• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራል፥

March 7, 2020 11:24 pm by Editor 2 Comments

ኢትዮጵያ ስንት ልጆች ወለደቸ፤ ስንቱን አስተማራቸ፤ ስንቱን አቋቁማ ለአቅመ ዓዳም አበቃች፤ ስንት ጉድስ ተሸከመች። ቆጥረን ስለማንዘልቀው ቤቱ ይቁጠረው ብለን ብናልፈው ይበቃል። ብዙ ጉድ እንደተሸከመች ብናውቅም ብዙ ልጆቿ ሸክሟን ለማቅለል፤ ችግሯን ለመቅረፍ፤ እድገቷን ለማፋጠን ብዙ ጥረውላታል። በእውቀታቸው፤ በጉልበታቸውና በሃብታቸው ባቻ ሳይሆን ሕይወታቸውን ጭምር ገብረውላታል፤ እየገበሩም ይገኛል።

በአንፃሩ በሃብቷ ተምረው ስሟን ያጎደፉ፤ ሕልውናዋን የተፈታተኑ ከሃዲዎች መኖራቸውን ስናይ እናዝናለን። እነዚህን የመሰሉ ልጆቿ ሃገሪቱን አመድ አፋሽ አርገዋታል። ይህ የቅርብ ጊዜ ክስተት ብቻ ሳይሆን በሶስት ሽህ ዘመን ጉዞዋ ሁሉ ሲከሰት የኖር ለመሆኑ ታሪክ ይነግረናል።

ያአሁኑን ከጥንቱ ለየት የሚአደርገው ያለንበት ሃያ አንደኛው ክፍለ ዘመን መሆኑ፤ ልጆቿ ዘመናዊ ትምህርት ያላቸው፤ ዓለም በቴክኖሎጂ ረቆ ህዋ ላይ የተንሳፈፈበት፤ ሃገራችን ሳተላይት ወደ ጠረፍ የላከችበት ዘመን ላይ መሆኑን ስናይ ቁጭታችን ይበረታል። ከታሪክና ከስህተታችን መማር አለመቻላችን ይበልጥ ያስቆጫል።

በነዚህ መካከል ጥሩ ሲሰሩና ሲሞገሱ የማይወድላቸው፤ ፀዱ ሲባል ታጥበው ጫቃ የሚሆኑ አንዳንድ ምሁራን እናገኛለን። ለዚህ ዶክተር መረራ ጉዲና ጥሩ ማሳያ ናቸው። ዶ/ር ጉዲና በወያኔ ዘመን ብዙ የተንገላቱ የፖለቲካ ምሁር ናቸው። መለስ ዜናዊን በአመክንዮ የሞገቱ፤ በኢትዮጵያ አንድነት ላይ ድርድር የማያውቁ እንደነበሩ እናውቃለን።  

ላለፉት ሰላስ ዓመታት ባደረጉት የፖለቲካ ከርክርና እሰጥ አገባ ሕዝብ (ዘር፤ ቋንቋ፤ ሃይማኖት፤ ፆታ፤ ጎሳና ጎጥ ሳይለይ) አመኔታ የቸራቸው ምሁር ናቸው። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ግለትና ቅዝቃዜ መለኪያ ‘ተርሞሜትር’ እስከመሆን ደርሰዋል።  የፖለቲካው ክርክር ሲጦዝ፤ አስታራቂ ሃሳብ ሲጠፋ፤ ነገሮች መስቀለኛ መንገድ ላይ ሲደርሱ ዶክተር መረራ ምን አሉ ተብሏል። ለሐቅ ምስክርነት ማጣቀሻና ዋቢ እስከመሆን ደርሰው ነበር። በፓርላማ መለስን ያለፍርሃት ሞግተውታል። እንዲህ የሚሞግት ባይኖር አምባገነኖች ካደረሱብን እርግጫ በባሰ እንረገጥ ነበር።

ዶክተር መረራ እንዳሉን መለስ ሲሻው ማሞካሸት ሲናደድ ማበሻቀጥን ያውቅበታል።  ጥላቻው አይድረስባችሁና ሲአሞካሽም ሆነ ሲአጥላላ ግብረገብነት የጎደለው ነበር:: በጸያፍ አንደበቱ አዛውንት፤ ካህን፤ ሸህ፤ ሽማግሌ፤ ምሁር፤ ወጣት፤ ሴት ወንድ ሳይለይ በእፅ የሰከሩ ሰዎች በሚናገሩት ቋንቋ ሰውን ሲዘልፍ ቅር አይለውም። የዓይን ቀለም አላማረኝም ብሎ ሕዝብ የሚአፈናቅል፤ የዩንቨርሲቲ ፕሮፌሰሮችን የሚአባርር መሪ ይህን ባይል  ነበር የሚገርመው።

በአንድ ቃለ ምልልስ መለስ እንዴት ይጠሩዎት ነበር ተብለው ሲጠየቁ ዶክተር ጉዲና ፈገግታ፤ ቀልድና ፌዝ ተልይቷቸው ስለማያውቅ በሳቅ ታጅበው የሰጡት መልስ ‘ሃሳቤንና አስተያየቴን ሲወዱት ዶክተር መረራ ይሉኛል፤ በሃሳቤ ሳይደሰቱ ደግሞ አቶ መራራ’ እያሉ ይጠሩኝ ነበር ብለዋል።  

ከኦሮሙኛ ተናጋሪ ወንድሞቸ እንደተረዳሁት መረራ ማለት አስተዛዛኝ፤ ጉዲና ደግሞ እድገት ማለት እንደሆነ ገልጽውልኛል-ነን ሶቤ! መለስ ደስ ሲላቸው አስተዛዛኙ መረራ ሲከፋቸው ደግሞ ቆምጣጣው ወይም መራራው (bitter) እያሉ በገደምዳሜ ይሰድቧቸው ነበር ማለት ነው። ዶክተሩም የዋዛ ስላልሆኑ በመልስ ምት አሁንስ መንጌን መስለው ታዩኝ ይሏቸው እንደነበር ሰምተናል። በዚህ ደረጃ ባለሥልጣን የሚፈታተኑ ቅን ፖለቲከኛ ነበሩ።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዶክተር መረራ በሚናገሯቸውና በሚሰሯቸው ሁሉ መራራነታቸውን እየመሰከሩ ሲአልቅ አያምር እየሆኑ መጥተዋል። ተደብቆ የነበረው ገጽታቸው አደባባይ እየወጣ ግራ ተጋብተው ግራ አጋብተውናል። ከጽንፈኛ እና ከፀረ-ኢትዮጵያ ቡድኖች ጋር ህብረት ፈጥረው ተገቢ ያልሆነ ነገር በመናገር ሕዝብን እያስቀየሙ ይገኛሉ።

በተለይ የጃዋር ዜግነትን በተመለከተ እርስበርሱ የሚጣረስ አምክንዮቢስ ንግግራቸውን የሰማው ሕዝብ መረራ ምን ነካው እስከማለት ደርሷል። ጃዋር አሜሪካዊ ዜጋ መሆኑን እያወቁ የቀበሌ መታወቂያ ሰጠው በራሳቸው ስልጣን ኢትዮጵያዊ ዜግነት ሲአጎናጽፍ አገር ጉድ አለ። አሰራሩ በሕግ የሚአስጠይቃቸው መሆኑንም ዘነጉት። ጃዋር ኢትዮጵያዊ መልክ ስላለው ኢትዮጵያዊ ዜግነቱ የማይመለስበት ምክንያት እንደማይገባቸው ሲናገሩ አገር ተገረመ።

የጉድ አገር ገንፎ እያደር ይፋጃል ካልህነ በቀር መረራ ምርጫ ቦርድ፤ ብርቱካን እና የዜግነት ሁነት ኤጀንሲ ከሕግ ውጪ መስራት እንዳለባቸው ግፊት እያረጉ መሆኑን ሳያውቁት ቀርተው አይደለም። በቅርቡ ከዶክተር ዓብይ ፊት ቀረበው ስለጆርጆ ዖርዌል (George Orwell-84) ሁሉም እንስሶች እኩል ናቸው ግን ትቂት እንስሶች የበለጠ እኩል ናቸው ብለው ንግግር ሲአሳምሩ ሰምተናል። ዶክተር መረራ በዜግነት አመላለሱ ሂደት የጆርጅ ዖርዌል ሕግ እንዲፈጸም እየጠየቁ መሆኑን አውቀውት ይሆን። ለምን የሕግ የበላይነት ይከበር እያሉ  ሕዝባዊ ሰልፍ እንደሚጠሩ ግልጽ አይደለም።

ቀስበቀስ ከዶክተር መረራ ጉዲናነት ወደ ዶክተር መራራ ጉዲናነት መሸጋገር ጀምረዋል። ድፍድፍ ሲቀል ይንሳፈፋል፤ ምሁር ሲዘቅት ይመራልና አድብ ገዝተው ወላጆቻቸው ወዳወጡላቸው አስተዛዛኝ እድገት/ብልጽግና ስማቸው ቢመለሱ ለስብዕናቸውም ሆነ ለቀሪው ሕይወታቸው የሚበጃል። ካልሆነ እንደ ስልሳ ስድስቱ ጓዶቻቸው ወጣ ወጣ እንደ ሸንበቆ ተንከባለለ እንደሙቀጫ ብለን ጫንጮ እናሸፍታቸው።

ሰማነህ ጀመረ፤ ካናዳ ( stjtamrat@hotmail.com)


“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣበ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።

Print Friendly, PDF & Email

60

SHARES
Share on Facebook
Tweet
Follow us
Share
Share
Share
Share
Share

Filed Under: Left Column, Opinions Tagged With: Left Column

Reader Interactions

Comments

  1. ነፃ ሕዝብ says

    March 9, 2020 05:33 am at 5:33 am

    “አሁንስ መንጌን መስለው ታዩኝ ይሏቸው እንደነበር ሰምተናል” ይህቺ የእናንተ ቅጥያ ናት ፥ ይህንን የተናገሩት ዶ/ር ነጋሶ ጊዳዳ ነብሩ ፥ አፈሩን ያቅልልላቸውና ፥ በዚህም ገነት ዘውዴ የተባለችው ማይም የህወሃት እግር አጣቢዋ ለምን መለስን እንደዚህ አሏቸው በማለት እንዳለቀሰች በስማ በለው ሰምተናል ፥ ዶ/ር መራራው ይህንን አልተናገረም ፥ ተሳስታችሁ አታሳስቱ ፥ በተረፈ ስለመራራው ያቀረባችሁትም ቢሆን በጣም የተለሳለሰና በአሁኑ ሰዓት ሰውየው ፋሽስታዊ ባህርያት የተጠናወተው ስለመሆኑ ሰፋና ጠለቅ አድርጋችሁ ብታበጥሩት መልካም ነበር ።

    Reply
  2. አለም says

    March 11, 2020 09:48 pm at 9:48 pm

    ውድ ሰማነህ ጀመረ፣
    ወቅቱ ፓርቲዎች ተደራጅተው ለውድድር የሚቀርቡበት ወቅት መሆኑን የሰማህ አትመስልም።
    ፕሮፌሰር መረራ ከጃዋር ቀርቶ ካንተም ጋር ወግነው ቢደራጁ ችግሩ ምኑ ላይ ነው? አሸንፌ ፓርላማ
    ለመግባት የሚያስችለኝ ከነማን ጋር ብቀናጅ፣ ብደራደር ነው ብሎ ማቀድ ያለ ነገር ነው።
    በዚህ ላይ የምርጫ ኮሚሽን ያወጣውን ደንብ ማሟላት ግድ ነው።
    መረራን የምትፈልጋቸው ከአሳብህ ጋር እስከ ተስማሙ ብቻ ነው? ይኸማ ያስተዛዝባል።

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • የአየለ ጫሚሶ ቅንጅት ፈረሰ January 18, 2021 02:31 pm
  • ህወሓት ተሠረዘ!!! January 18, 2021 01:32 pm
  • ዓሲምባ፣ ሣልሳዊ ወያኔና ባይቶና ከመፍረሳቸው በፊት ማብራሪያ እንዲሰጡ ተነገራቸው January 18, 2021 01:00 pm
  • ቤተሰቦች አስከሬን መውሰድ እንደሚችሉ ተነገረ January 14, 2021 06:48 pm
  • ስብሃት፤ “ከሞትን ቆይተናል፤ … አሁን የቀብር ሥነ-ስርዓታችን” እየተፈጸመ ነው January 14, 2021 01:37 pm
  • “ተመልሰን እንነሳለን” ያሉት ህወሓቶች ተመልሰው ወደማይነሱበት ተሸኙ January 13, 2021 01:12 pm
  • አፋር ነፃ አውጪ (ኡጉጉሙን) ለመጠቀም የታቀደው የህወሃት ሤራ ከሽፏል January 13, 2021 01:10 pm
  • ህወሃትን ወደ ጅቡቲ ለማሻገር ሲሰሩ የነበሩ የአፋር ታጣቂዎች በሰላም ወደ ክልሉ ገቡ January 13, 2021 06:47 am
  • በታህሳስ ወር ብቻ ከ344 ሚሊየን ብር በላይ የኮንትሮባንድ ዕቃ ተያዘ January 13, 2021 06:10 am
  • የብልፅግና ፓርቲ ቀጣይ ፈተና ምን ሊሆን ይችላል? January 13, 2021 04:10 am
  • ለትምህርት እንዲሆነን January 11, 2021 01:20 pm
  • “ከተቀበሩበት የጃርት ጉድጓድ ነው ያወጣናቸው” መቶ አለቃ ስዩም ቱርቦ January 11, 2021 12:11 pm
  • የተደመሰሱና በቁጥጥር ሥር የዋሉ የወንበዴው አባላት ይፋ ሆነ January 7, 2021 01:16 pm
  • ዐቢይና መኮንኖቹ በመቀሌ፤ “ድሉ የመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ነው” December 13, 2020 02:36 pm
  • ወንበዴው ህወሓት ከ1.4 ትሪሊዮን ብር በላይ ዘርፎ በውጭ አገራት ባንኮች አስቀምጧል December 8, 2020 01:05 am
  • ማይካድራ – የትህነግ የዘር ማጥፋት ጥግ ቋሚ ምስክር December 8, 2020 12:57 am
  • የወልቃይት ጠገዴ እናቶች ሰቆቃ ሲታወስ December 8, 2020 12:50 am
  • የደብረጽዮን ዋሻ December 7, 2020 11:30 pm
  • ባለ ከዘራው ኮሎኔል December 7, 2020 05:15 pm
  • ሰላማዊ ሕይወት በማይጨው December 7, 2020 04:12 pm
  • ተጠርጣሪ የፌዴራልና የአዲስ አበባ ፖሊሶች የመያዣ ትዕዛዝ ወጣባቸው December 7, 2020 11:46 am
  • ከ3 ሺህ በላይ ተተኳሽ ጥይቶች በወልዲያ ጉምሩክ ሊያሳልፉ የሞከሩ 4 ግለሰቦች ተያዙ! December 7, 2020 11:18 am
  • ወንበዴዎቹ ይጠቀሙባቸው የነበሩ ተሽከርካሪዎችና የግል ሰነዶቻቸው ተያዙ December 7, 2020 10:50 am
  • ነጻነትና እኩልነት ፓርቲ በሶማሌ ክልል ተመሠረተ December 7, 2020 10:31 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2021 · Goolgule