• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ህወሃት – 9 ስደተኞችን ደብዳቤ ጽፎ ከአሜሪካ ወሰዳቸው

March 11, 2016 09:09 am by Editor 5 Comments

ከተለያዩ አገራት አሜሪካ ገብተው የስደት ማመልከቻ ያስገቡ 9 ኢትዮጵያውያንን ህወሃት ተረከቦ ወደ አገር ቤት እንደወሰዳቸው ታወቀ። አንዱ ራሱን ለማጥፋት ሞከሮ ነበር። ወደ ኢትዮጵያ ቢሄድም የጤናው ሁኔታ አልታወቀም። ድርጊቱን አስመልክቶ አቶ ኦባንግ ሜቶ “ከህወሃት ተግባር በላይ በራሳችን አዝኛለሁ” ሲሉ ወጣቶቹን ለማዳን ያደረጉት ጥረት መረጃው ዘግይቶ ስለደረሳቸው አለመሳካቱን አመለከቱ።

“ለቤተሰቦቼ የት እንዳለሁ እንኳን ነግሬያቸው አላውቅም” ሲል የተናገረውን ወጣት ጨምሮ ህወሃት የተረከባቸው ኢትዮጵያዊያን ወግኖች አሜሪካ ለመድረስ እስከ 14 ወራት ፈጅቶባቸዋል። በብራዚል፣ በኮሎምቢያ ጫካ አቋርጠው፣ በፓናማ ወንዝ ተሻግረው፣ በሜክሲኮ አድርገው በአጠቃላይ እስከ 16 የሚደርሱ አገራትን አልፈው በተለያዩ መንገዶቸ አሜሪካ ደርሰው ጥገኝነት የጠየቁት ወገኖች ህጉ ከሚፈቅደው ውጪ ከስድስት ወር በላይ በፍሎሪዳ ጠቅላይ ቅዛት ማያሚ እስር ቤት መቆየታቸውን ለአቶ ኦባንግ በአስራ አንደኛው ሰዓት የላኩት “የድረሱልን” ደብዳቤ ያስረዳል። መረጃቸው እንደሚያመለክተው ከተለያየ የኢትዮጵያ ክፍል የመጡት ወገኖች በፍሎሪዳ እስርቤት ከአንድ ወር እስከ አመት ተኩል ድረስ በእስር ቆይተዋል፡፡

አቶ ግርማ ብሩ የሚመሩት የህወሃት የአሜሪካ ቢሮ ስደተኞቹ ቢመለሱ ምንም አይሆኑም፣ ምንም አይደርስባቸውም፣ ሰላማዊ ኑሮ መኖር ይችላሉ፣ ወዘተ በማለት በጻፈው ደብዳቤና አዘጋጅቶ በሰጠው የመጓጓዣ ሰነድ አማካይነት ወጣቶቹ ተላልፈው ሊሰጡት ችሏል።

ህወሃት በኤርትራዊነት መታወቂያ የራሱን ወገኖች ለስደት በምዕራባውያን አገራት እየላከ ኢትዮጵያውያንን ሲያሰልል፤ በባህርና በበረሃ ተንገላተው አሜሪካ የገቡትን ምስኪን ዜጎች ላይ የወሰደው ርምጃ “ዲያስፖራውን የመበቀያ አንዱ አካል ነው” ተብሏል።

“ኑሮዬ ሳይስተካከል ለቤተሰቦቼ የት እንዳለሁ እንኳን አላሳውቅሁም። እናትና አባቴ ልሙት፣ ልኑር አያውቁም፤ ከተለየኋቸው ጊዜ ጀምሮ ስልክ ሳልደውል አራት አመት ከ11 ወራት አልፈውኛል” ሲል ለአቶ ኦባንግ የድረሱልኝ ጥሪ ካሰሙት ወጣቶች አንደኛው ተናግሯል፡፡ ዘጠኙ በአንድነት ተላልፈው ከመሰጠታቸው ጥቂት ቀናት አስቀድሞ ነበር አቶ ኦባንግ ደብዳቤያቸው የደረሳቸውና ጉዳዩን የሰሙት።

“እንደሰማሁ” አሉ አቶ ኦባንግ “ወዲያውኑ ስደተኞቹን የሚወክል ጠበቃ ያዝኩ። የወጣቶቹ ከስድስት ወር በላይ መታሰር ከህግ አንጻር አግባብ ባለመሆኑና ስደተኞቹ ሊመለሱ እንደማይገባ ለማውቃቸው እንደራሴዎችና ሴናተሮች በማስረዳት የእስር ውሳኔ ላስተላለፉት ዳኛ ደብዳቤ ሊላክ የሰዓታት ዕድሜ ሲቀር መርዶውን ሰማሁ” ብለዋል፡፡

ለወትሮው ረጋ ብለው በመናገር የሚታወቁት ኦባንግ “ለአንድ ቀን ተቀደምን” ሲሉ በቁጣ ነበር ስሜታቸውን የገለጹት። የጎልጉል የአሜሪካ ዘጋቢ ያነጋገራቸው አቶ ኦባንግ ቁጣቸውን ሊደብቁ በማይችሉበት ሁኔታ “ከህወሃት በላይ በራሳችን አዘንኩ” ብለዋል። “ለምን?” በሚል ለቀረበላቸው ጥያቄ ሲመልሱም “በተመሳሳይ መንገድ ተሰድደው፣ ታስረው፣ ዛሬ በመልካም ሁኔታ ላይ ያሉ ወገኖች የ5 ሺህ ዶላር ዋስ ሆነው ልጆቹን ማስፈታት ይችሉ ነበር ። ዳሩ ምን ያደርጋል ሁላችንም መነሻችንን እንረሳለን” ሲሉ ጉዳዩን አስቀድመው የሚያውቁ ወገኖች ላሳዩት ቸልተኛነት ወቀሳ ሰንዝረዋል።

“አቶ ግርማስ ቢሆኑ” አሉ አቶ ኦባንግ “ይህን ደብዳቤ እንዴት ይጽፋሉ? ወይም ሲጻፍ እንዴት ዝም ይላሉ? የጉዞ ሰነዱ ተሰርቶ እንዲላክስ ለምን ይፈቅዳሉ? ምንም ቢሆን እርሳቸው ሳያውቁ የሆነ ነገር የለም፤ ኅሊና ካላቸው በጣም ሊያፍሩበት ይገባቸዋል፤ እርሳቸውም ሆኑ አብረዋቸው የሚሰሩት ራሳቸውን በእነዚህ ልጆች ጫማ አስገብተው ማየት ይገባቸው ነበር፤ እነርሱ አገልግሎታቸውን ሲጨርሱ እዚሁ ከነቤተሰቦቻቸው ጥገኝነት ጠይቀው ኑሯቸውን ይቀጥላሉ፤ በአየር፣ በምድር፣ በወንዝ በስንት ስቃይና መከራ እዚህ የደረሱትን ልጆች ግን ደህና አገር እንዳለው የጉዞ ሰነድ ልከው ባዶ እጃቸውን ወደመጡበት እንዲመለሱ ያደርጋሉ፤ ይህ ወራዳና አጸያፊ ተግባር ነው፤ አገሪቱን ወይ በትክክል አያስተዳድሩ ወይ አገሩን ለቅቀው የሚወጡትን የፈለጉበት እንዳይኖሩ በሩ ይዘጋሉ፤ ኅሊና አለኝ ለሚል ሰው ይህ እጅግ አሳፋሪ ነው” ሲሉ ይወቅሷቸዋል።

ከስደተኞቹ መካከል አንዱ ወጣት በአገር ውስጥ የሚካሄደው ሰቆቃ ያስመረረው ከመሆኑ የተነሳ ወደ ኢትዮጵያ ከሚመለስ በአሜሪካ እስርቤት ለመሞት እንደሚመኝ መናገሩን አቶ ኦባንግ ጠቁመዋል፡፡ “በረሃና ወንዝ ስናቋርጥ በርካታ ወንድምና እህቶቻችንን አጥተናል፤ ማንም ስለ እነርሱ ግድ ያለው የለም፤ ታዲያ ለምን ለኛ ግድ ያላቸው ለመምሰል ይሞክራሉ” በማለት እንዳወራላቸው አቶ ኦባንግ ጠቅሰዋል፡፡

አገር ቤት ስራ አለመኖሩን፣ ችጋር፣ ረሃብና ድርቅ ዜጎችን እየጠበሰ መሆኑንን፣ እስርና ግድያ፣ አፈና ባለበት ሁኔታ እነዚህን ምስኪኖች ሰብስቦ መውሰድ ህወሃት ዲያስፖራውን ከመበቀል ያለፈ ትርጉም እንደሌለው በመግለጽ ዜጎች ከወዲሁ ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ አመልክተዋል።

የአሜሪካ እንደራሴዎች ምክርቤት አባላት ደብዳቤ ለመጻፍ ቃል ገብተው፣ ጠበቃ ተገኝቶ ወጣቶቹን ለማስፈታት የሚያስችል ርምጃ ከመጀመሩ አንድ ቀን በፊት በተፈጸመው ድርጊት ክፉኛ ማዘናቸውን የጠቆሙት ኦባንግ ሜቶ አሁንም እስር ላይ ያሉትን ለማስፈታት ጥረታቸውን እንደሚገፉበት ተናግረዋል። ከእንግዲህ ጉዳዩ የህወሃት ወይም በዋሽንግተን ዲሲ ያስቀመጠው ጽ/ቤቱ አይደለም፤ ጉዳዩ የራሳችን ነው የሚሉት “ጥቁሩ ሰው” ኦባንግ “ህወሃት የጉዞ ሰነድ እያዘጋጀ የራሱ ጽ/ቤት ባደረገው ኤምባሲው አማካኝነት እየሰጠ ስደተኞች ላይ የሚፈጽመው ይህ ተግባር የሚቆምበት ሁኔታ ከእንደራሴዎች ጋር በመነጋገር ተጽዕኖ የማድረግ ሥራ” ካሁኑ መጀመሩን ሳይጠቁሙ አላለፉም፡፡

ኦባንግ ስደተኛ ወገኖች ባሉበት ሁሉ ፈጥነው በመድረስና አለኝታ በመሆን የሚታወቁ ኢትዮጵያዊ መሆናቸውን ዜጎች የአደባባይ ምስክርነት በ“ቃላቸው” ብቻ የሚሰጧቸው ሰው መሆናቸው የሚዘነጋ አይደለም።


ማሳሰቢያ፤ በተለይ በስም ወይም በድርጅት ስም እስካልተጠቀሰ ድረስ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ® ላይ የሚወጡት ጽሁፎች በሙሉ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ®ንብረት ናቸው፡፡ ይህንን ጽሁፍ ለመጠቀም የሚፈልጉ ሁሉ የዚህን ጽሁፍ አስፈንጣሪ (link) ወይም የድረገጻችንን አድራሻ (https://www.goolgule.com/) አብረው መለጠፍ ከጋዜጠኛነት የሚጠበቅና ህጋዊ አሠራር መሆኑን ልናሳስብ እንወዳለን፡፡

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: Full Width Top, Middle Column

Reader Interactions

Comments

  1. Yinegal Belachew says

    March 11, 2016 10:08 am at 10:08 am

    fotowuna debdabew tegelbtual. mastekakel ketechale bistekakel tru new.

    Reply
    • Editor says

      March 12, 2016 10:56 am at 10:56 am

      Yinegal Belachew

      የተገለበጠው በስህተት ሳይሆን ሆን ተብሎ ነው – ምክንያቱን ማስረዳት አስፈላጊ መስሎ ቢታይም ከጽሁፉ ዋና ሃሳብ አንጻር ከማስረዳት እንድንቆጠብ ሆነናል

      ከዚህ በላይ ማስረዳት ባለመቻላችን ይቅርታ እንጠይቃለን

      ከምስጋና ጋር

      አርታኢ

      Reply
  2. abe says

    March 11, 2016 12:49 pm at 12:49 pm

    Wishetam,Guregna.

    Helpless and disoriented himself ,how on earth could tsfenga Obang help?

    Reply
  3. geresu says

    March 11, 2016 02:03 pm at 2:03 pm

    መላ የኢትዮጵያ ህዝቦች: ሻቢያ: ደጋፊም ሆናችሁ ተቀዋሚ የሆናችሁ ወያኔን ዛሬ ካልመታህ እየተመታህ ትኖራለህ! ወያኔ ህግ እያስከበረ ሳይሆን ለእሱ የሚመቸዉን ብቻ ኦየፈፀመ ነዉ:: ምን እያሰብክ ነዉ? ፈሪዉ ብአዲን! ኦህዲድ!ሶዴፓ! ደህዲን! የተገነዛችሁ የፈሪ መንጋወች!!!

    Reply
  4. gud says

    March 12, 2016 02:00 pm at 2:00 pm

    Trump is coming .
    No hope for Jewar and other parasites . Real American is coming

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “ሚካኤል ችግኝ ነው። … ችግኝ ይተክላል” ቴዲ አፍሮ June 29, 2022 03:30 am
  • “የእኔን ልጆችና የልጅ ልጆች (22ቱንም) የቀበርኩት እኔ ነኝ” አቶ መሀመድ የሱፍ ከምዕራብ ወለጋ June 28, 2022 01:07 pm
  • የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ June 20, 2022 11:34 pm
  • “የወልቃይትን ጉዳይ ለድርድር የማናቀርበው ቀይ መስመራችን ነው” ርዕሰ መስተዳድር ይልቃል June 12, 2022 07:09 pm
  • የሰሜን ምዕራብ ዕዝና የአማራ ልዩ ኃይል ተከዜ ክፍለ ጦር ዕውቅናና ሽልማት ተሰጣቸው June 12, 2022 06:21 pm
  • ሀገር በቀል ባህላዊ የግጭት አፈታቶችን በተገቢው በመጠቀም ዘላቂ እርቅና ሰላምን ማምጣት ይቻላል June 12, 2022 05:40 pm
  • የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በገረጂና በቀበና ያስገነባቸውን የመኖሪያ አፓርትመንቶች አስመረቀ June 12, 2022 05:35 pm
  • በኦነግ ሸኔ ፈርሶ የነበረውና ወታደራዊ ጠቀሜታ ያለው ድልድይ ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት ጀመረ June 10, 2022 09:13 am
  • ጃዋር በዳውድ ኢብሣ ቀይ መስመር ተሰመረለት June 8, 2022 12:59 pm
  • ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር June 8, 2022 11:53 am
  • እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ? June 8, 2022 05:59 am
  • ሕዝብ ድምፅ የነፈጋቸው “ፓርቲዎች” የሽግግር መንግሥት ይቋቋም አሉ June 7, 2022 01:11 am
  • “አድጌ እንደናንተ መሆን እፈልጋለሁ” June 5, 2022 06:58 pm
  • በሳምንት ለ100 ያህል ሕሙማን አገልግሎት የሚሰጥ የኩላሊት ዕጥበት ማዕከል ሥራ ጀመረ May 30, 2022 02:20 am
  • የጥቁር አንበሳ ዕጩ መኮንኖች (ካዴቶች) ተመረቁ May 29, 2022 04:01 pm
  • “ኢትዮጵያን መንካት አይቻልም!!” በሚል ቁጭት ነው እየሠራን ያለነው May 29, 2022 01:04 pm
  • “ከሞፈርና ቀንበር ወደ ትራክተር” በሚል መርህ ለአማራ ገበሬዎች የግብርና ሜካናይዜሽን ተሰጠ May 29, 2022 02:02 am
  • ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል May 27, 2022 02:51 am
  • “እኛ የምናውቀው ነገር የለም፤ የሚያጣሉን ፖለቲከኞች ናቸው” የአማራ ወዳጃቸውን አደራ ቤት የመለሱ የቅማንት ተወላጅ May 27, 2022 01:40 am
  • ትግራይን አገር እናደርጋለን፤ “በውይይት እና በጦርነት” ሁሉንም ጉዳይ እንቋጫለን – የወንበዴው መሪ ደብረጽዮን May 26, 2022 09:18 am
  • “ሁለቱ የምዕራብ ዕዝ ተዋጊ ዶክተሮች” May 26, 2022 08:19 am
  • ወደ ትህነግ ሊተላለፍ የነበረ አምስት ሚሊዮን ብር ከ20 ተጠርጣሪዎች ጋር ተያዘ May 25, 2022 01:57 am
  • የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች May 19, 2022 09:37 am
  • በጦርነቱ የተጎዱ አካባቢዎችን ለማቋቋም የሚውል የ15 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር ድጋፍ የዓለም ባንክ May 16, 2022 10:22 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2022 · Goolgule