It has been nearly two months since 18 University students who were on their way back home from Dembi Dolo University were kidnapped, in Oromia region. Among these, 14 are female students. Different sources including one of the captives escaped confirmed this fact in her interview with BBC Amharic. In early of December, some of the victims contacted their families through phone in the first week of the kidnapping. However, ever since no one heard from them. Some parents stated that even if they … [Read more...] about Ethiopia should rescue the Kidnapped Female University Students in Oromia region
Opinions
የኔ ሃሳብ
ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ማን ነው?
ጥሪ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ከኤርትራ መጥቶ ህወሓት መቀላቀሉ በአብዛኛው የወይኔ በተለይ ነባሩ ታጋይ የሚታውቀ ሃቅ ነው፤ እሱም ራሱ የሚናገረው ሃቅም ጭምር ነው። ደብረፅዮን ወደ ህወሓት የተቀላቀለው በመጨረሻው 1974 ዓም አካባቢ ነው። በወታደራዊ ማሰልጠኛ የክፍሉ ዋና መሪዎች በተለይ ሶስቱ መሪዎች የነበሩ ስማቸው አልጠቅስም ይህን አረጋግጠዉታል። ተወልዶ ያደገው ትምህርቱም የተማረው ኤርትራ ውስጥ ነው። ትግራይ ትውልድ ቦታዬ ነው ቢልም ይህም አሻሚ ነገር አይሆንም!! የነገሩ ፍሬ ግን ኤርትራ አድጎ የጀብሃ ታጋይ የነበረው ትግራይና ህዝብዋን መምራት ይችላል ወይ? ነው፤የትግራይ ህዝብ ማንነት ፍፁም የማያውቅ ሰው!! ይህም የትግራይ ህዝብ ጥያቄ መሆን ያለበት ነው፤ ቀደም ሲልም በኤርትራውያን መሪዎች ትግራይ ስትመራ ቆይታለች፤ ሃለቃ ፀጋይ በርሄ አባይ … [Read more...] about ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ማን ነው?
ዜግነትን መቀየር በተመለከተ አንዳንድ ነጥቦች
ባይሳ ዋቅ-ወያ ከጥቂት ወራት በፊት ስለ አንዳንድ የውጭ አገር ዜግነት ከነበራቸውና በዶ/ር ዓቢይ ጥሪ መሠረት ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ የኢትዮጵያ ዜጋ ባለመሆናቸው ያጋጠማቸውን አስመልክቼ አንድ ጽሁፍ በተለያዩ ሚዲያዎች አሳትሜ ነበር፡፡ ዛሬም ጥያቄው ወቅታዊ የሆነና ከሕግ አንጻር ትንታኔና ገለጻ እንደሚያስፈልገው ስለተረዳሁ በፊተኛው ጽሁፌ ላይ ተመርኩዤ ይህንን ጽሁፍ ለማቅረብ ወሰንኩ፡፡ ዓላማዬም ዜግነትን የመሰለ ለማንኛውም ሰብዓዊ መብት ቁልፍ የሆነውን ጉዳይ በቀላሉ እንዳናይና ይህንን በሕይወታችን ወሳኝ የሆነውን “ዜግነትን የመቀየር” እርምጃ ከመውሰዳችን በፊት ከሕግ አንጻር ማድረግ ያለብንና መከተል ያለብንን ሂደት ችግሩ ላጋጠማቸውና ለወደፊትም ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ ለሚፈልጉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን ሕጋዊ ምክር ለመስጠት ነው፡፡ ወደ ኢትዮጵያ … [Read more...] about ዜግነትን መቀየር በተመለከተ አንዳንድ ነጥቦች
እየተስተዋለ – ለኢትዮ 360 ተንታኞች!
አምስተርዳም (በቪቫ ምኒልክ) ለዛሬው ጽሁፌ መነሻ የሆነኝ በኢትዮ 360 በሰሞኑ የኢትዮጵያን መከላከያና ደህንነት ክፍል አስመልክቶ የቀረበው ውይይት እጅግ ስለ አስደነገጠኝ ነው። ከውይይት ጭብጥ እንደተረዳሁትም ከመከላከያና የደህንነት መስሪያቤት ከፍተኛ አመራሮች በደረሰን መረጃ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አገራችንን ለአረቦች አሳልፎ በመስጠት የእስልምና ሐገራት አባል ለማድረግ እየሰራ ነው የሚልና የምእራብ እዝን ወደ ወለጋ ያዛወረው የኦሮሞን ልዩ ሃይል ለማደራጀት እንዲመቸው ነዉ የሚል በጥላቻ ላይ ብቻ የተመሰረተው ክሳችሁን መሉ ለሙሉ የምቃውምበትን ነጥብ ከዚህ በታች በአጭሩ ዘርዝር አድርጌ ለማስተላለፍ እሞክራለሁ። የውይይት ሃሳባችሁ መነሻ ያደረጋችሁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ከሰይፉ ጋር ያደረጉት ዉይይት ላይ ስለ አረብ አገራት ለኢትዮጵያ በሚሰጡት የገንዘብ … [Read more...] about እየተስተዋለ – ለኢትዮ 360 ተንታኞች!
ኦፌኮ ከለዘብተነት ወደ ነውጠኝነት
ህግ ያልገዛውን ሀይል ይገዛዋል ዛሬ ጦርነቱ ግልፅ ሆኗል። ኦፌኮ መንግሥትን ምንም አታመጣም እስኪ የምታደርገውን አይሃለሁ እያለው ነው። ኦቦ መረራ በስተርጅና ዋልታ ረገጥ ሆነው ፈንድተዋል። ሀይማኖት ውስጥ ያሸመቁ መናፍቃን ባደባባይ ፖለቲካውን ተቀላቅለዋል። ነውጠኛው ጃዋር ራሱን እንደ አሜባ አራብቷል። ጦርነቱ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ ብቻ ላይ አይደለም ያጠነጠነው የሀገሪቱን መሰረት የመፈነቃቀል ስትራቴጂ ፊት ለፊት አንግቦ እንጂ። ይህ ሀገር ላይ የተመዘዘ ሰይፍ የቱንም እምነት አይምርም። ሀገር ሳለች ነው እምነት፣ ክብርም፣ ራሱ መኖርም። ማንም ራሱን ካላሞኘ በስተቀር፣ ሁሉም በሰላም በማይኖርባት አገር ውስጥ የብቻዬን የሰላም ደሴት እፈጥራለሁ ሊል የሚቻለው አይደለም። እነሆ ዛሬ አንዳች ስውር፣ አንዳች ያልተገለጠ ምስጢር የለም። ዕቅዱ በገሀድ … [Read more...] about ኦፌኮ ከለዘብተነት ወደ ነውጠኝነት
“እሾህ የሚወጋው የተከለውን ሰው ነው”
ታዬ ደንደኣ እሾህ የሚወጋው የተከለውን ሰው ነው። የኦሮሞ ተረት ነው። ተንኮል መልሶ ባለተንኮሉን ነው የሚጎዳው ለማለት ነው። ትላንት ደም ለመመለስ እንደምትታገል ተናገርህ ነበር። ትናንት በአንድነት እና በፍቅር የሚኖርን ህዝብ እምነት እና ብሄር ከፋፍለህ እንዲጠራጠር አደረግክ። እሳቱ ሲነሳ ደግሞ ሌላ ሰው ተጠያቂ አደረግክ። ራስህ የሰራኸውን ወንጀል ለሌላ ሰው ማላከክ ትናንት የለመድከው ነው። አሁን የእውነት ጊዜ ተቃርባለች። ለበርካታ ዓመታት በድራማ ከኦሮሞው ላይ ገንዘብ ሰበሰብህ። አሁን ግን ያን ጊዜ አልፏል፤ ድራማ አዘጋጅቶ የኦሮሞን ድጋፍ መጠየቅ ቀርቷል። ህዝቡ ያንተን አጀንዳ አውቋል። ሀበሻና ሚኒሊክ የአንተ ገበያ ናቸው። የኦሮሞ ድጋፍ ሲቀዘቅዝ ጠዋት ተነስተህ ሀበሻ እና ሚኒሊክ ብለህ ስድብ በመልቀቅ ገንዘብ ትሰበስባለህ። በዚህ መልክ የራስን ብሄር ታልባለህ። … [Read more...] about “እሾህ የሚወጋው የተከለውን ሰው ነው”
የሌለውን ፈላስፋ ፍለጋ ሳይሆን የጠፋውን ፈላስፋ ፍለጋ
ለዲ/ን ዳንኤል ክብረት የተሰጠ ምላሽ ስለ ፈላስፋው ዘረ-ያዕቆብ ሙህራንና ጻህፍት በሁለት ተከፍለው ኢትዮጵያዊ ነው፣ ኢትዮጵያዊ አይደለም በማለት ይከራከራሉ። ኢትዮጵያዊ ነው ከሚሉት ውስጥ ዋናዋናዎች ፕሮፌሰር ጌታቸው ኃይሌ፣ ዶ/ር ዳኛቸው አሰፋ፣ አብርሃም ደሞዝ፣ የኔታ አለማየሁ ሞገስ፣ ፈንታሁን ጥሩነህ፣ ብሩህ አለምነህ ይጠቀሳሉ። ኢትዮጵያዊ አይደለም ከሚሉት ውስጥ ዋናዋናዎች ኮንቲ ሮሲኒ፣ ዲ/ን ዳንኤል ክብረት፣ ፍስሐ ታደሰ፣ ሰሎሞን አበበ ቸኮል፣ ካሳሁን አለሙ፣ ታሪኩ ውብነህ ይገኙበታል። ሁለቱም ቡድኖች የሚያሳምኑም የማያሳምኑም ሃሳቦችን ይሰነዝራሉ። ፈላስፋው ዘርዓ ያዕቆብ ኢትዮጵያዊ አይደለም ከሚሉት ውስጥ ጥልቅ የሆነው እና የሌሎችን … [Read more...] about የሌለውን ፈላስፋ ፍለጋ ሳይሆን የጠፋውን ፈላስፋ ፍለጋ
አትወለድ ይቅር!
ሙሉውን ግጥም ለማንበብ እዚህ ላይ ይጫኑ። አትወለድ ይቅር Download “ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው። … [Read more...] about አትወለድ ይቅር!
እንዴት ከዘቀጥንበት ወጥተን ወደ ፊት እንራመድ?
ባለፉት ወራት ባገራችን የተከሰተውን አሳዝኝና ትርጉም የለሽ ግድያን በተመለከተ የተለያዩ የመንግሥትና የግል ሚዲያ ተቋማት በየፊናቸው ያስተላልፉ የነበረውን ዜና ከያለንበት ሆነን ስንሰማውና በቴሌቪዥን መስኮቶቻችን ስንመለከተው እንደነበር ይታወሳል። አዎ! ሰዎች በግልጽ በአደባባይ እየተቀጠቀጡ ሲገደሉ አይተን በእጅጉ አዘንን። እጅግ በጣም አሳዛኝና ምነው ኢትዮጵያ ውስጥ ባልተፈጠርኩ የሚያሰኝ የጭካኔ ጣራ የታየበት ዓመት! በወጣትነት ዘመናችን ሲነገረን የነበረውና እኛም እንደወረደ ስንጋተው የነበረው ኢትዮጵያዊ ጨዋነት፣ ባህሉን አክባሪና ከሁሉም ጋር ተስማምቶ በፍቅር ኗሪ፣ የደከመውን የሚያበረታታና ያዘነውን የሚያጽናና፣ ፈሪሃ እግዚአብሄርን በመላበሱ በአምላክ ፍጡር ላይ ጉዳትን የማያደርስ ቅዱስ ሕዝብ ወዘተ የሚባለው ባሕላዊ እሴቶቻችን ወዴት እንደተነኑ በበኩሌ አልገባ ካለኝ ውሎ … [Read more...] about እንዴት ከዘቀጥንበት ወጥተን ወደ ፊት እንራመድ?
ኢሕአፓ ለምን ተከፈለ? ዛሬስ ምን መደረግ አለበት?
በዚህ ርዕስ አጭር ጽሁፍ መፃፍ ከባድ ነው፡፡ ኢሕአፓን ያህል አንጋፋ ድርጅት ለመከፈል ብዙ ውጣ ውረድ፣ ውይይት፣ ንትርክ፣ ተደርጎበት በወቅቱ የነበሩትን አባላት አሳዝኖ የተከሰተ ሂደት ነው፡፡ በኢሕአፓ ታሪክ ተወደደም ተጠላ ይህ የመከፈል ጉዳይ በመጽሐፍ መልክ እንኳ ቢቀርብ እንዴት ነፃ ሆኖ ይቀርባል? የሚለው ይፈታተናል፡፡ ያም ሆነ ይህ መፃፉ አይቀርም፡፡ ለምን ተከፈለ? እንዴት ተከፈለ? ዋናው ምክንያት ምንድነው? ሂደቱስ? ኢሕአፓን ያህል ተመክሮ ያለው ፓርቲ እንዴት የቅራኔ አያያዝ ጥበቡ፣ ዕውቀቱ አነሰውና ለዚህ አሳፋሪ ድርጊት እጁን ሰጠ? ሂደቱ ከተከሰተም በኋላ መከፈሉን የሰሙ ደጋፊዎቹ፣ የቀድሞ አባላቱ እንደገና አንድ ለማድረግ ያደረጉት ጥረት ምነው ሳይሳካ ቀረ? ወዘተ. መልሱ እንኳንስ ሀገር ቤት ላሉት የኢሕአፓ የቀድሞ አባላት፣ ደጋፊዎችና ቤተሰቦች ሌሎችም ይቅርና ሲከፋፈል … [Read more...] about ኢሕአፓ ለምን ተከፈለ? ዛሬስ ምን መደረግ አለበት?










