• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች

May 19, 2022 09:37 am by Editor Leave a Comment

የገጠመን ጠላት ጦርነትን እንደኦክስጅን የሚቆጥር ያለጦርነት መሽቶ የማይነጋለት ደመ-ቀዝቃዛ ኃይል ነው። በፍፁም የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ያለው ወያኔ ኢትዮጵያን ለማፍረስ፣ ቀጠናውን ለማተራመስ እረፍት የለውም፡፡ ምክንያቱም በአንድ በኩል የት*ግሬን ወጣት ሊመግበው የሚችለው በዘራፊነት አሰማርቶ ብቻ ነውና፡፡

የወያኔ ሠራዊት ዘራፊና ወሮ-በላ (pillager) ሠራዊት ነው፡፡ ወሮ-በላ ሠራዊት ደግሞ ዓይኑን ጨፍኖ ለመዝረፍ የሚመጣ ኃይል ነው፡፡ መዝረፍ፣ ማውደም፣… ግብሩ ነው። ቆቦ፣ ወልድያ፣ ሐይቅ፣ ደሴ፣ ኮምበልቻ፣ ከሚሴ፣ ሸዋሮቢት፣ ንፋስ መውጫ፣… ዐቢይ ማሳያ ሆነው ይቀርባሉ።

ከሐምሌ-ታህሳስ በዘለቀ የወሎ፣ ከፊል ሸዋና ጎንደር የጦር ወረራው ከዶሮ እንቁላል እስከ ፋብሪካ ማሽነሪ፤ ከአልባሳት እስከ ቀንድ ከብት፤ ከማህበራዊ የልማት ተቋማት እስከ እርሻ ሰብል፤…ድረስ ያለውን ንብረት የቻለውን ዘርፎ ያልሆነለትን አውድሞ መሸሸቱ ይታወሳል። በብዙዎቹ ቦታዎች ከባድ ምት ደርሶበት ከመሸሹ በፊት ‘scorched earth policy’ ተግብሯል።

ኢትዮጵያ ብሔራዊ ሰራዊት ባልገነባችባቸው በጥንት ዘመን እንኳ አሁን ካለው የወያኔ ወርሮ-በላ ሠራዊት በላይ ክፉ ጠላት ያጋጠማት አይመስልም። ከቋንቋ ተናጋሪነት ውጭ ከድርቡሽ የሚለይበት ነገር የለውም።

ሌላኛው እውነታ፣ ወያኔ የሚከተለው የጦርነት ስትራቴጂ መትረፍን እንደ ዓይነተኛ ዓላማ የያዘ መሆኑ ላይ ነው፡፡ የፖለቲካም ሆነ የውጊያ ሁለ-ነገሩ ‘Survival as a Strategy’ ነው። ለወያኔ በሕይወት ለመኖር መዋጋት መሠረታዊ ጉዳይ ነው፡፡ እዚህ ላይ ልብ ሊባል የሚገባው ወያኔነት በራሱ አስተሳሰብ ስለመሆኑ ነው። የአስተሳሰቡ ተሸካሚ የሆነ (ማህበራዊ መሰረቱ) ወሮ-በላነት የማንነቱ መገለጫ ሆኗል።

እነዚህን መሠረታዊ እውነታዎች ታሳቢ አድርገን ስንመለከተው፣ “ወያኔ ሰላም ይፈልጋል” ማለት ከፍ ሲል ተራ ቅዠት፤ ዝቅ ሲል ቅጥፈት ነው፡፡

ባለፈው ክረምት በነበረው ውጊያ 350,000 በላይ የትግሬ ወጣት ወደቤቱ አልተመለሰም። እዚያው ትግራይ ውስጥ በስኳር፣ ደም ግፊትና በምግብ እጥረት የረገፈውን ስንደምረው በዚህ ጦርነት 400,000 ገብሮበታል። ይህም ሆኖ ሰላም አይናፍቀውም፣ ዛሬም አውዳሚ ጦርነትን ያልማል።

በአጭሩ ወያኔ፦

  • የሰው ሕይወት በጅቶ የሚዋጋ የዘመናችን በላዔሰብ መሆኑን፤
  • ጦርነት ካቆመ ሕይወት እንደማይኖረው፤
  • ሁልጊዜም በጦርነት ውስጥ መኖር ለዚህ ድርጅት ህልውና ወሳኝ ኦክስጂን መሆኑን፤ … መረዳት
    ይገባል፡፡

ስለሆነም ከፊትለፊታችን የዋንጫ ጦርነት ነው የሚጠብቀን። ይልቁንስ ወንድም ጓንጉል የአርማጭሆው እንዳለው የአሁኑ ጦርነት ወያኔንና አስተሳሰቡን ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ከኢትዮጵያ ምድር ነቅሎ ለመጣል መሆን አለበት!!

አንድ መታወቅ ያለበት መሰረታዊ እውነታ የዋንጫው ጦርነት የአካባቢውን ሀገራት የግዛት ሁኔታና የሕዝቦችን ሥነ-ልቦናዊ ስሪት የሚቀይር ስለመሆኑ ነው።

እጅግ በተለየ ቀጣና ውስጥ ነው የምንኖረው፣ የቅኝ-ግዛት ድንበሮችን የማይቀበል፣ በሁሉም ተጎራባች አገራት መካከል የድንበር ውዝግብ ያለበት፣ በአለቃ አልባው የዘመናችን የዓለም ሥርዓት ውስጥ የጥላቻ ተፎካካሪዎች (Bitter Rivals) እጃቸውን ያስረዘሙበት አካባቢ ነው።

በዘመናዊው የአፍሪካ ታሪክ ረዥሙ ጦርነት የተካሄደው እዚሁ ቀጣና ብቻ ሳይሆን እኛ ሀገር ላይ ነው። ከቀጠናው ባህሪ አኳያ ነገሮችን ብንመለከት እንኳ የወያኔ መነቀል የሰላም ትሩፋቱ በተዋረድ ታንዛኒያና ኮንጎ ይደርሳል። ይቅርና ለአፍሪካ ቀንድ ሀገራት።

በዚህ ጦርነት እንደአፋር ያሉ ድንበር ተሻጋሪ ማንነት ያላቸው ማኀበረሰቦች ሚና በቀላሉ አይታይም። ጉዳዩ የማዕከላዊ መንግሥት መጠናከርና መዳከም ጉዳይ አይደለም ከዛም የሚሻገር ነው። ስለሆነም ወያኔን መቅበር የምርጫ ጉዳይ አይደለም። ምርጫ የለንም!

እናማ በዚህ ጦርነት ጠላት ኦንደፍልፈል እየገፋ ባለበት ሁኔታ “የሰላም ሰባኪ ነኝ” የሚለውን ጭምብላም በማይካድራ፣ በጭና፣ በቆቦ፣ በአጋምሳ፣ በንፋስ መውጫ፣… ሰማዕታት ስም ምህረት ንፈገው። የእነ እሸቴ ሞገስ አደራ አለብኝ በለው።

በመጨረሻም በዚህ ጦርነት የተለመደው አይነት የማጥቃት ስልቶች ይመጣሉ።

የማያቋርጥ የሐሰተኛ መረጃ ስርጭት፣ የሳይበር ጦርነቱን በሐሳብ የበላይነት የሚመሩ ግለሰቦችን አካውንት ማዘጋት፣ በማህበራዊ ሚዲያ የተመረጡ ግለሰቦችን ስም ማጥፋት፣ የደቦ ፍርድ ቅስቀሳ፣ … ወዘተ የሚጠበቁ ቀውሶች ናቸው። ያለምህረት መታገል የኛ ኃላፊነት ነው።

በተረፈ አካይስትና መሸጦውን ንቀህ ተወው አልልህም፤ ጀርባህን ለምታምነው ብቻ ሰጥተህ ግን ተዋጋ!! (ሙሉዓለም ገብረመድኅን)

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ

Filed Under: Left Column, Opinions, Politics Tagged With: endf, operation dismantle tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
  • የጃኖ ስጦታና የዶሮ ፖለቲካ በጎንደር March 10, 2026 09:24 am
Copyright © 2026 · Goolgule