• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ህወሓት ይፍረስ፤ ዕልቂት ሰባኪዎች ለፍርድ ይቅረቡ!

July 8, 2020 04:52 pm by Editor 1 Comment

“ሃጫሉን የገደሉት ነፍጠኞች ናቸው፤ መላው የኦሮሞ ህዝብ የምኒሊክን ሃውልት አፍርሰህ ወደ ቤተመንግሥት ገስግስ!” ይህንን የዘር ዕልቂት የተናገረው የዶ/ር ዐቢይ የለውጥ ቡድን እነ ጃዋር መሃመድን በቁጥጥር ሥር ከማዋሉ በፊት በሕወሃት የደም ገንዘብ የሚቀለበው ሕዝቅኤል ጋቢሣ አሜሪካ ቁጭ ብሎ ሕወሃት ባደራጀው ዲጂታል ሚድያ በመጠቀም ሲያውጅ ነበር።

“በደረሰን መረጃ መሠረት፤ የሃጫሉ ሁንዴሳ ገዳዮች ነፍጠኞ ሳይሆኑ ሥልጠናና ተልዕኮ ተሰጥቷቸው የመጡ ትግርኛ ተናጋሪ ኤርትራውያን ናቸው፤ እኔ በደንብ አውቃለሁ እነማን እንደገደሉት፤ ምን ዓይነት ሚሊተሪ ፐርሶኔል እንደተሳተፈም አውቃለሁ፤ ኢትዮጵያውያን እንኳን አይደሉም፤ ኤርትራውያን ናቸው” ይህን የተናገረው ደግሞ በጎጥ አስተሳሰብ እጅግ የጠበበው መርዘኛው ፀጋዬ አራርሳ ነው።

ፀጋዬ አራርሣ፤ ሃገር መምራት የማይችል ደካማ ነው፤ ምንም አያመጣም – እያለ በአደባባይ ሲንቀው የነበረው የዶ/ር ዐቢይ የለውጥ መንግሥት እነ ጃዋርን ጠራርጎ ለፍርድ በማቅረብ ሀገሪቱን ሲያረጋጋና መላው ሕዝብ ከጎኑ መቆሙን ሲያረጋግጥ በከፍተኛ ድንጋጤ ውስጥ ይገባል። ከአውስራሊያ የስደት ኑሮ በቅርብ ለፍርድ እንደሚቀርብ በመገመቱና ነገ ለእኔም አይቀርልኝም በሚል ስጋት ተውጦ ንፁሃን ዜጎች በዘር ማጥፋት ዕልቂት ካስጨፈጨፈና የሃገር ንብረት ካስወደመ በኋላ 360 ዲግሪ ተሽከርክሮ ትላንት ዕልቂት በሚሰብከው የሕወሃት ዲጂታል ሚድያ “ትግራይ ሚድያ ሃውስ” ቀርቦ የተናገረው ሌላ አሳፋሪ ጉድ ነው።

አበው “በአንድ እራስ ሁለት ምላስ” እንዲሉ፤ ይህ የፀጋዬ አራርሳ የመርዝ ንግግር ሕወሃት ለዘመናት ሲጠነስስ የኖረው የአማራና የኦሮሞ ግጭት አልሳካ ማለቱን ሲያውቅ ኢትጵያዊው በወንድሙ የኤርትራ ሕዝብ ላይ እንዲነሳ ያቀነባበረው ሌላኛው መሰሪ የሕወሃት ሴራ ዕቅድ መሆኑ ነው። ንግግሩን ከቪዲዮው እዚህ ላይ ማድመጥ ትችላላችሁ።

እንደ አፍሪካዊቷ ሀገር ሩዋንዳ በኢትዮጵያ ታላላቅ ብሄረሰቦች አማራ እና ኦሮሞ መካከል የዘር ዕልቂትን በማቀነባበር ሀገሪቷን ለማፍረስ የታሪካዊ ጠላታችንን ግብፅ ምኞትና ፍላጎት ለማሳካት ከሊቀ ሰይጣኑ የትህነግ/ሕወሃት የማፊያ ቡድን ጋር በጥምረት ሲንቀሳቀሱ በነበሩ ኃይሎች ላይ ከሰሞኑ የዶ/ር ዐቢይ አህመድ አስተዳደር ቆፍጠን ያለ እርምጃ መውሰድ መጀመሩ እጅግ የሚያስመሰግነው ነው።

