የትህነግ 10 በደሎች - በተለይ በአማራ ሕዝብ! "ትህነግ"... (ትግራይ/ተጋሩ አላልሁም) የተሸነፈው በ1967 ነው። ማንም ቡድን ወይም ርዕዮተ አለም ሕዝብን ጠላት አድርጎ ማሸነፍ አይችልም። ግለሰቦች፣ የፊውዳሉ ስርዓት ጠላት ሊሆን ይችላል። ሁሉም አማራ ግን ጠላት ሊሆን አይችልም። ትህነግ እንጂ የትግራይ ሕዝብ ጠላት እንዳልሆነው ሁሉ። የትህነግ መሠረታዊ ትርክት (ድርሰት) በገሃድ የተተወነው ባለፈው ዓመት ነው። ትህነግ በተለይ በአማራ ሕዝብ 10 ዐበይት በደሎች ፈፅሟል። በእኔ ሚዛንና ምልከታ። 1) መልክዓምድራዊ ለውጥ (Demographic Change): ድህረ 1983 ማንነትን ባላገናዘበ መልኩ ወልቃይት፣ ጠገዴ፣ ዋግና ራያ ላይ መሬቱን በመውረር ሰዎችን አፈናቅሎል፣ ጅምላ ግድያ ፈፅሟል። ሴቶችን በመድፈርና አስገድዶ በማግባት የዲሞግራፊ … [Read more...] about “ትህነግን ለማጥፋት የሚደረግ ማንኛውም ነገር ቅዱስ ነው”
Opinions
የኔ ሃሳብ
የትህነግ አመራሮች ልጆቻቸውና የትግራይ ልጆች
የትህነግ አመራሮች ልጆቻቸው በጦርነት ውስጥ አያልፉም። እንቅፋትና ሾህ አያገኟቸውም ብቻ ሳይሆን ስለእሾህና እንቅፋት ኮንሴፕቱም የላቸውም። ልጆቻቸው በውጭ ዩኒቨርስቲዎች ተሞላቀው ይማራሉ፣ በዛው በውጭም ተንደላቀው ይኖራሉ። የራሳቸውን ልጆች በቅንጦት እያስተማሩና በድሎት እያኖሩ የትግራይ የደሃ ልጆችን ግን በመንግስት የሰላም አማራጭ ዕድል ተሰጥቷቸው (ያለምንም ቅድመ ሁኔታ በየትኛውም ቦታና ጊዜ ) ሳለ ጦርነትን እንዲመርጡና እንደቅጠል እንዲረግፉ ያበረታታሉ። ይቀሰቅሳሉ። የትግራይ ሕዝብ የጀመረውን ተቃውሞ አጠናክሮ ሊቀጥል፣ የቀረበለትን የሰላም ዕድል ወደጎን ገፍቶ ለጋ ልጆቹን ሳይገብር በጦርነት ያገኘው ትርፍ እንደሌለና ለሰላምም ያለውን ጠንካ አቋም መግለፅ ይገባዋል። የትግራይ ሕዝብ ከጦርነት ይልቅ ሰላምን ለመምረጡ ዋናው ምልክት ደግሞ የትህነግን የጦርነት መንገድ … [Read more...] about የትህነግ አመራሮች ልጆቻቸውና የትግራይ ልጆች
የስሪ ላንካው “FamilyCracy” – ከመዓቱ እስከ ተውኔቱ
የታሚል ታይገር ተገንጣይ አማፂያንን ከረጂም አመት ውጊያ በኋላ ድል ማድረጋቸው የብልሹ አሰራራቸውን ብሶት ማስታገስ አይችልም። የስሪ ላንካው መሪ ራጃፓክሳ ሊተገበሩ የሚችሉ የመፍትሄ ርምጃዎች ላይ የታየባቸው ዳተኝነት ይባሱኑ ህዝባዊ ቁጣውም ጨመረባቸውንጂ፤ የስሪ ላንካ ዜጎች ለከፍተኛ መከራ የዳረጋቸው ሙስና ብልሹ አስተዳደር ነበሩ። በተለይም ዋና ዋና የሀላፊነት ቦታዎች በዘመዳዝማድና ቤተሰብ የሰበሰበው FamilyCracy ነበር። በስሪ ላንካ የኢኮኖሚ ቀውሷ በረታ…የኢኮኖሚ ውድቀቷን bankruptcy ከወራት በፊት ማወጇ ይታወሳል። የሀብት የፀጋ የተስፋ ምድር እንዳልተባለች በየቀኑ ሳይበሉ የሚያድሩ ዜጎች መገለጫዎቿ እስኪመስሉ ተቸገሩ። የስሪ ላይካ ዜጎች ወደ አመፅ ተሸጋገረ። እውነተኛው የዜጎች መከራን እንደመልካም አጋጣሚ በመቁጠር የተሰራው የጂኦፓለቲካ ጨዋታ ግን አሳዛኝ … [Read more...] about የስሪ ላንካው “FamilyCracy” – ከመዓቱ እስከ ተውኔቱ
የወልቃይት አማራ የተሰቃየባቸው የትህነግ 15 ድብቅ እስር ቤቶች!
