• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“መንግሥት ታጋቾቹን ለማስለቀቅ ጥረቱን ቀጥሏል” – ኮሚሽኑ

January 26, 2020 06:26 pm by Editor Leave a Comment

በደንቢዶሎ ከወር በፊት የታገቱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን ጉዳይ በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን ለአዲስ አድማስ የገለፀው የኢትዮጵያ ሠብአዊ መብት ኮሚሽን፤ መንግስት የተማሪዎችን ህይወት አደጋ ላይ በማይጥል መንገድ ከእገታ የማስለቀቁን ተግባር እንዲያከናውን ጠይቋል።

“የተማሪዎቹ እገታ ጉዳይ በዋነኛነት የደህንነት አካሉ ኃላፊነት ነው” ያሉት የኢትዮጵያ ሠብአዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ፤ የመንግስት የፀጥታ ሃይል ልጆቹን አደጋ ላይ በማይጥል መልኩ ከእገታው ማስለቀቅ መቻል አለበት ብለዋል።

ኮሚሽኑ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ መሆኑን የገለፁት ኮሚሽነሩ፤ መንግስትም ተማሪዎቹን ለማስለቀቅ የሚደረገው ጥረት ሚስጥራዊነትን የጠበቀ በመሆኑ ብዙ ጉዳይ ይፋ እንደማይደረግ ጠቁመዋል።

በዚህ የማስለቀቅ ጥረት እስካሁን የተገኘ ውጤት አለመኖሩን የገለፁት ኮሚሽነሩ፤ የእገታው ድርጊት በባህሪው ብዙ መረጃ የሚገኝበት ባለመሆኑ ግርታን መፍጠሩን ተናግረዋል።

ኮሚሽኑ በዋናነት ትኩረት አድርጐ የሚሠራው ተማሪዎቹ የሚለቀቁበትን ሁኔታ መሻት ላይ መሆኑን ያስረዱት ዶ/ር ዳንኤል፤ ኮሚሽኑም ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለ እንደሆነ ጠቁመዋል። “ጉዳዩ በጣም ልብ የሚሰብር ነገር ነው፤ ነገር ግን መንግስት ችላ ብሎ የተወው ጉዳይ አይደለም፣ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን እናውቃለን” ብለዋል – ኮሚሽነሩ።

መንግስት ከሚያደርጋቸው ጥረቶች ድርድር እና ሽምግልና አንዱ መንገድ መሆኑን ኮሚሽኑ መረዳቱንም ዶ/ር ዳንኤል ለአዲስ አድማስ አብራርተዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ “ሴታዊት” የተሰኘው የፆታ እኩልነት ላይ የሚሠራ አገራዊ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ባወጣው መግለጫ፤ በደንቢዶሎ የታገቱ ተማሪዎች በአስቸኳይ እንዲለቀቁ ጠይቋል።

የሚመለከታቸው የመንግስት አካላት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥተው እንዲሠሩም “ድርጅቱ” ጠይቋል።

ቀደም ብሎ የጠ/ሚኒስትር ጽ/ቤት ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ኃላፊ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ከታገቱት ተማሪዎች መካከል 22ቱ መለቀቃቸውን ገልፀው የነበረ ቢሆንም፤ ወላጆች “ተለቀዋል የተባሉ ልጆቻችንን ማግኘት አልቻልንም” ማለታቸውን ተከትሎ ጉዳዩ ሲያወዛግብ መሰንበቱ ይታወሳል። እስካሁን መንግሥት ውዝግብ ባስነሳው መረጃ ላይ ማብራርያም ሆነ ማስተባበያ አልሰጠም።

አዲስ አድማስ

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: News Tagged With: bring back our sisters, Left Column, olf, olf shine

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
  • “አዲሷ” ኢህአፓ፤ ከንፈሯን ቀለም የተቀባች አሳማ February 25, 2026 11:24 am
  • የተንጋደደው የገዱ መልስ February 6, 2026 03:05 pm
  • ሻዕቢያ “አክሱም ገብቶ ወጣቶች በጅምላ ሲረሽን ጸብ ተፋፍሟል …” February 4, 2026 01:15 pm
  • አደራ ጠባቂው የኢሉአባቦር ሕዝብ February 4, 2026 12:14 pm
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን January 28, 2026 09:56 am
  • በአሜሪካ ጥምር ዜግነት እንዲቀር ጥያቄ ቀረበ January 27, 2026 03:05 pm
  • “ከህወሓት፣ ከሻዕቢያ፣ ከግብፅ ሰዎች ጋር ሆኖ እንዴት የአማራን ጥያቄ ማስመለስ ይቻላል?” ኮሎኔል ፈንታው January 25, 2026 04:23 am
  • የኢትዮጵያ አየር ኃይል: ለአፍሪካ ሀገራት የመጀመሪያዎቹን የአየር ኃይል አብራሪዎች ያሰለጠነ ተቋም January 25, 2026 03:50 am
  • የአማረ ሪፖርተር እያደረሰ ያለው የብሔራዊ ደኅንነት አደጋ January 22, 2026 01:56 am
  • የካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን የማርያምን ማዕረግ ዝቅ አደረገች December 12, 2025 09:27 pm
  • ኢህአፓ: ከነጭ ሽብር ወደ “አዲስ አበባ ትናገር” የጎዳና ሽብር? December 12, 2025 09:11 pm
  • EOC Bans Haile Gebrselassie Over Are­qie Comments Linked to Doping November 21, 2025 07:47 pm
  • በሥራ ማቆም አድማ ጥሪ ዘርፍ ባለሙያው ጃዋር ሌላ ጥሪ አቀረበ November 17, 2025 09:25 am
  • የ-አብሮነት ማኅበር የመረጠው ሕቡዕ የሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ይፋ ሆነ November 5, 2025 12:06 pm

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2026 · Goolgule