ሃገሪቱን በቋንቋና በብሄር ከፋፍሎ የውሸት የጭቆና ትርክትንና የለበጣ እኩልነትን እየሰበከ፤ በአባይ ወንዝ ላይ ያላቸውን የበላይነት ለማስጠበቅ ተገንጣይ ቡድን አድርገው ጠፍጥፈው በመሰረቱት ግብፅ እና የአረብ ሃገራት የገንዘብና የጦር መሳሪያ ድጋፍ ትናንሽ ግዛቶችን በመፍጠር ኢትዮጵያን ለመበታተን የአንድነቱን ኃይል “ነፍጠኛ፣ ትምክህተኛና ጨቋኝ” ወዘተ የሚሉ ስሞችን በመለጠፍ፤ በዕለት ጉርስ እጦትና በእርዛት የሚንገላታውን ሀገር ወዳድ የአማራው ህዝብ ጥንታዊ ርስተ መሬቱን የዘር ማፅዳት ዕልቂት በመፈፀም የቻለውን ያህል ቆርሶ ወደራሱ በማካለል ግዛቱን ከ60 በመቶ በላይ ያሰፋው ሕወሃት ከጅምሩ የኢትዮጵያ ታሪካዊ ጠላት ለመሆኑ ዋናው ምስክር “ሥልጣን ከእጃችን ከወጣ ኢትዮጵያ ትፈርሳለች” እያለ በድፍረትና በንቀት ያሰማው የነበረው ቀረርቶ የአደባባይ ምስጢር ነው።

በሱዳን ድንበር አካባቢ የሚንቀሳቀሱ የሥልጣን ተቀናቃኝ ተቃዋሚዎቹን ለማጥፋት ሲል ብቻ፤ የኢትዮጵያን ለም መሬት ሳይቀር ከ12 ሺህ ሄክታር በላይ ቆርሶ ለሱዳን ገፀበረከት አድርጎ የሰጠው ሕወሃት ኢትዮጵያዊነት በደሙ ውስጥ አለ ለማለት ፈፅሞ ይከብዳል። ይህ ግፈኛ የማፍያ ቡድን ከሁለት ዓመታት በፊት በሕዝባዊ አመፅ ተገፍቶ ወደ መቀሌ ሲሸኝ “መግደል ሽንፈት ነው፤ ይቅርታ ማድረግና መቻቻል ብልህነት ነው” ሲሉ ተደጋጋሚ የአደባባይ ዲስኩር ሲያሰሙ ለነበሩት ጠቅላይ ሚኒስትር “እባክዎ! ሕወሃት የለየለት አምባገነን እና ሙሰኛ ቡድን ነው፤ ሥልጣን ዳግም ወደ እጁ ካልገባ ኢትዮጵያን ከማፍረስ ወደኋላ ስለማይል ይህን ቡድን ትጥቅ ማስፈታቱ ይበጃል” ሲሉ አያሌ ኢትዮጵያውያን ተማፅነዋቸው ነበር።

ሆኖም ሰሚ ጆሮ ባለመኖሩ ለ28 ዓመታት በዘረፉት የሀገሪቱ ሃብት በመላው ሀገሪቱ በብሄሮች መካከል ግጭትን እያቀናበሩ፤ የአያሌ ንፁሃን ደሃ ዜጎች ደም ዛሬም ድረስ እንዲፈስ፤ አብያተ ክርስቲያናትና መስጂዶች እንዲቃጠሉ ብሎም የግለሰቦችና የመንግሥት የልማት ተቋማት እንዲወድሙ ምክንያት ሆኗል። ዛሬም በአቋራጭ ሥልጣን ለመቆናጠጥና የበላይነታቸውን ለማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን፤ ከጠላት በሚሰፈርላቸው ረብጣ ዳረጎት የግብፅን ምኞት ለማሳካት ጭምር በኦሮሞ የተቃዋሚ ፖለቲካ ጎራ ስም ተደራጅተው ለዕኩይ ዓላማቸው መሳካት ከእነሱ ጋር መንግሥትን ለመገልበጥና ሃገሪቱን ለመበታተን ከበሮ የሚደልቁ ግለሰቦችን “የኦሮሞ ሕዝብ ጠላቶች” ሲል በጠንካራ የሰላ ሂስና ትችት በአደባባይ በተደጋጋሚ ሲወቅሳቸው የኖረውን ታዋቂውን ወጣት የነጻነት ታጋይና ድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን በመግደል፤ በኦሮሞ ሚድያ ኔትወርክና በትራይ ሚድያ ሃውስ “ነፍጠኛው ነው የገደለው፤ ምን ትጠብቃለህ? የምኒልክን ሃውልት አፍርሰህ! ነፍጠኛውን አጥፍተህ ቤተመንግስቱን ተቆጣጠር” ሲሉ እንደ ሕዝቅኤል ገቢሳ፣ ፀጋዬ አራርሳ፣ ጃዋር መሃመድና ሌሎችም የግብፅ እና ሕወሃት አጋፋሪ ደላሎችና የኢትዮጵያ ጠላቶች በግልፅ እንደ ሩዋንዳው የዘር ፍጅትንና ዕልቂትን በግልፅ አውጀው እንደለመዱት ለበርካታ ንፁሃን ሞትና ለንብረት ውድመት መንስኤ ሆነዋል።

የሃገር ጠላቶች ያሰቡት አልተሳካም። ስልጣን ናፋቂዎችም አፍረዋል። የግብፅ ከፋፋይ መሰሪ ፕሮፓጋንዳ ከሽፏል። እኩይ ምኞታቸው በኢትዮጵያውያን አንድነትና በዶ/ር ዐቢይ የለውጥ ኃይሉ አመራር ቆራጥ እርምጃ መክኗል። “እኛ ከተነካን ኢትዮጵያ ትፈርሳለች፣ የዓለም ፍፃሜ ይሆናል” አትንኩን የሹም ዶሮ ነን ሲሉን የከረሙት የአረብ ደላሎች እነ ከበቡሽ ጃዋር ዛሬ ከህግ በላይ አለመሆናቸውን መንግሥት በአደባባይ አሳይቷቸዋል። ትላንት ሰው አስገድለው ንፁሃንን ያለ ሃጢአታቸው እያሳሰሩ ሲሳለቁ የነበሩት እኩያን ዛሬ የእጃቸውን አግኝተዋል። ደካማ ነው ሲሉ የተሳለቁነት አመራር አሁን ላይ ጥርስ አውጥቶ እንደ አንበሳ እያነቀ ከጥልቅ ጎሬያቸው አንድ ላይ ሰብስቦ የፍርድ ችሎት አቁሟቸዋል።

ያሰቡት ሳይሆን እኩይ ድርጊታቸው የገባው የአማራ እና የኦሮሞ በአጠቃላይ አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብም ከዶ/ር ዐቢይ አመራር ጎን ተሰልፎ ሃገር በማዳኑ ተግባር ላይ እየተረባረበ ይገኛል። በውጭ ሃገር ተቀምጠው በሚከፈላቸው የደም ገንዘብ ህሊናቸውን ሸጠው በደሃው ወገናችን ላይ የዘር ዕልቂት ሲደግሱ የኖሩትን እነ ሕዝቅኤል ገቢሳ፣ ፀጋዬ አራርሳ፣ ብርሃነመስቀል አበበ፣ አሉላ ሰለሞን፣ ዳንኤል ብርሃኔ (አገር ውስጥ) እና ሌሎችንም በአፋጣኝ ለኢትዮጵያ መንግሥት ተላልፈው እንዲሰጡ አልያም በዓለምአቀፍ ችሎት ለፍርድ እንዲቀርቡ በማድረጉ ረገድም በጎ እንቅስቃሴዎች መጀመራቸውን አይተናል እሰየው የሚያስብል ነው።

የዶ/ር ዐቢይ መንግሥትም የኢትዮጵያንም ሆነ የራሱን ህልውና ለማስጠበቅ ይህ የመጨረሻ ዕድሉ ይሆናል። ይህን በእጁ የገባ እና በበቂ ማስረጃ የተደገፈ ሁነት ጊዜ ሳይሰጥ በህግ አግባብ ተግባራዊ ለማድረግ ህዝቡን አስተባብሮ መነሳት ይኖርበታል። ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በኢትዮጵያ ሰላምና መረጋጋት የሚሰፍነው ግን እንደ አሁን ቀደሙ በመግለጫ ጋጋታ አልያም “ሽብርና ዕልቂት የሚደግሱልን የምናውቃቸው ስልጣን ያጡ ኃይሎች ናቸው” እያሉ በመቆዘምና በመልመጥመጥ ሳይሆን እንደ አሁኑ ቆፍጠን ብሎ ሕወሃትን በማያዳግም እርምጃ ድባቅ መምታት ሲቻል ብቻ መሆኑ መታወቅ ይኖርበታል።

