• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ልጆቻችን ናቸው እኮ” ኮሚሽነር አበረ አዳሙ

January 26, 2020 03:58 pm by Editor Leave a Comment

“አንዳንዱ ነገር ድራማ ይመስላል” የኦነግ ቃል አቀባይ ቀጄላ መርዳሳ

በህዳር ወር 2012 የመጨረሻ ሳምንት ከደንቢ ዶሎ ዩኒቨርሲቲ ወደ ጋምቤላ ከተማ በመጓዝ ላይ ሳሉ በአጋቾች እጅ የገቡት ተማሪዎች ጉዳይ አሁንም አወዛጋቢ ሆኖ ቀጥሏል። እስከ አሁን ባለው መረጃም ተማሪዎቹ የአማራ ክልል ነዋሪ እንደሆኑ በመገለፁ አዲስ ማለዳ የአማራ ክልል የፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር አበረ አዳሙን አነጋግራለች።

ኮሚሽነሩ ምንም እንኳን በጉዳዩ ላይ በቀጥታ ለመሳተፍ የህግ ገደብ ቢኖርባቸውም የታገቱት ተማሪዎች ከተያዙ እለት ጀምሮ የልጆቹን ሁኔታ በቅርበት እየተከታተሉት አንደሆነ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል። “የስልጣን ገደብ ቢኖርብንም ልጆቻችን ናቸው እኮ፣ መቶ በመቶ ቅድሚያ ሰጥተን እየተከታተል ነው” ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ዛሬ አመሻሹ ላይ ገልጸዋል። “ጉዳዩ የኛ ጉዳይ ነው፣ ነገር ግን መዋቅር መከበር ስላለበት የፌደራል ፖሊስ እና የክልሉ ፖሊስ እንጂ እኛ ምንም መናገር አንችልም” ብለዋል።

“የማውቀው ነገር የለም ልልሽ አልፈልግም፤ ግን ደሞ መግለጫ ለመስጠት ገደብ አለብኝ” ሲሉም ተጨማሪ መረጃ ከመስጠት ተቆጥበዋል። 

በወለጋ ዞኖች ጠንካራ መሰረት እንዳለው የሚታወቀው የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) ቃል አቀባይ ቀጄላ መርዳሳ ግን “ጉዳዩን በደንቢ ዶሎ አካባቢ ካሉ ሰዎች አጣርተን የተጨበጠ ነገር አላገኘንም፤ አንዳንዱ ነገር ድራማ ይመስላል” ሲሉ ለአዲስ ማለዳ ተናግረዋል።

“ማን የት ቦታ እንደተያዘ ለማረጋገጥ ህብረተሰቡን እና አንዳንድ ተቋማትን ጠይቀናል፣ ተጨባጭ ነገር ማግኘት አልቻልንም” ብለዋል። “ምን አልባት ውዥንብር ይሆናል ብለን እንጠረጥራለን፣ ጉዳዩ የተማሪዎቹ ብቻ አይደለም፣ ከዚህ በፊት የኦሮሚያ ክልል ተወላጅ የሆነ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዘዳንት ተያዘ ተብሎ የት እንደገባ ሳይታወቅ ከዛ ተገኘ ተባለ፣ የት እንደነበረ ማን እንደያዘው አልተናገረም” ሲሉም ጥርጣሬአቸውን ገለጸዋል።

የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሪታሪያት ኃላፊ ንጉሱ ጥላሁን ከሁለት ሳምንት በፊት 21 ተማሪዎች መለቀቃቸውን እና ከነዚህም 13ቱ ሴቶች ስድስቱ ወንዶች መሆናቸውን ገልፀው ነበር። በተጨማሪም አምስት የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና አንድ የአካባቢው ነዋሪ የሆነ ወጣት በአጋቾች እጅ እንደሚገኙ እና እነዚህንም ለማስፈታት መንግስት ጥረት እያረገ መሆኑን ገልፀው ነበር።

በታጋቾቹ ደህንነት ላይ የመጨረሻውን መረጃ ለዶይቼ ቨለ የሰጡት የኦሮሚያ ክልል የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ሃላፊ ጌታቸው ባልቻ ከእገታው የተለቀቁት 21 ተማሪዎች ወደ ትምህርት ገበታቸው ተመልሰዋል ማለታቸው አይዘነጋም።

አዲስ ማለዳም ወደ የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት የፕሬስ ሴክሪታሪያት ኃላፊ ንጉሱ ጋር መረጃ ለማግኘት ያደረገቸው የስልክ ጥሪ ሳይሳካ ቀርቷል።

አዲስ ማለዳ

Filed Under: News, Social Tagged With: bring back our sisters, Full Width Top, Middle Column, olf, olf shine

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule