
የዚህች ሃገር ችግር የሴራ ፓለቲካ ነው። ጀዋር ሞሃመድ ዛሬ (ሰኞ) ለማየት የሚሰቀጥጥ አንድ ቪዲዮ ለጠፈ። በጣም አንጀት የሚበላ ጥቁርም ሆነ ነጭ ኦሮሞም ሆነ አማራ፤ የሰውን ልጅ እንደዛ በጭካኔ ማሰቃየት ከባድ የሰብዓዊነት ጥሰት ነው። የህግ ተጠያቂነት ደግሞ ግድ ነው፤ ግን ደግሞ ማነው ይህን ወንጀል የፈጸመው?
ዋናው ነገር ይህንን ወንጀል የፈጸመውን እና ያስፈጸመውን ለይቶ ለህግ ማቅረብ ነው። ቪዲዮው ልጁ ግፍ ሲፈጸምበት እንጂ ግፍ የፈጸሙትን አያሳይም ለምን ወንጀለኞችን መደበቅ አስፈለገ? ታስቦበት ስለተፈጸመ ነው።
በሴራ ከመዘፈቅ ይልቅ ወንጀሉን የፈጸሙትን በማጋለጥ ለህግ የበላይነት መተባበር ነበር። ግን ያንን ትተው ግፍ የተፈጸመበትን በማሳየት ህዝብን ማበሳጨት ነበር የተፈለገ።
ወንጀሉን የፈጸመውን በመደበቅ አማራ ኦሮሞን አሰቃየ ማለት የፖለቲካ ሴራ ነው። ነገሩ ድራማ መሆኑ በግልጽ ያሳያል። በሰው ጭንቅ እና ሰቆቃ ፖለቲካ ይሰራል።

የድራማው ባለቤት ደግሞ “Jawar” እራሱ ነው፤ የዚህ ጉዳይ አላማ ግልጽ ነው፤
1ኛው፤ አጀንዳ ማስቀየር ነው። የፖለቲካ ምረጡኝ “ጉማ እና ዲቃላ” ከሽፏል። “ጂርቱ እና ጂራ” የሚለው መፈክርም ተበላሽቷል። የጠባቂዎቼ መነሳት ፖለቲካም ውሃ አላነሳም። ስለዚህ አዲስ ኦሮሞን ስሜት የሚያነሳሳ አጀንዳ ማምጣት ያስፈለገው።
2ኛው፤ ኢትዮጵያ ወደ ዴሞክራሲ የምታደርገውን ጉዞ ማቆሸሽ ነው። ብዙ የአለም ሃገር መሪዎች አዲስአበባ ናቸው። ሁሉም ኢትዮጵያ ያለችበትን የሽግግር ጊዜ ትልቅ ቦታ ሰጥተውታል፤ ይህ የኢትዮጵያን ተቀባይነት ያሳድጋል። ይህንንም ለማቆሸሽ ነው ይህን ዘግናኝ ነገር ማምጣት ያስፈለገው።
3ኛው፤ ኢትዮጵያን ማፍረስ ነው። ማሳያውም በቅርቡ የአማራ ክልል ተማሪዎች በደንቢዶሎ መታገት ተነገረ። ኦሮሞ አማራን አገተ ሲባል ነበር። ዛሬ ደግሞ የአማራ ፖሊሶች ድሬዳዋ ላይ ኦሮሞን እያሰቃዩ ነው ብሎ ለጠፈ። ይህ ኦሮሞ እና አማራን የማባላት ከዩኒቨርስቲ ተማሪዎች እርስበርስ ማገዳደል የቀጠለ አጀንዳ መሆኑ ነው። ኢትዮጵያ ለማፍረስ ነው ይህ ሁሉ።
ወያኔ የሃውዜንን ህዝብ በእቅድ አስጨርሶ የትግራይን እና የአለምን ድጋፍ አገኘ። ዛሬ ውጪ የሚኖሩ ኦሮሞችን ደጋፍ ለመሸመት የወያኔን ተሞክሮ ወሰደ። ይህ መንገድ ዛሬ አያዋጣም።
ጃዋር በቀደም ተከበብኩ በማለት የ97 ንጹሃንን ህይወት አጥፍቷል። ይህ የኖቤሉን ድል በደም ለመቀባት የተደረገ ነበር። ዛሬ ደግሞ አጀንዳ ለማስቀየር እና ህዝብን ለማባላት ቪዲዮ በማዘጋጀት ለቀቀ። መንግስት በጣም ነው የታገሰው።
ከዚህ በላይ በህዝብ ደም እና ስቃይ መነገድ መቆም አለበት። ተጠያቂነትም ይመጣል። እንደ ትናንቱ በንጹሃን ደም እና ስቃይ በመጫወት GoFunDMe መክፈት የለም። ወንጀል የፈጸመም ያስፈጸመም ተይዞ ለህግ ይቀርባል። ምርመራም ተጀምሯል።
ሰብዓዊ መብት የህግ የበላይነት!
ታዬ ደንደአ
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።
ቀደሙኑ የሰብዐዊ መብት በማስከበሩ ረገድ የፍርድ ተቋማት ትክክለኛ ስራ ሰርተው ቢሆን ኖሮ የነጭ ሸሚዝ ከላይ የውስጥ ካናቴራ የሸተተ ሌቦች አገራችንን በሌብነት ሙያቸው በላዋረዷት ነበር አሸዋ ማሽላ ብሎ ሲሸጥ የነበረ ሌባ አገር ሲሰጠው ይምራል ወይ ቢባል ሊሞቱ የደረሱ ሌቦች አሁን ለፍርድ ቀረቡ ኣልቀረቡ ትርጉም የለውም የዘረፉት ግን ወደ መንግስት ካዝና ይግባ። የተሰረቀ ሐብት በውጭ በውሽሞችና በልጆቻቸው በየአገሩ ተበትኖ ይገኛልና ሌባ በአደባባየሰ ከማዋረድ በቀር ሌላ ፍርድ ኣያስፈልገውም። ሌቦቹን በአደባባይ ከሰረቁት ነገረሰ ጋር በአደባባይ ማጋለጠሰ እራሱ የሞራል ውድቀትና ኪሳራ ነው። ኂሊናወሰ የደነዘዘን ሌባ በፍርድ ቤት ለመቅጣት መነሳት የአገር ሐብትን ለፍርድ ቤት መባከን ነው። መጀመሪያ ሐብታቸውን መውረስ ይቀድማል ከዚያ በመረጃ ሐብታቸው ምንጭ ከየት እንደሆነ ይጣራ።
“ወያኔ የሓውዘን ሕዝብ በዕቅድ ኣስጨርሶ የትግራይንና የዓለም ድጋፍ ኣገኝ” የምትለዋን በኢትይጵያ በተለይ ደግሞ በኣማራ ፖለቲከኞች በተደጋጊሚ ስትትረክ እንሰማለን።
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የታሪክ ክህደትና ሌብነት የተለመደ ነው።
ኣንድ ከፍተኛ ባለስልጣን እንደዚህ ዓይነት የሕዝብን ቁስል የሚጭር ነውረኝ መግለጫ ሲሰጥ፡ ለትግራይ ሕዝብ ስድብ ብቻ ሳይሆን መራር ሓዘን ነው። ትናንት በኛ ዘመን የተፈጸው የህዝብ እልቂት፡ ሓሰት ነው ኣልተፈጸመም፡ ወይም ሴራ ነው ብሎ ማለት፡ በሽዎች ደም መቀለድ ነው። የትግራይ ሕዝብ የከፈለው መስዋእት ማንቃሸሽ ነው።ኢትዮጵያ እንደ ሓገር የት እንደሚያደርሳት እናያለን። ኣገረቱ በታሪክ ሌቦች እየተመራች ነው ልበል!
በጣም ያሳዝናል፡ እል
በጊዜው ለገበያ በተሰበሰበ ህዝብ መሀል የታጠቀ የወያኔ ሰራዊት እንዲገባ ተደርጓል፡፡ በመቀጠልም ወያኔዎች ደርግ ውስጥ በሚገኙ ሰዎች አማካኝነት ከደርግ የደህንነት ክንፍ መረጃ እንደመጣ በማስመሰል ለአየር ሀይል አዛዦች ይሄ መረጃ እንዲደርስ አድርገዋል፡፡ ደርግም ጠላቴን ገበያ ላይ አገኘሁት ብሎ ጀት ሲልክ፡ ወያኔ ደግሞ ካሜራ ይዛ እየጠበቀች ነበር፡፡ ይሄ ከሆነ አንተን ያሳዘነህ፡ ፓለቲካ አልገባህም ወይም አልበሰልክም ማለት ነው፡፡
የሃውዜንን ሚስጥር ያወጣው ማንም አይደለም: ከትግራይ ተወላጁ የህወሃት ነባር ታጋይ ገብረመድህን ኣርኣያ እንጅ:: ታዲያ አማራ ላይ ማላክክ ምን አመጣው? ከሃውዜን የቀጠለው እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል የሚለው የህወሃት የሴራ ፖለቲካ ተከታታዩ ድራማ ካልሆነ በስተቀር:: የቂልነት ገደብ ከሌለው በስተቀር: የኢትዮጵያ ህዝብ ስለህወሃት ያለው ግንዛቤ ከሩብ ክፍለዘመን በላይ ያስቆጠረ ስለሆነ ወድቆ መንፈራገጥ አጉል መላላጥ ነው:: የትግራይ ህዝብም አሁን አንተ የምታላዝነውን ጥቁር ውሸት በግርድፋ የሚያኝክ አይመስለኝም:: ከሆነ ግን ራሱን መልሶ ግብር የሚያስከፍለው መሆኑን ለማወቅ ነቢይነትን አይጠይቅም:: ገብረመድህን ኣርአያ አልሞተም አልታመመም በተንቀሳቃሽ ምስልም ተቀርፆ አለም ያየውና ለወደፊቱም የሚያየው የህወሃት አንዱ ጥቁር ታሪክ ነው:: የሙታን ቤተሰቦችም አንድ ቀን ህወሃትን ለፍርድ የሚያቀርቡበት መረጃ ስለሆነ እንዲሁ በቀላሉ ወደ አማራ በማላከክ የሚዘጋ ፋይል አይመስለኝም::