አቶ ሽመልስ አብዲሳ “በትላንትናው እለት የተናገረው ነው” ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ከሰባት ወር በፊት የብልፅግና ፓርቲ ገና በምስረታ ሂደት ላይ እያለ የተናገረው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል። በወቅቱ የድርጅቱን አባላትና አመራሮች በኦቦ ለማ መገርሳ፣ ወ/ሮ ጠይባ እና በዶ/ር ሚልኬሳ ከሚመራው ብሔርተኛ ቡድን ለመነጠልና በድርጅቱ ውስጥ ተፈጥሮ በነበረው የኃይል ሹኩቻ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት በሚደረግ ጥረት የተናገረው እንደሆነ ተረጋግጧል።
አቶ ሽመልስ የተናገረበት ግዜና ቦታ ምን ያህል የተለያየ ቢሆንም አዲስ አበባን አስመልክቶ የተናገረው ነገር መቼም፥ እንዴትም ትክክል አይሆንም። ይሁን እንጂ በወቅቱ ድርጅቱ ውስጥ የጃዋር መሃመድ ጉዳይ አስፈፃሚ የነበሩት ከላይ የተጠቀሱት የኦዴፓ አመራሮች ከኮዬ_ፈቼ ኮኖደሚኒዬም ጋር በተያያዘ ሲያራምዱት የነበረው አቋምና ጉዳዩ በብሔርተኞቹ ዘንድ የነበረው ድጋፍ ሲታሰብ እነ ሽመልስ የነበሩትን አጣብቂኝ በግልጽ ያሳያል። ያ ባይሆን ኖሮ ተቀናቃኙ ቡድን አሸናፊ ቢሆን ኖሮ አሁን ላይ ጃዋር_መሃመድ መገኛው እስር ቤት ሳይሆን ቤተመንግሥት ይሆን ነበር። ስለዚህ አቶ ሽመልስ የተናገረውን ነገር ከዚህ አንፃር ማየት ተገቢ ነው።
ሁለተኛው ምክንያት ደግሞ ከሰባት ወር በፊት የተደረገውን ንግግር ልክ ትላንት እንደተደረገ ተደርጎ የወጣው የጃዋር ጉዳይ አስፈፃሚዎች ለግምገማ ሲቀርቡ እንደሆነ መገንዘብ ይቻላል። ስለዚህ የመንግሥት ሥልጣንና ኃላፊነት ይዘው በአክቲቪስት የሚመሩ፤ ለምሳሌ ጥቅምት 12/2012 ማታ አቶ ጃዋር መሃመድ ባስነሳው ሁከትና ብጥብጥ በንፁሃን ዜጎች ላይ ጥቃትና ጉዳት እንዳይደርስ ከመከላከል ይልቅ የጃዋር ጠባቂ ለመሆን በውድቅት ሌሊት መኖሪያ ቤቱ ድረስ የሄዱት ለማና ጠይባ፣ ልክ በድርጅቱ ግምገማ ሲደረግባቸው ከሰባት ወር በፊት የተቀዳን ንግግር ለፅንፈኛ የአማራ አክቲቪስቶች Leak አደረጉ። ህዝቤ እየተነሳ እሪሪሪሪ አለ።
ነገር ግን ይሄን መረጃ አሾልኮ ያወጣው ቡድን ቀንደኛ የጃዋር ጉዳይ አስፈፃሚዎች፣ ይህንንም ያደረጉት ጃዋርንና ግብረ-አበሮቹን ለማስፈታትና እንደለመደው አናታችን ላይ እንዲፈነጭ ለማድረግ ነው። ስለዚህ ይህን ሤራና ተንኮል የጠነሰሱት በግምገማ ከአባልነት ሊሰረዙ እንደሆነ ሲያውቁ ነው። ነገር ግን የእነሱ ቡድን አሸናፊ ሆኖ ቢወጣ ኖሮ ሽመልስ የተናገረውን እነሱ በተግባር የሚያደርጉትን እና ያደረጉትን ነው። የኮዬ ፈጬ ኮንደሚኒየም ለነዋሪዎች ሊተላለፍ በኦሮሚያና አዲስ አበባ መካከል ያለው የድንበር ጉዳይ መፍትሔ ስላላገኘ ብለው የፃፉት ደብዳቤ ለዚህ ማሳያ ነው። በአጠቃላይ አቶ ሽመልስ ከሰባት ወር በፊት የተናገረው ከዚህ ፅንፈኛ ቡድን ጋር በነበረው የኃይል ሽኩቻ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት ነው።
“ዋሽቶ ማስታረቅ” እንደሚባለው አቶ ሽመልስ የተናገረውን ተናግሮ ድርጅቱና የክልሉ መንግሥትን ከእንዲህ ያለ ፅንፈኛ ቡድን መታደግ በመቻሉ ሊያስመሰግነው ይገባል። ከሰባት ወር በፊት ሆነ ትላንት በተለይ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ የተንፀባረቀውን አቋም ፋሽታዊ ነው በማለት አውግዤያለሁ። ነገር ግን ሽመልስ ሆነ ሌላ ሰው ይሄን የተናገረው በእውን የተረጋገጠ ፋሽታዊ አቋምና አመለካከት ያላቸው አመራሮች በክልሉም ሆነ በሀገር ደረጃ አሸናፊ ሆነው እንዳይወጡ ለማድረግ በሚል ስለሆነ “እሰይ አበጀህ” ብዬዋለሁ። ምክንያቱም ያ ቡድን ባይገታ ኖሮ ምን ሊከሰት እንደሚችል በዚህ አመት ጥቅምት 12 እና ሰኔ 22 በተግባር አይተንዋል።
ስዩም ተሾመ
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣበ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።
getachew says
እንደው ዝም ይሻላል
በለው ! says
“ከሚገድለኝ ሰይጣን ይልቅ የሚሰድበኝ ባለስልጣን ይሻለኛል! ሽመልስ የተናገረው በወቅቱ ትክክል ነው‼️” ስዩም ተሾመ
ቼ በለው!
** ይህ ተርቦም፡ ተጠምቶም፡ ታርዞም፡ ተቃጥሎም ፡ተቆራርጦም፡ተፈናቅሎም፡ተገሎም የሚጨፍር ቆራጥ የፈረደበት ቦርቃቃ ሕዝብ ከሰይጣንና ከባለሥልጣን ውግረት ሌላ ምን ምርጫ አለው! ወደሽ ነው ገጣቢት ንጉስ ትመርቂ…
“አቶ ሽመልስ አብዲሳ “በትላንትናው እለት የተናገረው ነው” ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ፒፒፒ (የፒኮክ ብልጥገና ፓርቲን )ከብሔርተኛ ቡድን ለመነጠልና በድርጅቱ ውስጥ ተፈጥሮ በነበረው የኃይል ሹኩቻ አሸናፊ ሆኖ ለመውጣት በሚደረግ ጥረት የተናገረው እንደሆነ ተረጋግጧል።”…
**ይህ ንግግር ስለተፎካካሪ ቡድን አክራሪና ፅንፈኛ ጎራ መለየት አያወራም! በትክክል የሸፍጥ(ሴራ፡ሰሬ) ፓለቲካ የህወሓት ትምህርቶችን ብልጥገና እንዴት በፈጠነና በተቀናጀ መልኩ ኢዴፓን አጃጅለን…(አግባብተንም ግራ አጋብተንም) ኢትዮጵያን በልካችን አፍርሰን ሠርተን፤ በገዳ ሥርዓት በአፍሪካ ቀንድ የበላይነትን ተቀዳጅተን በሕዝብ ቁጥር ለሚቀጥሉት ሶስት ሺህ ዓመት በኦሮሙማ የሚመረጥና በኦሮሞ የሚመራ ብልጥገና እንዴት እንደሚቀጥል የተነደፈ ሐሳብ የተንፀባረቀበት ንግግር ቀደሞ፡ ሽመልስ አብዲሳም ይሁን ዓብይ አህመድ ሰበርናቸው አበረርናቸው ተመልሰው ያለእኛ ፍቃድ እዚህ አይደርሱም ዘመንና ሥልጣን በእጃችን ነው ” ሲሉ አባራሪና ተባራሪ፡ ባለቤትና መጤ ፡ባለግዜና ባለብዙ የሰው ኅይል አንደኛና ሁለተኛ ዜጋ ብልጥግና መሥርቷል! ስለዚህ ከሰይጣንና ከሥድብ ማማረጥ ቅንጦት ነው።
እንዳለች እንደወረድች መዋጥ ሕገመንግስታዊ ግዴታ መሆኑን መረዳት ያሻል…አንዳንዴ ሲተነተን መበተን አለ!!
“… ተቀናቃኙ ቡድን አሸናፊ ቢሆን ኖሮ አሁን ላይ ጃዋር_መሃመድ መገኛው እስር ቤት ሳይሆን ቤተመንግሥት ይሆን ነበር። ስለዚህ አቶ ሽመልስ የተናገረውን ነገር ከዚህ አንፃር ማየት ተገቢ ነው።”
**ጀዋር ኮዬ ፈጬ ላይ ሰው ሊፈጭ ሜንጫና ሚስማር ይዞ ሲወጣ ሁለተኛው መንግስት ሆኖ ታምኖበት እንጂ የሕንጻው መሐንዲስ ወይም ቁጠባ ያደረገ ቡድን አዛዥ ሆኖ አልነበረም። ማነህ? ወዴት ነህ? ያለው የለም! ያም የሚነግረን “አንተ በዚያ ቅደም እኛ በሩቁ እንጠብቅሃለን የፈራ ይሸሻል ትወርሳላችሁ” ተብሎ ነው።የቡራዩን የዘር ማፅዳት የተመከረበት ሥራ ታዝበናል፡ በጦፈው የኮረና የዓለም ሥጋት ወረርሽኝ በሽታ ዘመን መንገድ የተጣሉ ዜጎችን አይተናል፡ ሥራውም በደንብ የተቀናጀ በሥላጣን ተዋረድ በመመሪያ የተደገፈ ነው ሽመልስ አሁን የተናገረውም በቋንቋና በኢኮኖሚ ውህድ ማንነት ያለውን ጥሩ የአዲስ አበቤን ሕዝብ ኑሮ ማተራመስ፡ መስበርና ማፍረስ! አጠና ገጀራ ይዞ ከማስፈራራት የሰለጠነና ጥሩ ቁማር ነው።
“ጥቅምት 12/2012 ማታ አቶ ጃዋር መሃመድ ባስነሳው ሁከትና ብጥብጥ በንፁሃን ዜጎች ላይ ጥቃትና ጉዳት እንዳይደርስ ከመከላከል ይልቅ የጃዋር ጠባቂ ለመሆን በውድቅት ሌሊት መኖሪያ ቤቱ ድረስ የሄዱት ለማና ጠይባ፣ ልክ በድርጅቱ ግምገማ ሲደረግባቸው ከሰባት ወር በፊት የተቀዳን ንግግር ለፅንፈኛ የአማራ አክቲቪስቶች Leak አደረጉ።”
*** ሽመልስ አብዲሳ ይሁን ዓብይ አህመድ “ጀውር አባ ሜንጫ ወንድማችን አጋራችን፤ መካሪችን ዋ! ተተኪያችን በእሱና በዓይን ቀልድ የለም” ሲሉ ነበር እንጂ ስለወደመ ንብረትም ይሁን ስለተጨፈጨፈው ህዝብና ተዘቅዝቆ ለተገደለው ዜጋ ትንፍሽ አላሉም… እንዲያውም የሀገሪቱ
ጠ/ሚ መሆኑ የሠራዊቱ አዛዥ መሆኑን ዘንግቶ ወረዳና ቀበሌ አላስተዳድርም እራስህን ጠብቅ ይልሃል!? ጥቃት ከመፈፀሙ ቀድመው ራስመጠበቂያ መሳሪያህን ያስፈቱሃል…መጓጓዣ መኪና ክብሪትና ጋዝ ያቀርባሉ.. ፖሊስና ጸጥታ አስከባሪው የመከላከል ትዕዛዝ አልደረሰንም ሲሉ ቆመው በድሃ ዕንባና ደም ይዝናናሉ! ሲበረታም መሳሪያቸውን ለወንበዴ ያውሳሉ… በዚያው ሹፈት የተበረታታ መንጋ መዝረፍ፡መድፈር፡ ማረድ፡ ማቃጠል፡ የዘርማፅዳቱን ዘመቻ ቀጥሎበታል።
“ዋሽቶ ማስታረቅ” እንደሚባለው አቶ ሽመልስ የተናገረውን ተናግሮ ድርጅቱና የክልሉ መንግሥትን ከእንዲህ ያለ ፅንፈኛ ቡድን መታደግ በመቻሉ ሊያስመሰግነው ይገባል።በክልሉም ሆነ በሀገር ደረጃ አሸናፊ ሆነው እንዳይወጡ ለማድረግ በሚል ስለሆነ “እሰይ አበጀህ” ብዬዋለሁ”
** “ዋሽቶ ነፍስ ማዳን” ሲባል ተሰምቷል! አስታራቂው ውሸታም ከሆነ ምኑን አስታረቀው!? አዋለቀው እንጂ… ዓይኔን ግንባር ያርገው ካልሆነ አሁን ብልፅግና ብልግና ሆኖ ሕዝብ ንብረትና ሀገር ሲፈርስ ፅንፈኛው ቡድን የሚሰራውን እየሰራ ያለውን እና ሊሰራ ያቀደውን ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ የአፓርታይድ ወይም አክራሪ ወራሪ የካድሬ ሥልጠና ላይ የተነገረን እውነትእንጂ ከማንም ጋር የሚነካካ አደለም። ለማስተባበል የተሄደበት መንገድ በራሱ ፅንፈኛና ሽመልስ እንዳለው ” የገባውን አሳምነሀ ያልገባውን አወዛግበህ ትልምህን ማሳካት!” ለምን ተምታታበት (ተወዛገበ) ብለህ አትጠይቅ!።”
ልክ እንደዚህ ፅሑፍ ግለሰቡ የፖለቲካ ተንታኝ ነውና ያመነውን አሳምን ያልገባውን ግራ አጋባው ትወና ማለት ነው። ከሚያጠፉት ሰዎች ይልቅ ጥፋትን የሚያጣፉት ሰዎች አጭቤ እጅግ አደገኞች ናቸው። አራት ነጥብ። ሰዩመ ብልጥ’ገና !
Natnael says
እንደ ስዩም ዓይነት አድርባይ ባንዳ በዚህ ምድር አላየሁም። ሽመልስ በአማራ ላይ ሲቀልድ የመጀመርያው አይደለም። መስቀል አደባባይ ላይ የተናገረውን ማስታወስ በቂ አይደለምን? ቆይ እውነትን መደበቅ ይቻላል? ይጠቅማል? እስከመቼ?