በሕወሓት ማጎሪያና ጭፍጨፋ እስር ቤቶች የተፈፀመው ዘግናኝ ታሪክ እንደ ሚከተለው ይቀርባል። እንደ አቶ ገብረ መድኅን ገለፃ በወቅቱ ሕወሓት ሓለዋ ወያነ (የወያኔ እስር ቤት) ወይም 06 (ባዶ ሸድሸተ -ባዶ ስድስት) ብሎ በማቋቋም በተለያየ የትግራይ አካባቢዎች ማጎሪያና ጭፍጨፋ ‘ካምፖች’ ነበሩት። እነዚህን የማጎሪያና የጅምላ የመጨፍጨፊያ ‘ካምፖች’ የመሰረተው ህቡር ገ/ኪዳን በሚባል ታጋይ (በኋላ በስኳር ኮርፖሬሽን ግዥ ክፍል ቡድን መሪ እና የሕወሓት የቁጥጥር ኮሚሽን አባል ሆኖ ሲሰራ የነበረ) ነው፡፡ አቶ ገብረ መድህን አርአያ እያንዳንዱ እስር ቤት (ሓለዋ ወያኔ 06) የተቋቋመበት ዓላማ የወልቃይት አማሮችን በጅምላ ለመፍጀትና የሕዝቡን መሬት ለመንጠቅ፣ ሕወሓትን የሚቃወሙ የትግራይ ተወላጆችን ለመግደል እንደሆነ ያብራራሉ። የግለሰቡ ገለፃ እንደሚከተለው አጥሮ ይነበባል። 1) … [Read more...] about የወልቃይት አማራ የተሰቃየባቸው የትህነግ 15 ድብቅ እስር ቤቶች!
“አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና ነው” አቶ ሃንጋሳ
በወለጋ የንፁሃንን ጭፍጨፋ እየተፈፀመ ያለው በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ነው ሲሉ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ ሃንጋሳ አህመድ ኢብራሂም ተናገሩ። አክለውም የኦሮሚያ ፕሬዘዳንት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ከስልጣናቸው እንዲነሱ ጠ/ሚ አብይ አህመድን በይፋ በፌስቡክ የቀጥታ ስርጭታቸው ጠይቀዋል። ከ 2 ቀናት በፊትም ጠባቂያቸው መገደሉን ተናግረዋል። አቶ ሀንጋሳ ትላንት ሁለት ሰዓት በፈጀውና ከ15 ሺህ በላይ ተመልካቾች በተከታተሉት የፌስቡክ የቀጥታ ስርጭት በኦሮምኛ (የተወሰኑ ቁልፍ ነገሮችን ደግሞ በአማርኛ) አስተላልፈዋል፡፡ የሚከተሉት ዋነኛ ነጥቦች ነበሩ: አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና እቅድና ተግባር ነው፣ አብዲ ኢሌ ሲነሳ ሶማሊያ ሰላም እንደሆነው ሁሉ ሽመልስ አብዲሳን ጨምሮ በክልሉ ያሉ ባለስልጣናትን እስር … [Read more...] about “አማራን ኦሮሚያ ውስጥ የመግደል እና የመጨፍጨፍ እቅድ የኦነግ ሳይሆን የኦሮሚያ ብልጽግና ነው” አቶ ሃንጋሳ
የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ
1. የገዳ ሥርዓት ጥንታዊ የኦሮሞ አርብቶ አደሮች (Primitive Oromo pastoral tribes) ለከብቶቻቸው ተጨማሪ የግጦሽ መሬትና የውሃ ምንጭ (natural resources) ለማግኘት ጎረቤቶቻቸውን ይወሩበት የነበረ ባህላዊ አደረጃጀት ሲሆን ጉዲፈቻና ሞጋሳ ደግሞ የኦሮሞን ባህል እና ቋንቋን በተወረረው ማኅበረሰብ ላይ ለመጫን የሚያገለግሉ ማስፈጸሚያ ስልቶች ናቸው። የአርብቶ አደሩን ማኅበራዊ፣ ወታደራዊና መንፈሳዊ እንቅስቃሴዎችን የሚመሩ፣ የሚያደራጁ፣ ተዋጊዎችን ለጦርነት መርቀው የሚልኩና በመሳሰሉት የስልጣን እርከን ላይ የሚገኙ የስርዓቱ የገዢ መደቦች አባ ገዳ፣ አባ ዱላ፣ አባ ላፋ፣ ሞቲ፣ ሉባ ወዘተ ተብለው ይጠራሉ። የገዳ ሥርዓት የኦሮምኛ ቋንቋ ተናጋሪ ለሆነው አርብቶ አደር ብቻ የሚያገለግል የአንድ ማኅበረሰብ ባህላዊ አደረጃጀት … [Read more...] about የገዳ ሥርዓት እና የኦሮሞ ገዢ መደብ
ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር
ዶ/ር አብይ አህመድ በተለያዩ መድረኮች ወልቃይት የበጌምድር አማራ መሆኑን በማያሻማ መንገድ በጠራ አገላለፅ ባረጋገጠበት መንገድ (የጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ፊርማ ነው)፤ ወልቃይት በአማራ ክልል መንግስት ስር እየተዳደረ ባለበት ሁኔታ፤ ወልቃይትን አብይ አህመድ ለወያኔ አሳልፎ ሊሰጥ ስለሆነ አማራ ከመከዳትህ በፊት ተነስ የሚሉ የግጭት ነጋዴዎች ድምፅ ማሰማት ሳይሆን ለእነሱ ጆሮ የሚሰጠው ሰው ቁጥር በዚህ ደረጃ መጠኑ መጨመሩ የሚያስደንቅና የሚያሳስብም ነው። እርግጥ ነው ጉዳዩ የማንም ሳይሆን የራሱ የመንግስት የPR ችግር የፈጠረው ነው። ዶ/ር አብይ አህመድ ለአማራ እንቆረቆራለን ወይም እንታገላለን ከሚሉት በላይ በወልቃይት ጉዳይ የሕዝቡን የዓመታት ጥያቄና ትግል እውቅና ሰጥቶ ወልቃይት የበጌምድር አማራ መሆኑን የጠራ አቋሙን በአደባባይ አረጋግጦ ለሕዝቡ ጥያቄ የራቀ ሳይሆን … [Read more...] about ወልቃይት: ቢመረንም ለመዋጥና ራሳችንን ለመመልከት እንሞክር
እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ?
ሕግ በረጅም ገመድ ያሰረው ጃዋር! ቅድሚያ “ኢትዮጵያዊ ፣ አባ ሜንጫ፣ አክቲቪስት፣ ተንታኝ፣ ፖለቲከኛ፣ አሁን ደግሞ “ሐጂ” ሆንኩ ያለው ጃዋር ማነው ነው? የሚለው ድብልቅልቅ ጉዳይ መመልከት ያሻል። ወይም የተለያዩ ማንነት ያለበት ጥያቄ መመለስ ግድ ነው። ጃዋር ወደ ፖለቲካ ሲመጣ በዳያስፖራ ያሉትን አገር ወዳዶች ለማማለል ፍጹም ኢትዮጵያዊ ሆኖ፣ በንግግሩ ሁሉን አስደምሞ ነበር ብቅ ያለው። ነገሮች መስመር ሲይዙለትና ደጋፊ ሲያገኝ እነዚህኑ ወደ ላይ የሰቀሉትን መሳደብና ኢትዮጵያን ማበሻቀጥ ጀመረ። በወቅቱ ተው ብለው አዛውንቱ የዳያስፖራ ምሁራን መከሩት። ወደላይ እየወጣ ስለነበር ይልቅ እኔን ብትሰሙ ይሻላል አላቸውና አልፏቸው ተስፈነጠረ። በቀጣይ ለኦሮሞን ትግል “አዲስ ትንፋሽ ነኝ” በማለት ራሱን መሪ አድርጎ ሾመ። የቀድሞ የኦሮሞ ታጋዮችን በተለይም ዕንቅፋት ይሆኑብኛል … [Read more...] about እብድ ይሻለዋል እንጂ አይድንም፤ ሐጂ ጃዋር አሁን ለምን ብቅ አለ?
ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል
ራሱን ኢትዮ 360 ብሎ ስለሚጠራው ቡድን ከዚህ በፊት በተደጋጋሚ በመረጃ ማንነቱን እና ለማን እንደሚሠራ አጋልጠናል። የትህነግ ተከፋይ ቡድን መሆኑን ከሁለት ዓመት በፊት በማስረጃ ተናግረናል። ዝርዝር መረጃውን ከዚህ በታች ይመልከቱ። “ዐቢይ የዘመተው አማራን አስፈጅቶ ጦርነቱ ሲያልቅ ለራሱ ዝና/ኢጎ ነው” የ360 የማክሰኞ አጀንዳየበረከት ስምዖን “ልጅ” የ360ው ኤርሚያስ፤ ከትህነጉ ጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረውየ360 ሤራ “ተንታኞች” መከፋፈል – “ጅብ ደም ከታየበት በጅቦች ይበላል”ኢትዮ 360 በገንዘብ ችግር ታንቄያለሁ፤ ራሴን ግምግሚያለሁና ዕርዱኝ አለኢትዮ 360 የወያኔ ሚዲያ መሆኑ ተረጋገጠ በዚህ ቡድን ውስጥ ያሉት ግለሰቦች ሲሻቸው መንፈሣዊ ሆነው በመቅረብ የሰውን ቀልብ ለመሳብ ይሞክራሉ። ሃብታሙ አያሌው አንዱ ተጠቃሽ ሲሆን ዘመድኩን በቀለ … [Read more...] about ኢትዮ 360 “የወያኔ፣ የጁንታ ሚዲያ ነው” – ባለከዘራው ጄኔራል
የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች
የገጠመን ጠላት ጦርነትን እንደኦክስጅን የሚቆጥር ያለጦርነት መሽቶ የማይነጋለት ደመ-ቀዝቃዛ ኃይል ነው። በፍፁም የተስፋ መቁረጥ ስሜት ውስጥ ያለው ወያኔ ኢትዮጵያን ለማፍረስ፣ ቀጠናውን ለማተራመስ እረፍት የለውም፡፡ ምክንያቱም በአንድ በኩል የት*ግሬን ወጣት ሊመግበው የሚችለው በዘራፊነት አሰማርቶ ብቻ ነውና፡፡ የወያኔ ሠራዊት ዘራፊና ወሮ-በላ (pillager) ሠራዊት ነው፡፡ ወሮ-በላ ሠራዊት ደግሞ ዓይኑን ጨፍኖ ለመዝረፍ የሚመጣ ኃይል ነው፡፡ መዝረፍ፣ ማውደም፣... ግብሩ ነው። ቆቦ፣ ወልድያ፣ ሐይቅ፣ ደሴ፣ ኮምበልቻ፣ ከሚሴ፣ ሸዋሮቢት፣ ንፋስ መውጫ፣... ዐቢይ ማሳያ ሆነው ይቀርባሉ። ከሐምሌ-ታህሳስ በዘለቀ የወሎ፣ ከፊል ሸዋና ጎንደር የጦር ወረራው ከዶሮ እንቁላል እስከ ፋብሪካ ማሽነሪ፤ ከአልባሳት እስከ ቀንድ ከብት፤ ከማህበራዊ የልማት ተቋማት እስከ እርሻ … [Read more...] about የጦርነቱ ስትራቴጂያዊ እውነታዎች