• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

“ነገርን ከሥሩ ውሃን ከጥሩ”

February 15, 2022 09:15 am by Editor 1 Comment

የአማራ ሕዝብ ምንም አይነት የመሰረተ ልማት ባልነበረበት፣ የግንኙነት አውታሮች እጅግ ኋላ ቀር በሆኑበት ሁኔታ አንድነቱን አስጠብቆ ከሌሎች ወንድሞቹ ጋር በመተባበር ኢትዮጵያን ገንብቷል። የባህል መስተጋብሩና ሌሎች ማህበራዊ እውነታዎቹ ከራሱ አልፎ ኢትዮጵያን ድርና ማግ ሆኖ አስተሳስሯል። የሁለቱ ታላላቅ ኃይማኖቶች (ክርስትና እና እስልምና) መንፈሳዊ መሪዎች መፍለቂያ መሆኑ አጥር የማይበጅለት አቃፊና ተጋሪ የማንነት ባለቤት አድርጎታል። ለዚህ በርካታ ማሳያዎችን ማቅረብ የሚቻል ቢሆንም የነገረ-ፍሬየ መዳረሻ አይደለምና እዘለዋለሁ። ሊሰመርበት የሚገባው የአማራ ሕዝብ አንድነት ግን የሰላሳ ዓመታት ሳይሆን በሺህ የሚቆጠሩ ዓመታትን የተሻገረ ነው። የዳማት ዙፋን ወራሽ፣ የአክሱም ሥልጣኔ ባለቤት ነው!!

ይህ የአማራ ያገጠጠ ሃቅ በትህነግ ዘመን ለመፍጠር ከታሰበው አማራ እና ፖለቲካዊ ስዕሉ እጅግ የተለየ ነው። አማራን ክልል በተባለ በረት መገደብ ከተጀመረበት ከ1983 ጀምሮ የውስጥና የውጭ ፖለቲካዊ ሁኔታዎች ተቀያይረዋል፤ አማራ የደምና የላብ ዋጋ በከፈለላት ኢትዮጵያ ማንነቱ ወንጀል ሆኖበት በጅምላ ተገድሏል፣ ተፈናቅሏል፣ ተሳ’ዷል። የአካልና የንብረት ጉዳት ደርሶበታል። በእኔ እምነት ከአይሁዳዊያንም ሆነ ከርዋንዳ ቱትሲዎች በላይ ለተራዛሚ ዓመታት የከፋ እልቂት (የዘር መጥፋት) እያስተናገደ ያለ ሕዝብ ነው። የአማራ የቁርጥ ልጅ ፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ ከጀመሩት ሕዝብን የማንቃትና የማደራጀት ንቅናቄ ጀምሮ ለአማራ እልቂትም ሆነ መፈናቀል ተጠያቂ የሚሆነው ከፍ ሲል የሥርዓቱ ባለቤት የሆነው ትህነግ/ኢህአዴግ ዝቅ ሲል ደግሞ ብአዴን ነበር። ይህን እውነታ ይዘን የአማራ ክልል መሪዎች እነማን ነበሩ?

1) አቶ አዲሱ ለገሠ [ሐረር-] 1984-1992 (8 ዓመታት)

2) አቶ ዮሴፍ ረታ [ሸዋ] 1993-1997 (5 ዓመታት)

3 አቶ አያሌው ጎበዜ [ጎጃም] 1998-2006 ህዳር (8 ዓመታት)

4) አቶ ገዱ አንዳርጋቸው [ወሎ] ከሕዳር 2006 – የካቲት 2011 (5 ዓመታት)

5) ዶ/ር አምባቸው መኮንን [ጎንደር] ከመጋቢት 2011- ሰኔ 2011 (3 ወራት)

6) አቶ ተመስገን ጥሩነህ [ጎጃም] ከነሐሴ-2011 – ጥቅምት 2013 (1 ዓመት ከሦስት ወራት)

7) አት አገኘሁ ተሻገር [ጎንደር] ከህዳር 2013 – መስከረም 2014 (1 ዓመት ብቻ)

