ቪኦኤ የአማርኛው ዝግጅት ክፍል ጃል መሮ በሚል ስም የሚታወቀውን ሽፍታ ሽፋን ሲሰጠው ስለምንነቱና በትክክልም እሱ ስለመሆኑ መረጃ ሰጥቶ አያውቅም። በቢቢሲ አማርኛና በቪኦኤ እንዳሻው ጊዜ መርጦ ወንጀሉን የሚያስተባብለው ጃል መሮ፤ ሲያሻው የሰጠውን ቃለ ምልልስ ስልክ ደውሎ እንዳይተላለፍ የሚያዝ ለመሆኑ ናኮር መልካ “ጃል መሮ ቃለ ምልልሱ እንዳይተላለፍ በጠየቁት መሠረት ትቼዋለሁ” ሲል ያረጋገጠው ሃቅ ነው። ቀደም ሲል በሃጫሉ ግድያ ኦነግ ሸኔ እጁ እንዳለበት በመታወቁ እጅግ የተቆጣውን ህዝብ ለማብረድ በናኮር መልካ አመቻችነት የቪኦኤ ዘጋቢ የሆነችው ጽዮን ግርማ ጃል መሮ በሬዲዮ ጣቢያው ቀርቦ ሳይፈተን እንዲፈነጭና ሃጢያቱን እንዲያራግፍ ፈቅዳለት እንደነበር ይታወሳል። ቢያንስ ማንነቱን መጠየቅ ሲገባ፣ ንጹሃንን በየቦታው እያደፈጠ ለሚጨፈጭፍ ሽፍታ፣ ሚዲያውንም ሌላ ጫካ በማድረግ … [Read more...] about ቪኦኤ በወለጋ ሆሮ ጉድሩ ለተጨፈጨፉ ኦነግ ሸኔን ከደሙ ንጹህ አደረገ
voa amharic
ቪኦኤና ጀርመን ድምጽ – የክልሎችን ኅልውና እንደ ህወሓት እየጣሱ ነው
በተለይ ካለፉት ሦስት ወራት ወዲህ የአሜሪካና የጀርመን ድምጽ ሬዲዮ ራሱን የትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ ብሎ የሚጠራውን መቀሌ የመሸገውን የወንበዴዎች ስብስብ (ትህነግን) እያገለገሉ ስለመሆኑ ከሚያቀርቡት ያልተመጣጠነ መረጃ መረዳት አያዳግትም። ለዚህም ይመስላል የተጠቀሱት ሚዲያዎች በተለይም የጀርመን ድምጽ ተቃውሞ እየቀረበበት ይገኛል። የጎልጉል የአዲስ አበባ መረጃ አቀባይ እንዳለው “አለቃና ተቆጣጣሪ ያለ አይመስልም” ሲል በተጠቀሱት ሚዲያዎች ከሚሰሩ ዜና አቅራቢዎች ጋር ቅርብ መሆኑንን የጠቀሰ አስተያየት ሰጪ እንደነገረው ይገልጻል። የአንድ ጋዜጣ ኤዲተር እንደነበር ገልጾ አስተያየት የሰጠው ባለሙያ “ሚዲያዎቹ አንዳንድ ጊዜ የሚያቀርቧቸው፣ በተለይም ከክልል ሪፖርተሮቻቸው የሚተላለፉት መረጃዎች ያስደነግጡኛል። ሁሉም እንዳሻቸው ሪፖርት የሚያቀርቡና የኤዲተሮች ሚና የሚታይባቸው … [Read more...] about ቪኦኤና ጀርመን ድምጽ – የክልሎችን ኅልውና እንደ ህወሓት እየጣሱ ነው