አምስተኛ መካናይዝድ ክፍለጦር ወታደራዊ ካምፕ ውስጥ እንደ ወትሮው ከዋርድያዋች ውጭ ሁሉም ተኝቷል።
አንድ ታላቅ ፣ ጥቀር የሌሊት ልብሱን እንደ ለበሰ መፅሃፍ ያነባል ድንገት የቶክስ ድምፅ ሰማ በአካባቢው ሁሌም የቶክስ ድምፅ መስማት የተለመደ ቢሆንም ወታደር ነውና ምልልስ ካለ ብሎ ለማዳመጥ ሞከረ ከሁለት አቅጣጫ መሆኑን ተረዳ።
ስልኩን አነሳ ወደተለያየ ቦታ ደወለ ሁሉም አይሰራም ስልኩን አየው ኔትወርክ የለውም አሁን ችግር እንዳለ ተራዳ ካለበት ክፍል ግድግዳ እየታከከ ወደ በሩ ተጠጋና በሩን ሲከፍተው የተመታ ጓዱ ከነክላሹ በጀርባው ወደቀ ወዲያው የቶክስ ሩምታ ወደ በሩ አቅጣጫ ተከፈተበት እንደምንም ከወደቀው ጓዱ ካላሹን ተቀብሎ እየተኮሰ በቅርብ ቀን ወደተሰራች የብሎኬት ግቢ ዘሎ ገባ።
በግቢው ውስጥ አንደ ገባ የራሱ ጓድ የሆነች ሴት ወታደር በብሎኬት አጥር ቀዳዳ መትረየስ ደቅና ወደ ጀኔራል አለበን መኖሪያ ቤት ስትተኩስ አያት አላቅማማም አነጣጥሮ አናቷን ነደለው።
ወዲያው መትረየሱን ተቀብሎ ጀርባውን ለጀኔራል አለበል ቤት ሰጥቶ የመከላከያ ምሽግ ይዞ ከፊትለፊቱ የነበሩ የትግራይ ልዩ ሃይል ጋር ብቻውን ገጠመ።
መድፎች ያጓራሉ፣ሚሳይልና ሮኬቶች ይወነጨፋሉ፣ ታንኮች ይርመሰመሳሉ፣ጥይቶች ይንጣጣሉ፣ቦንቦች ይፈነዳሉ፣መድፎች አቶን ያስታውካሉ፣ደም እንደ ጎርፍ ይፈሳል፣ አካልይበሳል፣ ይሰነጣጠቃል፣ ይቦደሳል፣ ይጎመዳል፣ ይደቃል፣ ይጨሳል፣ ይነዳል፣… ሕይወት ከሞት ይተናነቃል።
ታላቁ ጥቁር ወጊያው ከባድ መሆኑን ተረዳ እንደምንም በደረቱ አየተሳበ ከጀኔራሉ ቤት ደረሰ። ጀኔራሉ ሲያዪት ደስ አላቸው ድል ድል ሸተታቸው። ትንሽ እንኳን ሳይረጋጉ ጀኔራሉ ወታደራዊ ግዳጅ እንዲህ በማለት ሰጡት እኔ ሽፋን እሰጥሀለሁ አንተ ሃድና ከፋት ለፊት ከወደቁ ጓደቹህ ቦታ ሄደህ የጓዶችህን ዲሽቃ እና ኤ ኬ 47 መሳሪያ ይዘህ ተመለስ አሉት።
ትእዛዙን ጣሰ አልህና እና ቁጭት ቆሽቱን አሳርሮት ነበርና የተመቱ ጓዶቸን ደም ለመመለስ ባለበት ሆኖ አንዴ በዲሽቃ፣አንዴ በመትረየስ ፣አንዴ በብሬል ከመሳሪያ መሳሪያ አየዘለለ ጠላትን ይቆላው ያዘ።
ጠላት ተደናገጠ አንድ ሰው ሳይሆን ከመቶ ሃይል እሚተኮሰ መስሎት ወደ ኋላ አፈገፈገ።
ወዲያው የአማራ ልዩ ሃይልና ሚሊሻ ከኋላ ደርሶ ያ ታላቁ ጥቁር ያባረረወን የጠላት ሃይል መውጫ መግቢያ አሳጥቶ ሙሉ በሙሉ ደመሰሰው።
Leave a Reply