አካባቢ ወይም ለአንድ ብሔረሰብ የተሰጠ መለያ አይደለም። የቁጥር ማነስ የመደራጀት ወይም ህብረተሰቡን የማንቀሳቀስ ደረጃ ሊለያይ ይችላል። በኢትዮጲያችን የህብረተሰባችን የእድገት ደረጃ የዘረኘነትን ፖለቲካ የመሸከም አቅም በሁሉም ህብረተሰብ ውስጥ አለ። ለዚህም ነው አምባገነኑ መንግሥት ስልጣኑን ለማራዘም ሁሉንም በዚህ ካርድ የሚጫወትበት። የዘረኝነት ፖለቲካ ለኔ የራሱን ዘር ከሌሎች የተሻለ አድርጎ መሳልና በዘሩ ተከልሎ የፖለቲካ ስልጣን ለመያዝ ወይም በራሱ ዘር ላይ ለመንገስ የሚፈልግ ፖለቲካ አቀንቃኝነት ነው።

ስለዚህ ዛሬ በሀገራችን እያቆጠቆጠ ያለውና የሥርዓቱ ዋነኛ ካርድ የሆነውን “ማንነት በዘር” ልናተኩርበት የሚገባን በዚህ አቅጣጫ የሚሄዱትን ተው ማለት አስፈላጊ ይመስለኛል በተለይ አንዱ ወንድማችን በስብሰባው ላይ እንደገለጸው አባቶቻችን ትግል ትተውልናል፡፡

እኛም ለልጆቻችን መታገልን (ፖለቲካዊ ቀውስ) ማስተላለፍ መቆም አለበት ያለው ትክክል ይመስለኛል። በዚህ ረገድ በሀገራችን ውስጥ ያለውን ውጥረተት ለማርገብ በእነ አቶ ኦባንግና በሌሎች ኢትዮጵያዊያን የተጀመረው የብሔራዊ መግባባት አጀንዳ ትልቅ ቦታ ሊሰጠው ይገባል፡፡ ይህን አጀንዳ በሚመለከት ወገኖች የሚያቀርቧቸው በርከት ያሉ አስተያየቶች ጥያቄዎች ተቃውሞዎች ድጋፎች አሉ። የሚያሳዝነው ግን ሁላችንም በዚህ ጉዳይ የአቶ መለስ ራዕይ አንጋቢዎች ሆነን መቆየታችን ነው። “ማንና ማን ተጣሉ ማንና ማን ነው የሚታረቀው?” … በሌላ በኩል ደግሞ “ወያኔ/ኢህአዴግ እሺ አይልም” ወዘተ … እስከሚገባኝ ሁሉም የፖለቲካ ድርጅቶች ብሔራዊ መግባባት ወይም ብሔራዊ እርቅ መደረግ እንዳለበት በትጥቅ ትግል የተሳተፉትም ሳይቀሩ የሚያነሱት ጉዳይ ቢሆንም አንዳቸውም ወደ ተግባር የሚያመራ እንቅስቃሴ አላደረጉም።

እስከማውቀው ድረስም በስልጣን ላይ ያለው የኢህአዴግ መንግስትም የሚያወራውና የሚሰራው የተለያየ ቢሆንም በሚቀጥሉት አምስት አመት ከሚያከናውናቸው ተግባራት አንዱ ብሔራዊ መግባባትና ዲሞክራሲን በሚመለከት የሚያተኩር በአባዱላ ገመዳ የሚመራ አንድ ኮሚቴ መቋቋሙን ከዚህ ቀደም ከሪፖርተር አንብብያለሁ። ይህ አጀንዳ አሁን ሃገራችን ለገባችበት ቀውስ ሊያወጣት የሚችልና የፖለቲካ ድርጅቶች አሽናፊነትና ተሽናፊነት ፖለቲካ ሳይሆን ህዝብ በአሸናፊነት ሊወጣ የሚያስችል አይነተኛ መንገድ ቢሆንም ባለቤት ያጣ አጀንዳ በመሆኑ ብዙዎቻችን ባለቤት እዲያገኝ የጮህንለት ጉዳይ ነው። አሁን በእነ አቶ ኦባንግ የአጀንዳው ባለቤትነት ጥያቄ በመመለሱ መልካም ጅምርና ብዙዎች ኢትዮጵያውያን ሊያሰባስብ የሚችል በመሆኑ በርቱ ግፉበት እንላለን። ፖለቲከኞቻችንም ለዚህ አጀንዳ አብሮ መስራት ሌላው የመፈተኛ ጥያቄም መሆኑን ሊያምኑ ይገባል። የፖለቲካ ስልጣን ጥያቄን መመለስ የሚቻለው የተግባባ ማህበረሰብ ሲኖረን ነው። ልዩነቶቻችንን በመነጋገርና በመወያየት መፍታት ስንችል ብቻ ነው። አምባገነንነትና የዘር ፖለቲካ የወያኔ/ኢህአዴግ ብቻ መለያ አይሆንም። ያንን ፖለቲካ የሚሽከም የህብረተሰብ ክፍል ያቀፈው ሁሉ በውስጡ የተደበቀውን በሽታ ጠመንጃ ሲይዝ ያወጣዋልና። ለብሄራዊ መግባባት የምትጮሁ ወገኖች አንገታችሁን ቀና አድርጉ። ወቅቱ የግድ ይላል።

ጊሼይ ጊሻ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule