የኦሮሞ ሕዝብ ትግል ፍሬ እንዳያፈራ ትልቁ ተግዳሮት የነበረው ኦነግ ሸኔ መሆኑን የኦሮሚያ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የሕዝብ ግንኙነት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ታዬ ደንደኣ አስታወቁ። ህወሓት ኦነግ ሸኔን በአደባባይ እንደ ጠላት እየፈረጀ በተግባር ግን የኦሮሞን ትግል ለማክሰም እንደ መሣሪያ ይጠቀምበት እንደነበረም አመለከቱ። አቶ ታዬ ደንደኣ በተለይ ከአዲስ ዘመን ጋዜጣ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ የኦሮሞ ሕዝብ ያካሄደው የፍትህ የእኩልነትና የነፃነት ትግል ፍሬያማ እንዳይሆን ኦነግ ሸኔ ከህወሃት ጋር የነበረው ከሕዝብ የተሰወረ ህብረት ዋንኛ ምክንያት ነው ብለዋል። ኦነግ ሸኔ የኦሮሞ ታጋዮች አንድ ወጥመድ ሆኖ ለህወሃት ሲያገለግል እንደነበርም አመልክተዋል። ብዙዎች ኦነግ ሰፊ የሕዝብ ድጋፍ እያለው የዚህ ድርጅት ትግል ለምንድን ነው ወደፊት ገፍቶ የማይመጣው? የሚል ጥያቄ ነበራቸው። … [Read more...] about “ኦነግ ሸኔ የህወሓት መጠቀሚያ ዕቃ ነው” ታዬ ደንደኣ