• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“በሴትነቴ የደረሰብኝ በደል ቁስሉ ከኅሊናዬ ባይጠፋም ታሪኬ ተቀይሯል”

May 2, 2016 09:52 am by Editor 4 Comments

* “… እህታችን ታሪኳን ስትነግረኝ፣ ለፍትህ እንደምትመጥን አመንኩ” ኦባንግ

“… የተረሳሁ ነበርኩ፡፡ የደረሰብኝ ግፍ ጠባሳ የሚያልፍ መስሎ አይታየኝም ነበር። ግን ብርሃን ሆነልኝ። በየትኛውም ወቅት ልረሳው የማልችለው ኦባንግ ሜቶ ችግሬን ዝቅ ብሎ አደመጠኝ። ና ባልኩት ቦታ ሁሉ ፈጥኖ እየደረሰ ፍትህ ደጅ እንድቆም ረዳኝ። ስለ እሱ ለመናገር ቃላቶች የሉኝም። ከሁለት ዓመት በፊት ያለመድሃኒት አልተኛም ነበር። ዛሬ መድሃኒት ከመቃም ተገላግያለሁ። በሴትነቴ የደረሰብኝ በደል ቁስሉ ከህሊናዬ ባይጠፋም ታሪኬ ተቀይሯል። … በየቦታው ፍትህ የተዛባባችሁ ወገኖቼ ዝም አትበሉ። ፍትህ በደጃችሁ ነው። ግን ተናገሩ። ሆን ብላችሁ ያላጠፋችሁት ጥፋት አያሳፍራችሁምና ራሳችሁን ከዝምታ ድባብ አላቅቁ…” ይህ ስሟ እንዳይነገር ከጠቀችው እህት አንደበት ነው።

“… እኔ የሰራሁት ሥራዬን ነው። ነገም የማከናውነው ሥራዬን ነው። ሙገሳና ጭብጨባ ብዙም አልሻም። ካለብን ችግር ብዛት የሰራነው ሥራ እዚህ ግባ የሚባል አይደለምና ይህንን ሰራሁ የማለት ልዩ ኩራት አይሰማኝም። ይልቁኑም ብዙ ጉድለቶች አሉብን። ፍትህ እንዲዛባብን ራሳችን በራሳችን የምንፈቅድበት አጋጣሚ እጅግ የበዛ መሆኑ ሁሌም ያሳዝነኛል። ለፍትህና ራስን ስለማክበር ያለን ጎዶሎ ነገር ራሱን የቻለ ትግል የሚጠይቅ ነው። ራሳቸውን ገልጠው የሚመጡ ወገኖችን መርዳት እርካታ እንዳለው እረዳለሁ…” አቶ ኦባንግ ሜቶ በበኩላቸው ይህን ይላሉ።

ይህች እህታችን የራሷንና የቤተሰቦችዋን ኑሮ ለማሻሻል የመን በሚገኘው የአሜሪካ ኤምባሲ ሠራተኛ ቤት ውስጥ ለመስራት ተስማምታ ወደዛው ታቀናለች። ምስሏ በፎቶው የሚታየው አሜሪካዊት ዲፕሎማት ባለቤቷ woman የአውስትራሊያ ዜግነት ያለው ሲሆን እርሱ የኤምባሲው ተቀጣሪ አልነበረም፡፡ ነገርግን በዚሁ ቤት ተቀጥራ ደመወዝና የሳምንት ፈቃድ እንዲሁም ሌሎች የሠራተኛ ጥቅማጥሞች እንደሚከበሩላት ቃል ተገብቶላት የመጣችውን እህት ፈጽሞ ያላሰበችውንና ያልጠበቀችውን ጸያፍ ጥያቄ ያቀርብላት ጀመር። ከዚህ በፊት በነበሩ ላይ ተመሳሳይ ጥያቄ እያቀረበ ፍላጎቱን እንደሚፈጽሙና እርሷም ይህንን የማድረግ ግዴታ እንዳለባት ያሳስብ ጀመረ፡፡ ባለቤቱና ቀጣሪዋ ዲፕሎማትም የባሏን ፍላጎት እንድትፈጽም ከመለመን እስከማስገደድ እና እስከመተባበር ገፍታበታለች፡፡ የጥቃቱ ሰለባ የሆነችው እህት ሁኔታው በባህላችን የተወገዘና ክብረነክ ፍጹም ጸያፍ ጉዳይ መሆኑንን በመግለጽ ደጋግማ ድርጊቱን ብትቃወምም አማራጭ አልነበረም።

በዚህ ሁኔታ በትግል፣ በሰቆቃ፣ የሚደርስላት በማጣት በተዘጋ ግድግዳ ለመኖር የተገደደችው እህት ሁለት ዓመት ያህል ከተሰቃየች በኋላ አለቃዋ ወደ ጃፓን ስትቀየር ሳትወድ በግድ አብራት ተጓዘች። ጃፓንም ባልና ሚስትም ይህቺን እህት በሳምንት 80ሰዓትና ከዚያ በላይ ማሠራት ሳያንሳቸው መረን የለቀቀውን ሴሰኝነታቸውን ገፉበት። ከዚህም ሌላ ተግባራቸው አደባባይ እንዳይወጣ በዚህች እህት ላይ ከፍተኛ የሆነ ቁጥጥር ማድረግ ጀመሩ፡፡ የምታደርገውን ነገሮች፤ የምትደውለውን ስልክ፤ … መከታተልና መቆጣጠራቸውን ከጸያፍ ተግባራቸው እኩል ቀጠሉበት፡፡ ከዚህም ሳያንስ ወደ ውጭ የምትወጣና ጉዳዩን ለአደባባይ የምታበቃ ከሆነ በቀጥታ ወደ አገሯ እንደሚመልሷት ዛቻቸውንና ማስፈራሪያቸውን ያቆሙበት ቀን አልነበረም፡፡

የፍትህ ደጅ መድረስ የተሳናት ይህቺ እህት አንድ ቀን ወደ ከተማ የመውጣት እድል አግኝታ በመንገድ ካገኘችው ወገኗ ጋር ስልክ የመቀያየርና መጠነኛ መረጃ የማግኘት አጋጣሚ እንደተከፈተላት ታስታውሳለች። እለት እለት የሚደርስባት ግፍ ሲበዛ አንድ ቀን የፍርሃትን በር ሰብራ አመለጠች። ከዚያ በፊት ግን የሚደርስባት በደል መቆም እንዳለበት አምርራ ስትናገር በሁኔታው አለማማር የገባት አሠሪዋ የአንድ መንገድ የአውሮጵላን ቲኬት ገዝታ ወደ ኢትዮጵያ ልትመልሳት ዝግጅቷን ባጠናቀቀችበት ወቅት ይህች ምስኪን አስቀድማ የወሰደችው ርምጃ የህይወቷን አዲስ ምዕራፍ አመላከተ።

አምልጣ እንደወጣች ጎዳና ላይ ላገኘችው ሰው ደውላ “ድረሱልኝ” አለች። አምልጣ መውጣቷን የተረዱት ወንጀለኞች በሁኔታው በመደናገጥ አሠሳ ጀመሩ፡፡ ባል የተባለው ኢትዮጵያ ድረስ በመሄድ ፍለጋ ያዘ፤ ወንጀል ሰርታ ያመለጠች መሆኗን የሃሰት ክስ በመመሥረት ፖሊስ እንዲፈልግለት የሚቻለውን ሁሉ ጣረ፡፡

ለወገን ደራሽ ወገን ነውና ከጨካኞቹ አሠሪዎቿ ከተገላገለች በኋላ ጃፓን በሚገኙት ወገኖቿ ጉያ ተሸሸገች፡፡ እነርሱም በእቅፋቸው ይዘው ሰብአዊ መብት ላይ ከሚሰሩ ድርጅቶች ጋር አስተዋወቋት። ወቅቱ አቶ ኦባንግ በጃፓን የሚገኙ ስደተኛ ወገኖችን ጉዳይ ለመስማትና ለሚመለከታቸው አካላት አቤት ለማለት ሄደው የተመለሱበት ነበር፡፡ የጉዳዩ ባለቤት የሆነቸው እህት ስለሁኔታው ስታስታውስ “ጃፓን ያሉ ወገኖችን እስከወዲያኛው አልረሳቸውም” በማለት ነው።

us embassy japanከለላ የሆኑላት ወገኖች ጉዳይዋን ጃፓን አገር ላለው አለቃዋ ለምትሰራበት የአሜሪካ ኤምባሲ እንዲደርስ አደረጉላት። አምባሳደሩ በጉዳዩ ላይ ምርመራ እንዲካሄድ አዘዙ፤ ዲፕሎማቷና ባሏ ተመሳሳይ ጥቃት በሌሎች ሁለት ሴቶች ላይ ማድረሳቸው ተረጋገጠ፡፡ ከዚህችኛዋ እህት በተጨማሪ ሌላኛዋ የጥቃት ሰለባን ጉዳይ ጥቁሩ ሰው ኦባንግ ሜቶና ድርጅታቸው ከጠበቆች ጋር እየሠሩበት ያለ ጉዳይ ነው፡፡ ለዚህችኛዋ እህት ግን ኤምባሲው የውል ማፍረሻ ገንዘብ ይሰጥሻል፤ ፈቃድ ተሰጥቶሽ ወደ አሜሪካ ትሄጃለሽ ተባለች። እሷ ግን ሞቼ እገኛለሁ በሚል ፍትህ እንደምትፈልግ አስታወቀች። የጉዳዩን መክረር ያስተዋለው ኤምባሲ ዋሽንግተን ዲሲ ለሚገኘው ዋና መ/ቤት አስታወቀ፤ የደኅንነት ሰዎች ጉዳዩን ጃፓን ድረስ በመምጣት መረመሩ፤ ጉዳዩንም አረጋገጡ፤ ወንጀለኛዋን አሠሪዋ ከሥራ እንድትባረር አደረጉ፡፡ በቀጣይም ወደ አሜሪካ የመምጣቷ ጉዳይ ተመቻቸ፡፡

አሜሪካ ከመጣች በኋላ ሁኔታው እንደ ሽልማት የተሰጣት መሆኑን አቶ ኦባንግ በተረዱ ጊዜ ምን እንደምትፈልግ በቀጥታ ጠየቋት፤ እርሷም ፍትሕን የተራበች መሆኗን ገለጸችላቸው፡፡ ኦባንግም ጠበቆች ፈለጉላት፤ ጠበቆቹም ጉዳዩን በጥሞና ከገመገሙና ከእርሷጋር ለረጅም ሰዓታት የወሰደ ቃለምልልስ ካደረጉ በኋላ ጉዳዩ በፍርድቤት መታየት የሚገባው መሆኑን ለአቶ ኦባንግ በማስረዳት የክስ ፋይል ይከፈታል፡፡

“ታሪኳን ስሰማ አዝንኩ። ወንጀሉን የፈጸሙት ሰዎች በትክክልም የፈጀውን ጊዜ ፈጅቶ ፍትህ አደባባይ እንድሚወጡ አመንኩ። እህታችንም ፍትህ እንዲበየንላት የምትመጥን እንደነበር ተረዳሁ” ሲሉ ስለ ጉዳዩ ያስረዱት አቶ ኦባንግ “ለዚህች እህት ጀርባችንን የምንሰጥበት አቅም አልነበረንም” በማለት እርሳቸው የሚመሩት ድርጅት የቆመበትን ዓለት የሆነ ዓላማ አነሱ። የአዲሲቷ ኢትዮጵያ የጋራ ንቅናቄ /አኢጋን/ የአንድ ኢትዮጵያዊ ህይወት ህይወቱ፣ የአንድ ኢትዮጵያዊ ኑሮ ኑሮው በመሆኑ በማመላከት የተፈጸመው ተግባር ከድርጅታቸው ባህሪና መርህ፣ አብረዋቸው ከሚሰሩ አጋሮቻቸው እምነት አንጻር ሊመዘንና ፍትህ ሊያገኝ  እንደሚገባው ጠቆሙ። ከዚህ አንጻር እርሳቸው በግምባር ቀደምትነት የሚጠቀሱ ቢሆኑም ሥራው ግን የተሠራው በእርሳቸው ብቻ እንዳልሆነና እጅግ በርካታ ስማቸው እንዲጠቀስ የማይፈልጉ ኢትዮጵያውያን ብዙ የለፉበትና መስዋዕትነት የከፈሉበት እንደሆነ ያወሳሉ፡፡ ድርጅታቸው አገራቸውንና ሕዝባቸውን የሚወዱ  በርካታ ያልተዘመረላቸው ጀግኖችን ያቀፈ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ ሳያወሱ አላለፉም፡፡

ከጠበቆች ቡድን ጋር ይህንን ጉዳይ ከዳር ለማድረስ አቶ ኦባንግ በራሳቸው የግል ወጪ ከሚኖሩበት ካናዳ ወደ አሜሪካ በመመላለስ የጠበቃ ቡድኑ ጉዳዩን አምኖበት እንዲቀበለው በዙ ደክመዋል። ከትርጉም ጀምሮ የድርጅታቸው አባላት ድጋፍ አድርገዋል። ብዙ ጊዜ ውሸት ስለሚያጋጥም የማሳመኑ ሂደትም ቀላል አልነበረም። ትግሉ ጉልበት ካላቸው ጋር ስለነበር እህታችንን ማበረታታቱም ሌላ ስራ ነበር። ብቻ ሁሉም ሆኖ በጥቅሉ ለአራት ዓመታት ያህል የፈጀው ክርክር የፍትህን ብርሃን ፈንጥቆ በማብራት ተጠናቀቀ። በፍርድቤቱ ብያኔ 3.3 ሚሊዮን ዶላር ካሳ ተፈረደላት፤ አሸነፈች። የህግ ልዕናው ስጋዋን አጠገገው። ወንጀለኞቹ ወደ አውስትራሊያ ሸሽተው ስለነበር እነርሱን የተከታተሉና የሕግና የመረጃ ድጋፍ የሰጡ አካላት ከካሣው ድርሻቸውን ወስደዋል፡፡ አውስትራሊያዊው የዲፕሎማቷ ባለቤት እዚያው እያለ ህይወቱ አልፋለች፤ እርሷም ፍትህን ለመሸሽ እዚያው ተሸሸጋለች፡፡

“ቁስሌ ዝም ብሎ የሚጠፋ አይደለም። የደረሰብኝ ጉዳት ስጋ ሲጠግብ የሚረሳ አይደለም። በርካታ ስፍራዎችን የነካካ ነው። ሁሉንም ክፍሎች አድኖ ነጻ መሆን ቀላል አይደለም። በደሌ ፍጹም አይርሳም። ሆኖም ዝምታዬን ሰብሬ በመነሳቴ ገሃድ ባይወጡም ዛሬ ለብዙዎች ምስክርና ምሳሌ ለመሆን በቅቻለሁ” በማለት የጥቃቱ ሰለባ የሆነችው እህት ታስረዳለች።

ወደ ኋላ መለስ ብላም ስለባለቤቷ ስትናገር ጃፓን ሆና የሆነችውንና ያጋጠማትን ካስረዳችው በኋላ “ከእኔ ጋር ኑሮ መቀጠል ትፈልጋለህ ?” ስትል ጠየቀቸው። በሶስተኛው ቀን ደውሎ አለቀሰ። ሃዘኑንን ገለጸ። እናም አንድ ትልቅ ማጽናኛ ዜና አሰማት። “ሆን ብለሽ አላደረግሽውም። እንዴት በዚህ ሁኔታ ውስጥ ሆነሽ እተውሻለሁ?” ነበር ያላት። ወደ አሜሪካ ተዛውራ ፍትህ ከተበየነላትም በኋላ አብረው ናቸው፤ የልጅ በረከትን አይተዋል። “ሳያንቋሽሸኝ ስለተቀበለኝና እንከንየለሽ የኑሮ አጋሬ ስለሆነ አመሰግነዋለሁ!!” ስትል የደረሰባትን ጉዳት ተረድቶ ስላደረገላት ሁሉ ያላትን ክብር ትገልጥለታለች። አዲስ አበባ ባለው የአሜሪካ ኤምባሲ አማካይነት ተጠቅመው ባለቤቷ ላይ ያደረሱትን በደልም በክፉ ትዝታነቱ ታነሳዋለች።

“ዛሬ ባለቤቴ ከኔ ጋር ነው። ከልጃችን ጋር በደስታ ቤተሰባችንን እየመራን ነው። ለባለቤቴ ልዩ ክብር አለኝ። የሆነውን ሁሉ አውቆ ፊቱን አላጠቆረብኝም። ፍቅሩን አብዝቶ ይሰጠኛል። የተፈጸመብኝን ክፉ ድርጊት ከሰማበት ቀን ጀምሮ ለኔ ያዝናል። ‘አውቀሽ ያደረግሽው ነገር ስላልሆነ ያንቺ ችግር አይደለም’ ሲል ሁሌም ስሜቴን ይጠግነዋል። አሁን እንደሚገባኝ ከሁሉም በላይ የሚጠግነኝ መልካምነት ነው። ወገኖቼ፣ ኦባንግ፣ ቤተሰቦቼ፣ ባለቤቴ … ፈውሴን አፍጥነውታል” በማለት ስሜት የተቀላቀለበት ልባዊ ምስጋናን ታቀርባለች።

ይህቺ እህት ጥሪ አላት፤ በዝምታ የተሸበቡ እህቶች እንዲናገሩ። “ገሃድ ውጡ!” ትላለች። አያይዛም “በደል ተሸክመው የተቀመጡ በነፍስም በስጋም የታመሙ አሉ። መጋረጃውን ገልጸው ወደ አደባባይ ካልወጡ ፍትህ መጋረጃ ከፍታ እነሱ ዘንድ አትደርስም” ስትል ሰዎች አውቀው ባልሰሩት ጥፋት ስለማይወቀሱ ፍትህ በሚሻው ጉዳይ ሁሉ መሸሸግ ሞኝነት እንደሆነ አድምቃ ታሰምርበታለች። ማንኛውም ጉዳይ ቢሆን ሊሸሸግ እንደማይገባ አጥብቃ ትናገራለች። መናገር ማርፍ እንደሆነ፣ በመናገር ውስጥ እረፍት እንዳለ ትመክራለች።

በጃፓን ላሉ ወገኖች ለዩ ምስጋና እንዳላት ደጋግማ የምትናገረዋ እህት፣ “ዝቅ ብሎ ለተላላከኝ ኦባንግ ያለኝ ክብር ትልቅ ነው” ስትል ምስጋና አቅርባለች። በመቀጠልም ተመሳሳይ ጥቃት ለሚፈጸምባቸው ወገኖች ድጋፍ ለመስጠት ዝግጁ መሆኗን አስረግጣለች። እንደ እርሷ ለተጎዱ ሁሉ የበኩሏን ሁሉ ለማድረግ ቃል ገብታለች።

አቶ ኦባንግ በበኩላቸው “ይህ ደሞዛችን ነው። ይህ ርካታችን ነው። ከዚህ በላይ ርካታ የለንም” ሲሉ ስሜታቸውን ይገልጻሉ። ማንም ከህግ በላይ እንዳይደለ ከማረጋገጥ በላይ ታላቅ ተግባር እንደሌለ ማሳየት ታላቅ ቁም ነገር እንደሆነና ዜጎች የትም ሆነ የት መብታቸውን ማስከበር እንዳለባቸው፣ ለመብታቸው መታገል እንዳለባቸው ያሳስባሉ። “ይህችን እህት ሳገኛት ዘሯን፤ ብሔሯን ወይም ሃይማኖቷን አልጠየኩዋትም። በደልዋን ሰማሁ። ለፍትህ ትመጥናለች አልኩ። ከሥራ አጋሮቼ ጋር ሆነን ለህግ የበላይነት ተነሳን። ፍትህ ድል ነሳች። ይህና ይህ ነው የእኛ እርካታ!!” ሲሉም ለታፈኑ ሁሉ የ“ተነሱ” ጥሪ ያቀረባሉ። አያይዘውም “ሰዎች ሁሉ እኩል ነን። ጉዳታችን በገንዘብ አይለካም” ሲሉ የህሊና ቁስል ከባድ መሆኑን ይጠቁማሉ።

ደቡብ ኮሪያ

ባለፈው ሳምንት የጥቁሩ ሰው ውሎ ደቡብ ኮሪያ ነበር። ኢትዮጵያዊያን ጀግኖች የዛሬ 56 ዓመት ደም፣ አካልና ህይወት የገበሩላት ህዝብና መንግስታቸው የረሷቸውን ኢትዮጵያዊያኖች እንባ ለማበስ!! በጉዟቸው የአገሪቱን የሰደተኞችና ኢሚግሬሽን ቢሮ ባለስልጣናትን፣ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳይ ሹማምንትንና የማህበራዊ ተቋማትን ኃላፊዎችን አነጋግረው ተመልሰዋል።

የኑሮ መስመሩ የጠፋባቸውን ወገኖች አሰባስበው ባንድ አዳራሽ ውስጥ የጀመሩት ንግግር የዛሬ 56 ዓመት ለደቡብ ኮሪያ ነጻነት ለተሰው ኢትዮጵያዊያኖች መታሰቢያ በቆመው የመታሰቢያ ሃውልት ዙሪያ ተጠናቋል። ሁሉም የመኖሪያ ወረቀት የሌላቸው ወገኖች በቅርቡ ምላሽ የሚያገኙበትን ሁኔታ አመቻችተው ተመልሰዋል። “ላልተዘመረላቸው የወገን አለኝታ ክብር እንሰጣቸው” በሚል በተለያዩ የማህበራዊ ገጾች ስማቸው እየተነሳ ያሉትን አቶ ኦባንግ ሜቶን በደቡብ ኮሪያ ምን አድርገው ተመለሱ? በሚለው ጉዳይ ላይ አነጋግረናቸዋል ዘገባውን እናስከተላለን።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Social Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. zt says

    May 4, 2016 12:55 am at 12:55 am

    widase kentu mehonun kemeles temirehal. weyanen yeminidemesiaew me che new?/

    Reply
  2. abrham says

    May 8, 2016 01:47 am at 1:47 am

    ጎልጉል፣ አንድ ጉዳይ ልንገራችሁ፤ አቡጊዳን ስከታተል ዓመት ሆነኝ። አቡጊዳ ህወሓት እጅ ገብቷል። እንዴት አወቅሁ። 1/ አስተያየት መስጫው አጠገብ “ሻብያና ወያኔን ለመከላከል ብለን አስተያየቶችን ለማጣራት ተገድደናል” የሚለው ተነስቷል፤ 2/ ስክሪንሾት ሁለት ጊዜ ወስጄአለሁ፤ “ዳዊ” የተሰኘው ሁለቱንም ጊዜ ያልተለጠፉ አስተያየቶች ላይ አስተያየት ከሰጠ በኋላ አንድ ላይ ተለጥፈዋል። ለምሳሌ፣ ቅርብ ጊዜ ዶ/ር አሰግድ የተባለው በጻፈው ላይ 53 አስተያየቶች እንደተሰጡ የሚያሳይ ቢሆንም መጀመሪያ ከ1-29 ተለጠፉ፤ ከዚያ ከ30-50። “ዳዊ” ሁሉም ጋ መልስ ሰጭና አወዛጋቢ መሆኑ ቢታወቅም፤ #50ኛ አስተያየቱን ለ”አሃ” #47ኛ የሰጠው ከመለጠፉ በፊት ነው።

    Reply
    • zt says

      May 17, 2016 06:54 pm at 6:54 pm

      ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር !

      Reply
  3. netsanet melese says

    December 5, 2017 06:59 pm at 6:59 pm

    ወያኔን ያጥፋልን ትግሬም ወያኔም 1 ናቸው ጥርግ
    ይበሉልን ባንዳ!

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am
  • በትግራይ የሰላም ስምምነቱን መሠረት ያደረገ የሽግግር ፍትሕ እንደሚፈጸም ተገለጸ December 13, 2022 09:20 am
  • ከ30 ሚሊየን ብር በላይ በሚሆን ሌብነት የተከሰሱት የደኅንነት መ/ቤት ሠራተኞች ክስ ተመሰረተ December 13, 2022 09:06 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule