የውሃ ሃብት ባለሙያ ነኝ፤ የግድቡ ጉዳይ ቀጥታ ከሙያዬ ጋር ባይገናኝም እንደዜጋ ሁኔታውን በቅርብ እከታተላለሁ፤ ፖለቲካንም እንዲሁ። የዋዜማን ሰዎች ዋዜማ ሳትሆኑ ነው የማውቃችሁ፤ ካገር ከመውጣታችሁ በፊት ማለቴ ነው። የማውቃችሁም በግል ሳይሆን እንደማንኛውም የሚዲያ ተጠቃሚ ነው፤ ስለዚህ እናንተ አታውቁኝም። አሁንም ዋዜማን እከታተላለሁ። ከዳያስፖራ ከሚመነጩት የዜና ዘገባዎችና መረጃዎች የእናንተ በተሻለ መጠን ተዓማኒነትና ሥርዓት የያዘ ነው ብዬ ስለማምን አነባችኋለሁ። “ኢትዮጵያን ቋሚ ባለዕዳ የሚያደርገው የህዳሴ ግድብ ስምምነት ላይ መንግስት የመፈረም ፍላጎት እያሳየ ነው” በሚል ርዕስ ያወጣችሁትን ዘገባ አንብቤዋለሁ። ዘገባው እንደሚለው ለረጅም ጊዜ የተጠበቀውን ሰነድ ስምምነት እንድትፈርም ኢትዮጵያ ግፊት እየተደረገባት እንደሆነ፤ ይህም “ኢትዮጵያን ቋሚ የውሀ ባለ እዳ … [Read more...] about ለዋዜማ ሬዲዮ – የህዳሴውን ግድብ ዜናችሁን ላስተካክልላችሁ
Opinions
የኔ ሃሳብ
ካድሬውና ገጣሚው
ሁለትም ናቸው። በግብ ግን የሚለያቸው የለም። ያን ጊዜ በአካል ላይተዋወቁ ይችሉ ይሆናል። በመንፈስ ግን የአንድ እናት ልጆች ናቸው። ትላንት ገጽ ለገጽ ሳይገናኙ፡ በስምም ሳይተዋወቁ በአንድ ካምፕ ለአንድ ሰፈር ሲጫወቱ ነበር። በመሃል መንገዳቸው ተለያየና በየፊናቸው ህይወትን ቀጠሉ። አንደኛው የህወሀት ቃለቀባይ ስጋጃ አንጣፊ ሆኖ ተከሰተ። ሌላኛው በኪነጥበብና መዝናኛ መድረኮች የጭቃ ውስጥ እሾህ ባህርይ ተላብሶ ብቅ አለ። ነገ እንደሚገናኙ ላያውቁ ይችሉ ይሆናል። አንድ ቀን የመንፈስ ጥምረታቸውን በአካል ተገናኝተው የሚያጠናክሩበት ጊዜ እንደሚኖር ሀገር ቤት ሳሉ ላያውቁት ይችሉም ይሆናል። የባህርይ አምላክ፡ በመንፈስ ያጣመራቸው ጌታ ፍቃድ ሆኖ ግን ሳያውቁት በባህር ማዶ ተገናኙ። በአካልም በመንፈስም ተቀራረቡ። በየግል በልባቸው የተከመረውን የጥላቻና የእኩይ መንፈስ በጋራ … [Read more...] about ካድሬውና ገጣሚው
ፕሮግራም አልባ “የሕዝብ አደራ” ተሸካሚዎች
ባላፈው ሳምንት “ከዘቀጥንበት ወጥተን እንዴት ወደ ፊት እንራመድ?” በሚል ርዕስ ያቀረብኩት ጽሁፍ በተለያዩ የሚዲያ ገጾች ላይ ከታተመ በኋላ፣ በቅርጽ የተለያዩ በይዘት ግን የሚመሳሰሉ ብዙ አስተያየቶች ከተለያዩ አቅጣጫዎች ደርሰውኝ ይዘታቸውን ከገመገምኩ በኋላ ያነሳሁት ጉዳይ ተጨማሪ ትኩረት የሚያስፈልገው መስሎ ስለታየኝ ይህንን ተከታይ ጽሁፍ ለማሳተም ወሰንኩ። በዚህ ጽሁፌ ሁለት ቁም ነገሮችን ማለትም “ሕዝባዊ አደራና” “የፖሊቲካ ድርጅቶች ፕሮግራም ግልጽ አለመሆንን” በተመለከተ አንዳንድ አስተያየት ሰጥቼ ሌሎችም የየበኩላቸውን አንዲያዋጡ ለመጋበዝ እሻለሁ። የኔ ሃሳብ ብቻ ትክክል ነው ከሚለው ፊውዳላዊና ኋላ ቀር አስተሳሰብ ተላቅቀን በየበኩላችን የሚሠማንን ወደ ውይይት መድረኩ ካመጣን አንድ ታላቅ ታሪካዊ እርምጃ የወሰድን መሆኑን አውቀን ሁላችንም እንድንካፈልበት ከወዲሁ ለማሳሰብ … [Read more...] about ፕሮግራም አልባ “የሕዝብ አደራ” ተሸካሚዎች
የኢትዮጵያ ጣምራ ፌደራሊዝም ተቋም
ኢትዮጵያ ወደ ፍጹም ህብረት! Towards a Perfect Union! ቀን 1/27/20 የኢትዮጵያ ጣምራ ፌደራሊዝም ተቋም የመጀመሪያ ሰሚናሩን አጠናቀቀ! የኢትዮጵያ ጣምራ ፌደራሊዝም ተቋም (DFIE Dual Federalism Institute for Ethiopia) በ January 18, 2020, በኢትዮጵያ ኤምባሲ አዳራሽ ውስጥ ክቡር አምባሳደር ፍጹም አረጋን ጨምሮ የተለያዩ የፖለቲካና ሲቪክ ድርጅት ተወካዮችና ምሁራን በተገኙበት የአንድ ቀን ሙሉ ሰሚናር አድርጓል። በዚህ ሰሚናር ላይ ለኢትዮጵያ ተብሎ የተዘጋጀውን አዲስ ቅርጸ መንግስት (Government Structure) አስተዋውቋል። ይህ አዲስ ቅርጸ መንግስት የኢትዮጵያ ጣምራ ፌደራሊዝም ይሰኛል። በዚሁ እለት የኢትዮጵያውያንን ህብረት ታሪካዊ ጉዞ በመገምገም ህብረታችንን ወደ ፍጹም ህብረት ሊያደርስ … [Read more...] about የኢትዮጵያ ጣምራ ፌደራሊዝም ተቋም
ሴት ልጅ በሽፍታ እጅ ወድቃ የሚተኛ ጎን የለኝም
ከሃምሳ ቀናት በላይ በአጋቾች እጅ ያሉት እህቶቻችን ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ሆኖብናል። የአንድ ሃገር ህዝብ ከሁሉ በፊት የሚፈልገው ነገር ዋስትና ነው። ተማሪው፣ ነጋዴው፣ ገበሬው፣ ሰራተኛው ሁሉ ከመንግስት የሚጠብቀው ዋና ነገር ደህንነቱ እንዲረጋገጥለት ነው። የመንግስት ተቀዳሚ ተግባርም ይሄ ነው። ለውጥ በሃገራችን ጀመረ ካልንበት ማግስት ጀምሮ ከፍተኛ መፈናቀልና አለመረጋጋት ሃገራችንን እየናጣት ነው። ይህንን ችግር የለውጥ ባህርይ ኣድርገን የምናይ ካለን ስህተት ነው። የሰው ደም ሳንገብር ወደ ለውጥ የምናልፍበትን መንገድ ነው የምንሻው እንጂ ከዚህ በፊት በየለውጡ ያየነውን ኣይነት የኢትዮጵያውያን ስቃይ እንዲደገም አንሻም። በመሆኑም የለውጥ መሪዎች ቁጥር አንድ ስራ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ መሆን ኣለበት። ከሃምሳ ቀናት በላይ በእገታ ላይ የሚገኙት የሃገር ተስፋ … [Read more...] about ሴት ልጅ በሽፍታ እጅ ወድቃ የሚተኛ ጎን የለኝም
የኤርምያስ ለገሰ ቪዲዮዎች ፉከራ ሲጋለጥ
ኤርሚያስ ለገሠ ... ዶ/ር ዐቢይ ላይ ድብቅ የ3 ሠዓት ቪዲዮ አለኝ ማለቱን ተከትሎ ብዙዎች ለዶ/ር ዐቢይ የወገብ ቅማል ሆነባቸው እያሉ ሲጠይቁ … ገሚሱ ሲያሞግሱ፣ ገሚሱ ሲወቅሱ አየሁና እኔም የማውቀውን እውነት ላካፍላችሁ ወደድሁ። በነገራችሁ ላይ ዶ/ር ዐቢይ በቪዲዮ ማስፈራሪያ ሲደርስባቸው (ብላክ ሜል) ሲደረጉ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ በመሆ ጉዳዩን በጥልቀት ለመርመሬ ምክንያት ሆኖኛል። ከዛሬ ዓመት በፊት የኢሕአዴግ ሊቀመንበር ለመወዳደር ዶ/ር ዐቢይ በእጩነት በቀረቡ ጊዜ የቀድሞው የደህንነቱ ሹም ጌታቸው አሰፋም ዶ/ር ዐቢይ ላይ በድብቅ የተቀረጸ የድምጽና የምስል ማስረጃ አለኝ በማለት ዶክተሩን በማስፈራራት ቀዳሚው ሰው ሲሆን አሁን ደግሞ ዓመቱን ጠብቆ ኤርሚያስ ይሄን የቪዲዮ ጌም ይዞ ብቅ ብሏል። ሚስጥር በተወሰነ መልኩም ስለማውቅ እና የሀገሪቱን ፖለቲካ በንቃት ስለምከታተል … [Read more...] about የኤርምያስ ለገሰ ቪዲዮዎች ፉከራ ሲጋለጥ
Ethiopia should rescue the Kidnapped Female University Students in Oromia region
It has been nearly two months since 18 University students who were on their way back home from Dembi Dolo University were kidnapped, in Oromia region. Among these, 14 are female students. Different sources including one of the captives escaped confirmed this fact in her interview with BBC Amharic. In early of December, some of the victims contacted their families through phone in the first week of the kidnapping. However, ever since no one heard from them. Some parents stated that even if they … [Read more...] about Ethiopia should rescue the Kidnapped Female University Students in Oromia region
ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ማን ነው?
ጥሪ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ከኤርትራ መጥቶ ህወሓት መቀላቀሉ በአብዛኛው የወይኔ በተለይ ነባሩ ታጋይ የሚታውቀ ሃቅ ነው፤ እሱም ራሱ የሚናገረው ሃቅም ጭምር ነው። ደብረፅዮን ወደ ህወሓት የተቀላቀለው በመጨረሻው 1974 ዓም አካባቢ ነው። በወታደራዊ ማሰልጠኛ የክፍሉ ዋና መሪዎች በተለይ ሶስቱ መሪዎች የነበሩ ስማቸው አልጠቅስም ይህን አረጋግጠዉታል። ተወልዶ ያደገው ትምህርቱም የተማረው ኤርትራ ውስጥ ነው። ትግራይ ትውልድ ቦታዬ ነው ቢልም ይህም አሻሚ ነገር አይሆንም!! የነገሩ ፍሬ ግን ኤርትራ አድጎ የጀብሃ ታጋይ የነበረው ትግራይና ህዝብዋን መምራት ይችላል ወይ? ነው፤የትግራይ ህዝብ ማንነት ፍፁም የማያውቅ ሰው!! ይህም የትግራይ ህዝብ ጥያቄ መሆን ያለበት ነው፤ ቀደም ሲልም በኤርትራውያን መሪዎች ትግራይ ስትመራ ቆይታለች፤ ሃለቃ ፀጋይ በርሄ አባይ … [Read more...] about ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ማን ነው?
ዜግነትን መቀየር በተመለከተ አንዳንድ ነጥቦች
ባይሳ ዋቅ-ወያ ከጥቂት ወራት በፊት ስለ አንዳንድ የውጭ አገር ዜግነት ከነበራቸውና በዶ/ር ዓቢይ ጥሪ መሠረት ወደ ኢትዮጵያ ከተመለሱ በኋላ የኢትዮጵያ ዜጋ ባለመሆናቸው ያጋጠማቸውን አስመልክቼ አንድ ጽሁፍ በተለያዩ ሚዲያዎች አሳትሜ ነበር፡፡ ዛሬም ጥያቄው ወቅታዊ የሆነና ከሕግ አንጻር ትንታኔና ገለጻ እንደሚያስፈልገው ስለተረዳሁ በፊተኛው ጽሁፌ ላይ ተመርኩዤ ይህንን ጽሁፍ ለማቅረብ ወሰንኩ፡፡ ዓላማዬም ዜግነትን የመሰለ ለማንኛውም ሰብዓዊ መብት ቁልፍ የሆነውን ጉዳይ በቀላሉ እንዳናይና ይህንን በሕይወታችን ወሳኝ የሆነውን “ዜግነትን የመቀየር” እርምጃ ከመውሰዳችን በፊት ከሕግ አንጻር ማድረግ ያለብንና መከተል ያለብንን ሂደት ችግሩ ላጋጠማቸውና ለወደፊትም ተመሳሳይ እርምጃ ለመውሰድ ለሚፈልጉ ትውልደ ኢትዮጵያውያን አስፈላጊውን ሕጋዊ ምክር ለመስጠት ነው፡፡ ወደ ኢትዮጵያ … [Read more...] about ዜግነትን መቀየር በተመለከተ አንዳንድ ነጥቦች
እየተስተዋለ – ለኢትዮ 360 ተንታኞች!
አምስተርዳም (በቪቫ ምኒልክ) ለዛሬው ጽሁፌ መነሻ የሆነኝ በኢትዮ 360 በሰሞኑ የኢትዮጵያን መከላከያና ደህንነት ክፍል አስመልክቶ የቀረበው ውይይት እጅግ ስለ አስደነገጠኝ ነው። ከውይይት ጭብጥ እንደተረዳሁትም ከመከላከያና የደህንነት መስሪያቤት ከፍተኛ አመራሮች በደረሰን መረጃ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አገራችንን ለአረቦች አሳልፎ በመስጠት የእስልምና ሐገራት አባል ለማድረግ እየሰራ ነው የሚልና የምእራብ እዝን ወደ ወለጋ ያዛወረው የኦሮሞን ልዩ ሃይል ለማደራጀት እንዲመቸው ነዉ የሚል በጥላቻ ላይ ብቻ የተመሰረተው ክሳችሁን መሉ ለሙሉ የምቃውምበትን ነጥብ ከዚህ በታች በአጭሩ ዘርዝር አድርጌ ለማስተላለፍ እሞክራለሁ። የውይይት ሃሳባችሁ መነሻ ያደረጋችሁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ ከሰይፉ ጋር ያደረጉት ዉይይት ላይ ስለ አረብ አገራት ለኢትዮጵያ በሚሰጡት የገንዘብ … [Read more...] about እየተስተዋለ – ለኢትዮ 360 ተንታኞች!