8) ዶ/ር ይልቃል ከፋለ [ጎጃም] ከመስከረም 2014 – …

የመሪነት ሁኔታውን ዘመን በአውራጃ ካሰላነው እንደሚከተለው ይሆናል:-

አንደኛ፦ ጎጃም 3 ዙር ጠቅላላ ድምር = 10 ዓመታት

ሁለተኛ ፦ የወያኔ አማርኛ ክንፍ አዲሱ ለገሠ ከሐረር – 8 ዓመታት

ሶስተኛ፦ ወሎ 1 ጊዜ ጠቅላላ ድምር 5 ዓመታት

አራተኛ ፦ ሸዋ 1 ጊዜ ጠቅላላ ድምር 5 ዓመታት

አምስተኛ ፦ ጎንደር 2 ጊዜ ጠቅላላ ድምር 1 ዓመት ከሦስት ወር ሁኖ እናገኘዋለን።

በሰላሳ ዓመታቱ የአማራ ክልል መንግሥት ውስጥ የመሪነት ድርሻው ምን እንደሚመስል ከዚህ በላይ የቀረበውን መረጃ አይቶ መፍረድ ይቻላል። እንደጎንደር ያለው አካባቢ በርካታ ዞኖችና የሕዝብ ቁጥር ቢኖረውም በ30 ዓመቱ የክልሉ ታሪክ ያለው የፕሬዝዳንትነት መጋራት ከ1 ዓመት ከ3 ወራት ያልዘለለ ነው። ይህ ማለት በመቶኛ ሲሰላ ከ2.4 % አይዘልም!

ልብ በሉ ፍሬ-ነገራችን አውራጃዊ ስሌት አይደለም። ለአማራ ሕዝብ እስከጠቀመ ድረስ አማራዊ ስነ-ልቦና ይኑረው እንጂ፣ አማራ አንድ ህዝብ እስከሆነ ድረስ ከየትኛውም አውራጃ ይምጣ ጉዳያችን አይሆንም። በፉጹም። ግን ሌላ ጥሬ ሃቅ አፍጥጦ የምንመለከተው አለ:-

ይህውም የአማራ ብሄርተኝነት ከተነሳበት 2008 ጀምሮ የፖለቲካችን አውድ ድርጅትን ተጠያቂ ከማድረግ ይልቅ ግለሰቦች ላይ ማጠንጠን መለያ ባህሪው ሆኗል።

የአማራ ፖለቲካ እስከ አሁንም የተንጠለጠለው በግለሰቦች ላይ ነው። ተቋም ላይ አትኩሮት አልነበረውም። ከሰሞኑ ግን የሚታይ ነገር አለ። በአማራ ፖለቲካ ዑደት የሚወደሱትም ሆነ የሚብጠለጠሉት ግለሰቦች ብቻ እየተመረጡ ነው። ይህ ብሄርተኝነቱ የፈጠረው ስሜት ነው ለማለት ይቸግራል። ግን በብሄርተኝነቱ ዘመን የተፈጠረ የጎጠኝነት ደዌ ውላጅ ባህሪ ነው። ድርጅቱን ጥሎ ግለሰቡን አንጠልጥሎ አልያም አብጠልጥሎ የመጓዝ የብልጣብልጦች መንገድ ነው። ይህ በተፍካካሪውም ሆነ በገዥው ፓርቲ የተጣባው አባዜ ነው።

በተለየ ሁኔታ ትህነግ ከአዲስ አበባ ተባርሮ መቀሌ ከመሸገና አገራዊ ለውጡ ከመጣ በኋላ (ባለፉት 4 ዓመታት) በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፕሬዝዳንትነት ወንበር ላይ የተለያዩ ግለሰቦች ተቀምጠውበታል። የወንበሩ አለመርጋት ለእኔም ይደንቀኛል። ከ2010- 2014 አምስት ፕሬዝዳንቶችን ቆጥረናል:- (አቶ ገዱ፣ ዶ/ር አምባቸው፣ አቶ ተመስገን፣ አቶ አገኘሁና ዶ/ር ይልቃል) በዚህ የእብደት ጊዜ መርጦ አልቃሽነትና መርጦ አሞጋሽነትን ታዝበናል:-

1ኛ በ2011 ሚያዚያ ላይ አምቦና ከሚሴ የተካሄደውን ስብሰባ ሰበብ በማድረግ በዶ/ር አምባቸው መኮነን ላይ (ነብስ ይማር) የነበረውን እርግማንና ዘመቻ እናስታውሳለን። ጠጅ የአማራ ባህል ያልሆነ ይመስል “ጠጆ” የሚል ቅፅል ስም እስከመስጠት ተደርሶ እንደነበር አንዘነጋም!

2ኛ በ2013 መጋቢት የአጣዬን ውድመት ተከትሎ በአቶ አገኘሁ ተሻገር ላይ የተደረገውን ዘመቻም አንረሳውም።

ያ…ኔ ጥቂትም ቢሆኑ ጥፋት ሲጠፋ መወቀስም ካላባቸው ግለሰቦች ሳይሆኑ እንደ ድርጅት መሆን አለበት ብለው የተከራከሩ አርቆ አሳቢዎች እንደነበሩም አንዘነጋም። ሃሳባዊያኖቹ “መርጦ መራገም” ልክ አይደለም፤ ብለው መክረው ነበር። የእርግማኑ ጥርቅምና ሌሎች ሴራዎች ተደማምረው ያን ጥቁር ቀን ፈጥሮ አልፏል። በተራ ቁጥር አንድና ሁለት የጠቀስኳቸው ዋና ዋናዎቹን የእርግማኖች ዶፍ እንጂ በውሃ ቀጠነ ምክንያት ሳይቀር የነበሩትን ግለሰቦች ላይ ያተኮሩ ዘመቻዎችን አንዘነጋቸውም።

አሁን ግን ከባለፈው ትምርት ተቀስሞ ይሆን? አላውቅም። ወይም የአርቆ አሳቢዎቹ ምክር ሰምሮ ይሁን? አሁንም አላውቅም። ብቻ ጉዳዮቻችን እናነሳለን። እንዘረዝራለን። የት*ግሬ ወ*ራሪና አሸባሪ ደሴን፣ ኮምበልቻን ተቆጣጥሮ ደብረ-ሲና ደርሶ ነበር። በአማራ ህዝብ ላይም ዘግናኝና ሁልቆ መሳፍርት ግፎችን ፈጽሟል። ነገር ግን በዚያን ወቅት እንዳለፈው ሁሉ በግለሰቦች (ፕሬዝዳንቱ) ላይ የእርግማን መአት አልወረደም። ይሰመርበት መወረድ ነበረበት እያልኩ አይደለም።

ይደገም:-

ከሰሞኑ እጅግ ሰቅጣጭ በሆነ ሁኔታ ከ168 በላይ በኦሮምያ ክልል ወለጋ “አገሬ” ብለው በኖሩ ንጹሃን የአማራ ተወላጆች ላይ በማንነታቸው ምክንያት ተለይተው በአሸበሪው ሸኔ ሲጨፈጨፉ ከዚህ በፊት እንደ ነበረው ሁሉ በክልሉ ፕሬዝዳንት ላይ ብቻ ተለይቶ የእርግማን መአት አለመውረዱ አዲስ ነገር ነው፤ ይህ በመሆኑ እንደኔ መልካም ነው። ጥሩ ጅምር ነው። በዚህ ረገድ የወቅቱ ፕሬዝዳንትም ዕድለኛ ናቸው። እንቅልፍ ከሚነሳ ስድብ ነፃ ሆነዋልና መተኛት ይችላሉ።

እንደ ከዚህ ቀደም የነበሩት (ያሉት) ወቀሳዎችም ሆኑ እርግማኖች በገዢው ፓርቲ በተለይ የአማራን ህዝብ ወክየዋለሁ ባለው በአማራ ብልጽግና መሆኑናቸውን አስተዋል እንጂ በፕሬዝዳንቱ ላይ ብቻ ያነጣጠሩ አይደለም። እንኳንም አላነጣጠሩ። “ተቋም የግለሰቦች ስብስብ እንጂ ግለሰቦች ብቻቸውን ተቋም አይደሉምና” ለልማቱም ሆነ ለጥፋቱ ተቋሙን ይመለከታል የሚለው አመክንዮ ገዢ ሆኖ ተገኝቶ ከሆነ (?) ጥሩ ጅምር ነው እንላለን። ከዚህ ሌላ ዓላማ ተይዞ ከሆነም ከልምድ እንማራለን። እንደዛሬው ጅምር ትችታችንም ሆነ ውዳሴ’ችን ተቋም ላይ ይሁን እያልኩ ጽሁፌን መቋጨቱን መርጫለሁ።

ጽሁፉ የተወሰደው ከአምደማርያም ዕዝራ ቴሌግራም ገጽ ነው

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Middle Column, Opinions Tagged With: amhara region

Reader Interactions

Comments

  1. ጥላሁን ጌታነህ says

    February 15, 2022 12:53 pm at 12:53 pm

    በውነቱ ጥሩ ትንታኔ ይመስላል ፤ እኒህን የመሰሉ አንቂዎች መልካም ቢሆኑም ቅሉ ወደ አንድ ጎን ማዘንበሉን ተወት አድርገው ኢትዮጵያዊነትን መዘመርና ማስዘመር ላይ ትኩረት ቢያደርጉ ዕውነተኛና ቁርጠኛ አጃቢዎችን ብቻ አይደለም ተከታዮችን ያፈራሉ፡፡ በአመለካከቱ እና በአስተሳሰቡ የመጠቀ እንዲሁም ወደ ቀደመ ትልቅነቱ የሚያመራ፤ ለስልጣኔና ለጋራ ባህሉ ልማት አርቆ አላሚ ፤በየትኛውም መስክ የላቀ ክኅሎትና የዳበረ ዕውቀት ያካበተ………ወዘተርፈ ትውልድ የማስቀጠል መሠረት እንደሚገነቡ እገምታለሁ፡፡
    ስለ ጎልዳፋ አስተያየቴ ይቅርታን እሻለሁ፡፡

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule