እንደ አገርም፣ እንደ ሕዝብም የገባንበትን የችግር ማዕበል በቅጡ የመረዳት ችግር እንዳለ የሚያመላክቱ ጉዳዮች አሉ። እነዚህን ጉዳዮች ባስቸኳይ ካላቆምን ውርደት በግል፣ በቤተሰብ፣ በቀዬና በአገር ደረጃ በደጅ ቆሞ እየጠበቀን ነውና “ግባ በለው” የማለት ያህል ይሆንብናል። ይህ ከሆነ ደግሞ ዕድሜ ልክ ቀና ማለት አይቻልም። እንግሊዞች ተንበርክከው እንደ ከብት ሳር እንደጋጡት እንኳን ዕድል የሚሰጥ የለም።
ኢትዮጵያ ከዳር እስከዳር ተነስታ፣ ልጆቿ አንድ ሆነው፣ የቻለ ህይወቱን፣ ያላቻለ በደጀን ተጋምዶ በከፈሉት ዋጋ ዛሬ የተገኘው ድል ተመዝግቧል። ከትግሬ ወራሪ ኃይል ነጻ በወጡ አካባቢዎች እንደታየው ዓላማው አገሪቱን መዘረፍ፣ ቀሪውን ማውደምና ወደ ዓመድነት መቀየር ነው። ይህ በዓይን ብረታችን ያየነው እውነት በመሆኑ ማስተባበያ አይቀርብበትም። ይልቁኑም ትምህርት ቤት፣ ክሊኒክና ሆስፒታል፣ ወፍጮ ቤትና የሃይማኖት ተቋም ማውደሙ አፈጣጠሩ ላይ ስህተት እንዳለ እንድናጠና፣ እንድንመረመር የሚያደርግ ሆኗል።
ከዝርፊያና ማውደሙ ቀጥሎ ሰዎች በዘራቸው ብቻ ተለይተው ከቀያቸው ድረስ በመጡ ወራሪ የትግሬ ኃይሎች ተጭፍጭፈዋል። በጅምላ ተቀብረዋል። ሴት እህቶቻችን ዕድሜና የጤና ሁኔታቸው ሳይለይ በደቦ ተደፍረዋል። ስሜትን በሚጎዳና መኖርን በሚተናነቅ ደረጃ ግፍ በንጹሃን ላይ ተፈጽሟል።
ይህ ምክንያት አልባ ወራሪ ቡድን አማራ ክልልን ብቻ ሳይሆን አፋርንም በተመሳሳይ አውድሟል። ንጹሃንን ገድሏል። ደፍሯል። በጅምላ ቀብሯል። ዛሬም “ዳግም ተደራጅቼ፣ ስልት ቀይሼ ዳግም እመጣለሁ” እያለ ነው። ሁለተኛ ዓላማው ያልዘርፈበትን አካባቢ አዳርሶ ለማውደምና “እኔ ከሞትኩ” እንዲሉ ወደ ዓመድ መቀየር እንደሆነ የመጀመሪያ ዘመቻው ማረጋገጫ ነው።
እውነታው ይህ ሆኖ ሳለ በቅልብነት ዩቲዩብ ውስጥ ተቀርቅረው መርዝ የሚረጩት የአውዳሚው ትህነግ “ቅምጦች” ሳያንስ፣ በአገር ውስጥ በተለይም በአማራ ስም እየማሉ ከወዲሁ ሽርሸራ የጀመሩ እንዳለ እየታዩ ነው። በግል የፈለጉትን አቋም መያዛቸው ችግር ባይኖረውም፣ መከላከያን ለማሳነስ፣ መከላከያን ለመተቸት፣ መከላከያን ለመገሰጽ የሚሞክሩ የአገርና የአማራ ክልል ዕጢዎችን እያየን ነው።
ይህ ወራሪ ኃይል መውጫና መግቢያ አጥቶ የሞት ሽረት ውጊያ ላይ መሆኑ እየታወቀ፣ ለመውጫ ሁሉንም ዓይነት ጉድጓድ እየቆፈረ መሆኑ እየታየ፣ ከሸዋ ጀምሮ እየተገፋ ከመደምሰስ የተረፈው እየሸሸ ከኮምቦልቻ ከሚሴና ደሴ ኃይሉ ጋር እንድ ላይ ሲገጥም ሰፊ ቁጥር ያለው ኃይል መሆኑ በቂ ግንዛቤ እያለ፣ ልክ ጦርነቱ እንዳለቀና ድል እንደተጨበጠ በማስመሰል የጅግንነት ሽሚያ እየተስተዋለ ነው። ምንም ክፋት የማያውቁ አገር ወዳድ ፋኖዎችንና ሚሊሻዎችን በስልክ እየገኙ ለሳንቲም ለቀማና ለስውር ዓላማ ማስፈጸሚያ ሲደረግ እያየን ነው።
ዛሬ ዳያስፖራው ወገቡን አስሮ ለአገሩ እየሞገተ ነው። ዛሬ ደጀኑ ሕዝብ በሴረኞች የኑሮ ውድነት ቢጠብሰውም “አገሬ ትዳን” ብሎ ተነስቷል። ከዳር እስከዳር ማለት በሚቻል ደረጃ ሕዝብ አንድ ሆኖ የኃያላኑን መርዛማ ዘመቻ እየመከተ ነው። ትግሉ ገና መጀመሩ እንጂ ገና አልተነካም። እናም ተራ የዝና ሽሚያ ሌላ ዋጋ እንዳያስከፍለን እንጠንቀቅ። ፉከራና ቀረቶ አይጠቅምም። ዛሬ የፉከራና ወደላይ ጥይት በማንኳኳት የሚጮኽበት ወቅት አይድለም። አድብቶ፣ ዝም ብሎ፣ ፍም ሆኖ ጠላትን ማረመጥ እንጂ በየአቅጣጫው መዛበት ዳግም ውርደትን እንጂ ክብርን አይወልድም።
በዚህ የህልውና ዘመቻ ድንቅ የሪፖርት ስራ በመሥራት የተዋጣለት የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ተግባሩን በታላቅ ጥንቃቄ እያካሄደ ይገኛል። የወራሪውን ኃይል በስሙ “የትግሬ ወራሪ ሠራዊት/ኃይል” በማለት በመጥራትና በመሰየም የሠራው ብቻ ትልቅ ክብር የሚሰጠው ነው። የወልቃይትን ሰቆቃ፣ የጦር ሜዳ ውሎ፣ ያልተዘመረላቸውን ጀግኖች ወደፊት በማምጣት፣ ወዘተ አሁን እዚህ ተዘርዝሮ የማያልቅ ድንቅ የጋዜጠኛነት ተግባር በመፈጸም የአማራን ሕዝብ ብቻ ሳይሆን መላ ኢትዮጵያዊን ያነቃ የሚዲያ ተቋም ነው።
ወራሪውን የትግሬ ኃይል ከመቀሌ ሆነው ከሚመሩት ወንበዴዎች መካከል አንዳንዶቹ ሰሞኑን በሚዲያው ላይ ያወረዱት ውርጅብኝ በእርግጥም አሚኮ በጠንካራ መሠረት ላይ ያለ እና ሙያውን በተግባር እየፈጸመ የሚገኝ ተቋም መሆኑን ያስመሰከረ ነው። የዚያኑ ያህል ደግሞ በሤራ አወቃቀረር ወደር የማይገኝለት ትህነግ አሚኮን ለማጥቃትና ሰርጎገቦችን ለማስረጽ ዓላማ እንዳለው አመላካችም ተደርጎ መወሰድ ይገባዋል።
ስለሆነም አሚኮ በዘመቻ ስም ያገኘውን ሁሉ አደባባይ አያምጣ። ትናንት ሻለቃ ዳዊት ወልደ ጊዮርጊስ የሚባል የክህደት ሊቅን ጋብዞ የሽግግር መንግሥትና ትህነግ መራሽ የአዲስ መንግሥት ምስረታ ሲያውጅ፣ አሁን ያለውን መንግሥት ዕውቅና እንደማይሰጡ ጦር ሜዳ ድረስ ወርደው እየተፋለሙ ያሉ መሪያችንን ሳይቀር ባገኘው አጋጣሚ ሲዘለፍ የከረመ፣ በሤራ የተገደሉ ውድ የአማራ አይተኬ ልጆች አሟሟት ላይ “ለአንድ ወገን” ወግኖ ለማተራመስ ሲጠቀምበት የነበረንና ዛሬ መረጃ ቴሌቪዥን ሲቀረቀርበት አማራ ቲቪ ፕሮግራም ላይ ማቅረብ አሳፋሪ ብቻ ሳይሆን እንዳንሸረሸርም የሚያሰጋ ነው። የመድረክ ተወዛዋዡን አበበ በለው በአሚኮ ላይ ቀርቦ ማየት ወይ ስለ ግለሰቡ ማንነት ሳይታወቅ የተፈጸመ ቅን ስህተት ነው፤ ወይም አሚኮ ጓዳውን እንዲመለከት የሚጋብዝ የማንቂ ደወል ነው።
የረሃብተኛ ኢትዮጵያውያንን ገንዘብ ዘርፎ አሜሪካ ቤት የገዛውና ከዚያው ሆኖ አገራችንን ለማፍረስ ዕድሜ ልኩን “ሲተጋ” የኖረውን ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስን የዛሬ ሰባት ወር አበበ በለው “ሻለቃ ዳዊት ወልደጊዮርጊስ ሃቁን አፈረጡት” በማለት ዕድሜ ልኩን ሃቅን ሲጾማት የኖረውን ሰው አቅርቦት ነበር። አበበ ለሃያ አምስት ደቂቃ ዳዊትን በሙገሳ እስክስታ ሲያወርድለት ቆይቶ ሲያበቃ ዳዊትም በአጸፋው መልሶ “እንዳንተ ያለ …” ብሎ አበበን ሲያሞቀውና ውዳሴ አበበ ሲያቀርብለት “በእርሶ መሞገስ …” እየተባባሉ ጀምረው ኢትዮጵያ ላይ ያለውን ሕዝብ የመረጠውን መንግሥት እንደማይቀበሉ፣ የሽግግር መንግሥት መመሥረት አለበት፣ ከማት አልፎ “አማራና ኦሮሞ አብሮ መኖር አይችልም” የሚል ቅስቀሳ ማካሄዱ እየታወቀ፣ ዛሬ የአንበሳ ምስል እያሳየ “ማሸነፍ ብቻ” ለሚለው የአማራ ሚዲያ አበበ በለው እንዴት ሊመጥን ቻለ?
አበበ እየመራ ሻለቃው የጋለቡበትን የዩቲዩብ ቪዲዮ ላፍታ ተመልከቱ።
አበበ የሚታዘዝላቸው የሻለቃ ዳዊት አፍራሽ ኃይሎች ምን እየሠሩ እንደሆነ፣ ከማን ጋር ገጥመው አማራና ኦሮሞውን አላኩሰው እሳት ሊሞቁ እንደተዘጋጁ አቶ ተመስገን ጥሩነህን ደንነት ቢሮ ጎራ ብሎ መጠየቁ ብዙ መረጃ ይሰጣል።
ከዚህ ሌላ አበበ ራሱ በተደጋጋሚ በየቀኑ እየወጣ በሚናገርበት የሚያቀርባቸው እጅግ መርዛምና በሤራ የተሞሉ አፍራሽ ሃሳቦች እንዴት ተዘንግተው ነው ዛሬ የአሚኮ “ጀግና” ሆኖ ለዕውቅና የበቃው? ወይስ የሤራ ሽረባው የሚተላለፍበት መረጃ ሚዲያ ስለተዘጋና ድሉ ከትግሬ ወራሪ ኃይል እጅ ማምለጡ የ“አስገቡኝ” ማመልከቻ ነው? ጋዜጠኛውስ በምን መነሻ ነው አበበ ዕንግዳው ለማድረግ የበቃው? እንደ ጀግናው ታማኝ በየነ ወደ አገር ቤት ገብቶ ትግሉን አልተቀላቀለ? ወይም ሰሞኑን የፈጸመው አንድ የተለየ ተግባር የለ? ጀግኖቹ የቁርጥ ቀን የአብን ልጆች ዩሱፍና ጋሻው በሚቀርቡበት ስንቱ ጀግና በሚወደስበት ሚዲያ ለመንግሥት ግልበጣ ከሚያሤሩ ጋር የሚሞዳሞደው አበበ በለው በምን መሥፈርት ነው የአሚኮን ደጅ መርገጥ የቻለው? ወይስ ጋዜጠኛው ስለ አበበ ምንም ሳያውቅ ወይም እያወቀ የምንደኝነት ተግባሩን እየፈጸመ ነው?
በትግሬው ወራሪ ኃይል የወደሙ መሠረተልማቶችን መልሶ ለማቋቋም ብዙ ዕቅዶች እየወጡ ነው። ከእነርሱ አንዱ በዳያስፖራ የገንዘብ ማሰባሰብ ማካሄድ ነው። ታዲያ በውዳሴ የታጀበው ቃለምልልስ ለአበበ የ“አስገቡኝ” ማመልከቻ በር መክፈቻ ይሆን? ይህንን መፈጸም የትግሬ ወራሪ ኃይል ካፈረሰው በላይ የራስን እጅ በራስ ቢላ መጉመድ ነው የሚሆነው። ኮምቦልቻና ደሴ በትግሬ ወራሪ ኃይል ቁጥጥር ሥር የወደቁት በማንም ሳይሆን እዚያው ከተሞቹ ውስጥ ተወልደው ባደጉ ትግሬዎችና ባንዳዎች ፊት አውራሪነት እንደሆነ ጋሻውና ዩሱፍ በተደጋጋሚ ነግረውናል።
ከላይ እንዳልኩት በሙያዊ ልሕቀቱ ከፍተኛ ሽልማት የሚገባው የአሚኮ ሥራ በትህነግ ደጅ ብዙ ውዥንብር ፈጥሯል። ወደ በቀል የሚወስድ ብስጭትም አስነስቷል፤ ሤረኛው ትህነግ ደግሞ ለአማራ ሕዝብ መቼም እንደማይተኛ “ሒሳብ አወራርዳለሁ” በሚለው ቃሉ ነግሮናል። የደረሰብን መከራና ስቃይ ሳንጠረጥር ከመታረድ ይልቅ ጠርጥረን ብንሳሳት ትክክል ነው ወደሚል ድምዳሜ አድርሶናል። የሆነው ሆኖ ግን ከጋዜጠኛነት ሙያ ጽዱ የሆነው የዕውቀት ጾመኛው አበበ በለው በግብርም ሆነ በምግባር በአሚኮ መስኮት ለመታየት አይመጥንም፤ ቢቻል ማስተካከያ ተደርጎ ለወደፊት ጥንቃቄ ቢደረግ ጥቆማ እሰጣለሁ።
ዳዊት በለው
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣበ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።
አምባው በቀለ says
ሻለቃው በድርቅ የተጎዱ ኢትዮጵያውያንን ጉረሮ ዘግቶ ከእርዳታ መስተባበሪያ ኮሚሺን ከወያኔ ባልተናነሰ መልኩ ኢትዮጵያን ገንዘብ እና ንብረት ዘርፎ ከወያኔ ባልተናነሰ መልኩ ወገኖቹን በረሃብ አለንጋ የገረፈ ያስገረፈ፤የፈጀ ያስፈጀ፤ቁጥር አንድ የኢትዮጵያ ጠላት ሲሆን የሚዘርፈውን ዘርፎ እና አዘርፎ ወደ ሁለተኛ እናት እና አባቱ አገር የመጣው የስልጣን ጥመኛነቱን ለማርካት አለቆቹ የደርግ አባላትን ገልጦ ስልጣን መያዝ ስለተሳነው ነበር።በመሠረቱ ይህ ሰው ስልጣንን እንደተመኘ ሳይሳከለት በሁለት እግሩ መራመድ እየተሳነው በሁዊል ቸር መገፋት ደረጃ ደርሶም የስልጣን ጥመኝነቱ መርካት ባለመቻሉ ኑዛዜም ስልጣን ሲሆን የሰው ልጅ አንድ እናትና አንድ አባት ሲኖረው ይህ ሰው ግን ከሁለት እናትና ከሁለት አባት የተጸነሰ የሰንበት ጽንስ ነው።በመሆኑም “ቢጽ ለቢጽ” እንደሚባለው አበበ በለውም ወስፋቱን ለመሙላት የሚያደርገው ውጣ ውረድ በመሆኑ በአማራ ሚዲያ እንዲሁም በሌሎች እንዳይቀርብ ጥንቢራው ማለቱ የተሻለ ነው።