ከሃምሳ ቀናት በላይ በአጋቾች እጅ ያሉት እህቶቻችን ጉዳይ እጅግ አሳሳቢ ሆኖብናል። የአንድ ሃገር ህዝብ ከሁሉ በፊት የሚፈልገው ነገር ዋስትና ነው። ተማሪው፣ ነጋዴው፣ ገበሬው፣ ሰራተኛው ሁሉ ከመንግስት የሚጠብቀው ዋና ነገር ደህንነቱ እንዲረጋገጥለት ነው። የመንግስት ተቀዳሚ ተግባርም ይሄ ነው። ለውጥ በሃገራችን ጀመረ ካልንበት ማግስት ጀምሮ ከፍተኛ መፈናቀልና አለመረጋጋት ሃገራችንን እየናጣት ነው። ይህንን ችግር የለውጥ ባህርይ ኣድርገን የምናይ ካለን ስህተት ነው። የሰው ደም ሳንገብር ወደ ለውጥ የምናልፍበትን መንገድ ነው የምንሻው እንጂ ከዚህ በፊት በየለውጡ ያየነውን ኣይነት የኢትዮጵያውያን ስቃይ እንዲደገም አንሻም። በመሆኑም የለውጥ መሪዎች ቁጥር አንድ ስራ የህዝቡን ሰላምና ደህንነት ማስጠበቅ መሆን ኣለበት። ከሃምሳ ቀናት በላይ በእገታ ላይ የሚገኙት የሃገር ተስፋ … [Read more...] about ሴት ልጅ በሽፍታ እጅ ወድቃ የሚተኛ ጎን የለኝም
bring back our sisters
“መንግሥት ታጋቾቹን ለማስለቀቅ ጥረቱን ቀጥሏል” – ኮሚሽኑ
በደንቢዶሎ ከወር በፊት የታገቱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ለአዲስ አድማስ የገለፀው የኢትዮጵያ ሠብአዊ መብት ኮሚሽን፤ መንግስት የተማሪዎችን ህይወት አደጋ ላይ በማይጥል መንገድ ከእገታ የማስለቀቁን ተግባር እንዲያከናውን ጠይቋል። “የተማሪዎቹ እገታ ጉዳይ በዋነኛነት የደህንነት አካሉ ኃላፊነት ነው” ያሉት የኢትዮጵያ ሠብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፤ የመንግስት የፀጥታ ሃይል ልጆቹን አደጋ ላይ በማይጥል መልኩ ከእገታው ማስለቀቅ መቻል አለበት ብለዋል። ኮሚሽኑ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን የገለፁት ኮሚሽነሩ፤ መንግስትም ተማሪዎቹን ለማስለቀቅ የሚደረገው ጥረት ሚስጥራዊነትን የጠበቀ በመሆኑ ብዙ ጉዳይ ይፋ እንደማይደረግ ጠቁመዋል። በዚህ የማስለቀቅ ጥረት እስካሁን የተገኘ ውጤት አለመኖሩን የገለፁት ኮሚሽነሩ፤ … [Read more...] about “መንግሥት ታጋቾቹን ለማስለቀቅ ጥረቱን ቀጥሏል” – ኮሚሽኑ
“ልጆቻችን ናቸው እኮ” ኮሚሽነር አበረ አዳሙ
“አንዳንዱ ነገር ድራማ ይመስላል” የኦነግ ቃል አቀባይ ቀጄላ መርዳሳ በህዳር ወር 2012 የመጨረሻ ሳምንት ከደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ ጋምቤላ ከተማ በመጓዝ ላይ ሳሉ በአጋቾች እጅ የገቡት ተማሪዎች ጉዳይ አሁንም አወዛጋቢ ሆኖ ቀጥሏል። እስከ አሁን ባለው መረጃም ተማሪዎቹ የአማራ ክልል ነዋሪ እንደሆኑ በመገለፁ አዲስ ማለዳ የአማራ ክልል የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙን አነጋግራለች። ኮሚሽነሩ ምንም እንኳን በጉዳዩ ላይ በቀጥታ ለመሳተፍ የህግ ገደብ ቢኖርባቸውም የታገቱት ተማሪዎች ከተያዙ እለት ጀምሮ የልጆቹን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተሉት አንደሆነ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። “የስልጣን ገደብ ቢኖርብንም ልጆቻችን ናቸው እኮ፣ መቶ በመቶ ቅድሚያ ሰጥተን እየተከታተል ነው” ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ዛሬ አመሻሹ ላይ ገልጸዋል። “ጉዳዩ የኛ ጉዳይ ነው፣ ነገር ግን መዋቅር … [Read more...] about “ልጆቻችን ናቸው እኮ” ኮሚሽነር አበረ አዳሙ