የሀገሪቱን ዜጎች በነጻነት የመኖርና የመንቀሳቀስ መብት ፍፁም በሚጻረር መልኩ ትንሽ ኮሽ ባለ ቁጥር በባህል ስም ዱላና ገጀራ አልያም የጦር መሳሪያ ይዞ አደባባይ ለተቃውሞ የመውጣት ድርጊትም ሆነ በየሰፈሩ ኢ-መደበኛ መንግስት ሆኖ “ከመሬቴ ለቀህ ሂድ ንብረትህን አምጣ” ወዘተ የሚሉ ግፎችና በህዝቦች መካከል ግጭትን የሚጋብዙ የወንጀል ትንኮሳዎችም ከጎረቤት ሶማሊያው አልሽባብ አልያም ከናይጄሪያው ቦኮ ሃራምና ከእስላማዊው አሸባሪ መንግሥት አይ.ኤስ አልያም ከአልቃይዳ ተግባር ቢከፋ እንጂ የሚተናነስ ባለመሆኑ መንግሥት በአፅንዖት ልዩ ትኩረት ሊሰጠውና በአፋጣኝ በህግ ሊያስቆመው ይገባል።

ወጣቱ ሃገር አልሚና ሥራ ፈጣሪ እንጂ በስሙ ገንዘብ የሚነግዱ የፖለቲካ ቁማርተኞችና ደላሎች መጠቀሚያ እንዳይሆንም በኢትዮጵያውያን ሙያተኞችና ባለሃብቶች እንዲሁም በመንግሥትም ዘንድ ብዙ መስራት ተገቢ ነው።

በአጠቃላይ የዶ/ር ዐቢይ የለውጥ ቡድን ሆይ!

ሕዝባዊ አመኔታን ለማግኘትና እማማ ኢትዮጵያ አንድነቷ ተጠብቆ ሳትፈራርስ በሰላም እና በብልፅግና የልጅ ልጆቻችን መኖሪያ እንድትሆን በጀመራችሁት ቆራጥ እርምጃ የሀገሪቱን አስከፊ ቀንጀኛ ጠላት ወያኔ በማጥፋት አንፀባራቂ ታሪክ ሰርታችሁ ስማችሁን በደማቅ የወርቅ መዝገብ ላይ እንድታሰፍሩ እንማፀናችኋለን ። አዎ ተደጋጋሚ ጥሪያችን ” ዶ/ር ዐቢይ ሆይ! ኢትዮጵያ ሳትፈርስ የሕወሃትን ማፍያ ቡድን በነካ እጅህ አፍርስ!!” የሚል ነው ልብ ያለው ልብ ይበል!

ኢትዮጵያ በክብር ለዘለዓለም ትኑር!!

ከታዛቢው


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣበ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, Opinions, Slider Tagged With: alula solomon, berhanemeskel abebe segni, daniel berhane, hezikiel gabissa, tigrai media house, tmh, tplf, tsegaye ararsa

Reader Interactions

Comments

  1. Yitbarek Kana says

    July 10, 2020 08:02 pm at 8:02 pm

    የአረፍተ ነገሮች ያለ ቅጥ መርዘም አንባቢዎ የሃሳብዎን ጅረት ተከትሎ ለመዝለቅ አዳጋች ይሆንበታል። ባንድ ረጅም አንቀጽ ውስጥ በጣም የበዙ ሃሳቦችን በሁለት አረፍተ ነገሮች ብቻ ማጨቅ ለርስዎ ቀልዎት ሊሆን ይችላል፣ አንባቢዎን ግን ያሰቃያል።
    ሃሳብዎ የሚነበብ መሆኑን አይተው መሻሻል ቢያደርጉ። ይህን ያልኩት ጊዜ ሰጥቼ ስላነበብኩት መሆኑን ያስተውሉ።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የእሁዱ ሰላማዊ ሰልፍ ተራዘመ፤ ተጠባቂው ዕርቅ ፍንጭ እያሳየ ነው February 3, 2023 05:17 pm
  • የብላቴ: የውጊያ ማርሽ ቀያሪ ሠራዊት መፍለቂያ ማዕከል February 3, 2023 10:06 am
  • በኢትዮጵያ 27 በመቶ የሚሆነው የአእምሮ በሽተኛ ነው ተባለ February 3, 2023 09:47 am
  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule