• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ጥቁር ውሃ ላይ አስጨርሶ፣ እንደገና የፈረጠጠው ጄኔራል ከበደ ፈቃዱ ማን ነው?

August 16, 2021 12:46 am by Editor Leave a Comment

የህወሃቱ ታጋይ ጄ/ል ከበደ በ1988 ዓም  የ31ኛ ክ/ጦር 3ኛ ብርጌድ ፓራ ኮማንዶ፣ የ1ኛ ሻለቃ አዛዥ ሆኖ ሰርቷል።  በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት በ31ኛ ክ/ጦር ምክትል ብርጌድ አዛዥ ሆኖ አገልግሏል። በ1992 ዓም 35ኛ ክ/ጦር ስትፈጠር የ35ኛ ክ/ጦር 3ኛ ብርጌድ አዛዥ ሆኖ ተሹሟል።

በ1997 ዓም ኮር የሚባለው አጀረጃጀት ፈርሶ ዕዝ የሚባል አደረጃጀት ሲቋቋም፣ ግለሰብ የ35ኛ ክ/ጦር ም/አዛዥ ቀጥሎም የ33ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ ሆኖ እስከ 2006 ዓ/ም ሠርቷል።

በ2006 ዓ/ም እነ ጄኔራል አበባው ታደሰን ለማስወጣት በተደረገው ግምገማ፣ ግለሰቡ የአበባው አሽከር ነህ ተብሎ ተፈርጇል። ይህን ተከትሎም  ከክፍለ ጦር አዛዥነቱ ተነስቶ፣ የዕዙ ማሰልጠኛ ት/ት ቤት አዛዥ ሆኖ ተመድቧል።

የጡረታው ጊዜ ሲደርስ “ተጠቅሞ ይውጣ” ተባለና ወደ አብዬ በሚሊቴሪ “ኦብዘርቨርነት” ተላከ።  በአማራና ኦሮሞያ የነጻነት  ትግል ሲቀጣጠልና የህወሃት ህልውና አደጋ ላይ ሲወድቅ፣  ህወሃት በጡረታ ልታስወጣው ያሰበችውን ሰው መልሳ፣ በ2010 ዓ/ም አጋማሽ ላይ የብ/ጄኔራልነት  ማዕረግ ሰጥታ ለሌላ ተልዕኮ አጨችው።  ከዚያም የ31ኛ ክ/ጦር ዋና አዛዥ አድርጋ ሾመችው። 

ሰውዬው በጣም ጨካኝ ነው ይሉታል አብረውት የሰሩት ሰዎች ሲናገሩ። “በኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ወቅት፣ ወደ ኤርትራ በጥልቀት ገብተን እያለ፣  ወደኋላ እንድንመለስ ስንታዘዝ፣ ሻዕብያም መረጃው ደርሶት ሰለነበር፣ ከፍተኛ የከባድ መሳሪያ ድብደባ ማድረግ ጀመረ። በዚህ መሃል  አዲስ ከመጡት ምልምል ወታደሮች መካከል አንድ ወጣት ተደናግጦ ራሱን አቆሰለ። ስለልጁ ድርጊት ለከበደ ሪፓርት ሲደረግለት፣ ‘አምጡት’ አለና፣  ሽጉጡን አውጥቶ ግንባሩን ብሎ ገደለው።”

በ2013 ዓ/ም ደግሞ በመከላከያ ሰራዊት ላይ ድንገተኛ ጥቃት ሲፈጸም፣ የእሱ ምክትል የነበረውን ኮ/ል ሻምበል በየነን (ባለከዘራውን) ለማስገደል አቅዶ፣ የክ/ጦሩ ም/አዛዥ እቅዱን ባለመቀበሉ፣  ከተማ ቀጥሮ በሽጉጥ ግንባሩን ብሎ ገደለው።

የብርጌድ አዛዥነቱን ተጠቅሞ ከኤርትራ ያዘረፈውን የኮንስትራክሽን መሳሪያዎች፣ ስኳርና ከብት፣  ሽራሮ ላይ ሽጦ  አክሱም ላይ ፎቅ ሰርቶበታል። ከጭካኔውና ሌብነቱ በተጨማሪ በቀላሉ ሊገለጽ የማይችል ዘረኛም ነው።

በለውጡ ማግስት አምባሳደር ስዩም መስፍን  ከኮሎኔል ማዕረግ በላይ ያላቸውን ወታደራዊ አዛዦች በየሁለት ሳምንቱ እየሰበሰበ ግዳጅ ይሰጥ ነበር።  ጄ/ል ከበደ ደግሞ  ሽሬ ላይ ከፍተኛ መኮንኖችን እየሰበሰበ ከላይ ያመጣውን ተልኮ ወደታች በማውረድ ስራውን ይሰራ ነበር። ይህ ሁሉ ሲሆን ሰራዊቱ በተደጋጋሚ ለበላይ አለቆች ቢያሳውቅም፣ ምላሽ በማጣቱ፣ የጥቅምት 24ቱ እልቂት ተከሰተ። ከዚህ እልቂት ጀርባ ካሉት ቁልፍ ሰዎች መካከል አንዱ ይህ በተደጋጋሚ ታዳጊዎችን እያስጨፈጨፈ የሚፈረጥጠው ጄኔራል ነው።

ፋሲል የኔዓለም

Filed Under: Opinions, Right Column Tagged With: operation dismantle tplf

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule