• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ቪኦኤ በወለጋ ሆሮ ጉድሩ ለተጨፈጨፉ ኦነግ ሸኔን ከደሙ ንጹህ አደረገ

March 19, 2021 04:32 pm by Editor 1 Comment

ቪኦኤ የአማርኛው ዝግጅት ክፍል ጃል መሮ በሚል ስም የሚታወቀውን ሽፍታ ሽፋን ሲሰጠው ስለምንነቱና በትክክልም እሱ ስለመሆኑ መረጃ ሰጥቶ አያውቅም። በቢቢሲ አማርኛና በቪኦኤ እንዳሻው ጊዜ መርጦ ወንጀሉን የሚያስተባብለው ጃል መሮ፤ ሲያሻው የሰጠውን ቃለ ምልልስ ስልክ ደውሎ እንዳይተላለፍ የሚያዝ ለመሆኑ ናኮር መልካ “ጃል መሮ ቃለ ምልልሱ እንዳይተላለፍ በጠየቁት መሠረት ትቼዋለሁ” ሲል ያረጋገጠው ሃቅ ነው።

ቀደም ሲል በሃጫሉ ግድያ ኦነግ ሸኔ እጁ እንዳለበት በመታወቁ እጅግ የተቆጣውን ህዝብ ለማብረድ በናኮር መልካ አመቻችነት የቪኦኤ ዘጋቢ የሆነችው ጽዮን ግርማ ጃል መሮ በሬዲዮ ጣቢያው ቀርቦ ሳይፈተን እንዲፈነጭና ሃጢያቱን እንዲያራግፍ ፈቅዳለት እንደነበር ይታወሳል። ቢያንስ ማንነቱን መጠየቅ ሲገባ፣ ንጹሃንን በየቦታው እያደፈጠ ለሚጨፈጭፍ ሽፍታ፣ ሚዲያውንም ሌላ ጫካ በማድረግ የጨፍጫፊዎችን መሪ ቀረርቶ ስታሰማ “አይ ቪኦኤ ኤዲተርም፣ አለቃም፣ የሌለው ቤት ሆኗል” በሚል በርካቶች ሐዘናቸውን መግለጻቸው አይዘነጋም።

አሁን ደግሞ ከአርባ በላይ ሰዎች በግፍ የታረዱበትና የተጨፈጨፉበት ማስረጃና እማኞች እያሉ በተመሳሳይ ጽዮን በሪፖርቷ ጃል መሮን እንደተለመደው በናኮር በኩል አስገብታ ማስተባበያ ሰርታለታለች። “አወቅሽ አወቅሽ” እንዲሉ በዜና ማመጣጠን ስም ይህን ዘግናኝና ህዝብን ያስቆጣ ጭፍጨፋ ኦነግ ሸኔ በነፍሰ ገዳይነቱ የታወቀበትን ስሙን ቀይሮ “የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት” በሚል እንዲያስተባብል አድርጋለች።

የሆሮ ጉድሩ ሰለባዎች እና የጭፍጨፋው ምስክር የሆኑት ድንጋጤ ባዛለው ድምጽ፣ ሳግ እየተናነቃቸው “ኦነግ ሸኔ አረደን” እያሉ ነበር ለጽዮን የነገሯት። ሆኖም ጽዮን ግርማ “የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት” ዘርና ሃይማኖት ለይቶ እንደማያጠቃ ጃል መሮ ሲነገራት “ኦነግ ሸኔ” ብሎ ስሙን እንዲያስተካክል አላደረገችም። በቃለ ምልልሱ ወቅት በስህተት ቢዘነጋ እንኳ በጽሁፍ መንደርደሪያ ሲሰራለት አልተስተካከለም። ይህም ከደም ጋር ተያይዞ የቆሸሸውን ወንጀለኛውን ኦነግ ሸኔ ስሙን በመቀየር ቪኦኤ ተባባሪ እንዲሆን ያስቻለ በራሱ ወንጀል የሆነ ተግባር ነው።

በሌላ አነጋገር ዱሮ ሲገድል የነበረው ኦነግ ሸኔ ነው፤ እሱ ያለፈ ታሪክ ነው፤ አሁን ያለው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ነው፤ ይህ ሠራዊት ደግሞ በዘርና በሃይማኖት ለይቶ አያጠቃም እንዲባል ያስደረገ ነው። ስለ ሁለቱም ቡድኖች ተወካይ ሆኖ የሚናገረው ደግሞ ጃል መሮ የተባለው በደም የተነከረ ወንጀለኛ ነው። በኦነግ ሸኔ የተበላሸውን ወንጀለኛ ስሙን አስረስቶ በኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ስም ሲያድስ ቪኦኤ ዋነኛ ተባባሪው ሆኗል።

ቅንጣቢ እንዳየ ጩሉሌ የገበያ ወሬ የሚጠባበቁት የዩቲዩብ ነጋዴዎች ምኑንም ሳይመረመሩ እንዲህ ያለውን “ክፉ ዓላማ” ያነገበ ዜና ከአድናቆት ጋር ፎቶ በማከል ያሰራጫሉ፤ ከግፍ ሳንቲም ይለቅማሉ። ጃል መሮ የሚባለው በከፍተኛ ወንጀል የሚፈለግ፣ ኢትዮጵያን ለማፍረስ በኦሮሞ ደም ለትህነግ የሚሰራ ሽፍታ “ግድያውን የፈጸሙት የአማራና የኦሮሞ ልዩ ኃይል ናቸው” ብሎ መርዝ እንዲረጭና ክፋቱን እንዲያራባ መፍቀድ በታሪክ የሚመዘገብ አገር የተፈጸመ ሸፍጥ ከመሆን አያልፍም። መልኩን የቀየረ ክህደትም ሊሆን ይችላል። ቢያንስ የኦሮሞ ልዩ ኃይል ገደለ የሚለውን እንቀበል ቢባል፤ አንድ ደም አፍሳሽ ሽፍታ የአማራ ልዩ ኃይል ወለጋ ገብቶ ገደለ ብሎ ሲናገር እንዴት “ለምንድነው የአማራ ኃይል ይህንን በገዛ ወገኖቹ ላይ የሚያደርገው ተብሎ አይጠየቅም”?

በተደጋጋሚ እንደሚነገረው በአገራችን ቋንቋዎች ለሚተላለፉ የውጭ አገር ሚዲያዎች የሚሠሩ ሪፖርተሮች ከመጣው ጋር ሲከንፉ፣ አገራቸውን ጉዳይ በተመለከተ ተሰፍሮ በሚሰጣቸው ልክ የድርጎ ሠፋሪ ጌቶቻቸውንና ቀጣሪዎቻቸውን አቋም ለማሟላት ከመኖር ውጭ ነጻነትን፣ “እኔ አገሬ ላይ ክህደትና ሤራን አላውጅም” በሚል የኢትዮጵያዊነት ጀዝም (ወኔ) ራሱን ያገለለ አንድም ባለሙያ እንደሌላቸው ሕዝብ ልብ ይበል። በዘመነ ደርግ ለወያኔ ሲሰሩ የነበሩ አሁንም አሉ።

በዘመን ህወሃት/ኢህአዴግ ሕዝብ ሲቀጠቀጥና ሲጨፈጨፍ ለወያኔ ሲዘፍኑ የነበሩ ዘጋቢዎች አሁንም አሉ። እነዚህ በሰብዕና ጥራት፣ በሐቅ፣ በኢትዮጵያዊነት መሥፈርት ቢለኩ ማለፍ የማይችሉ ሰሞኑን በአገራችን ላይ በተቃጣው የሚዲያ ዘመቻ ማንነታቸው ጥርት ብሎ ታይቷል።

የለውጡ ሰሞን ቀላቢዎቻቸው ፊታቸውን በትህነግ ላይ ሲያዞሩ አብረው የዞሩ፣ ዛሬ ደግሞ ትህነግ አፈር ሲገባ አፈሩን ልሶ እንዲነሳ አልቅሰው የሚያለቅሱ፣ መረጃ የሚያጣምሙና ሤራ የሚጎነጉኑ እንደ ጃል መሮ ዓይነት በደም የተጨማለቀ ሽፍታ እንዲታመን አዲስ ስም ሰይመው የሚተጉ እንዳሉ ሕዝብ ልብ ብሎ መከታተል ይገባዋል።

አገራችንን እንደ መዥገር እየመጠመጠ፤ እንደ ነቀርሳ እየገደላት የነበረውን ትህነግ በጦር አውድማ በቀላሉ ማምከን ብንችልም በሚዲያ የተነዛብን ፕሮፓጋንዳ ብዙ ጉዳት አድርሶብናል። ለዚህም ደግሞ በአገራችን ቋንቋ እና በሌሎችም በመረጃ ስም ወዳገራችን መርዛቸውን የሚተፉት የምዕራብ ዜና ወኪሎች በዋንኛነት ተጠያቂዎች ናቸው። እንደ ሕዝብ የምንሰማውንና የምናየውን በጭፍን የምንጋት ሳንሆን ከአገር ኅልውና ጋር በማገናዘብ፤ ግራ ቀኙን በማየት በብልሃትና በጥበብ የምንመላለስ ልንሆን ይገባናል።

ጎልጉል፤ የድረገጽ ጋዜጣ


ይህ ርዕሰ አንቀጽ የ“ጎልጉል: የድረገጽ ጋዜጣ™” አቋም ነው።

Filed Under: Editorial, Left Column Tagged With: jal mero, olf shanee, olf shine, operation dismantle tplf, tsion girma, voa amharic

Reader Interactions

Comments

  1. Yassin Kedir says

    March 20, 2021 08:59 am at 8:59 am

    ቪእኤ, የጀርመን ድምፅ እና TPLF ለኔ ምንም ልዩነት የላቸውም ፡፡

    Reply

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
  • ሕገወጡ ትህነግ ወጣቶችን ለዳግም ዕልቂት እያሰናዳ ለፈረንጆች “ኢትዮጵያን አውግዙልኝ” እያለ ነው June 11, 2026 12:57 am
  • በሐዘንና ግልፅ ደብዳቤ ስም የተሸፈነ የድህረ ምርጫ ሀገር የማተራመስ ስትራቴጂ June 10, 2026 12:19 am
  • የጽምዶ ልክፍት June 9, 2026 12:49 am
  • ገዳዩ ማነው? አስገዳዩስ ማነው? June 5, 2026 02:37 pm
  • ጽንፈኝነት ግን በኢትዮጵያ ምድር ፈጽሞ ቦታ የለውም! June 5, 2026 01:47 pm
  • የትብብሩ “ብናሸንፍም ፓርላማ አንገባም” መግለጫ “ወንበር ስታጡ ነው” የሚል ከፍተኛ ተቃውሞ አስነሳ June 4, 2026 12:04 am
  • አዲሱ የትራምፕ የምርጫ መመሪያ፡ የአሜሪካ ዲፕሎማቶችን አፍ ያስዘጋ፤ ተቃዋሚዎች ተስፋ ያስቆረጠ June 3, 2026 08:50 pm
  • “ኢህአፓ ከምርጫው በኋላ ይሰነጠቃል” May 29, 2026 07:07 pm
  • ሪፖርተር፡ “ስውር ተልዕኮ” – በከባድ ወንጀል ሊከሰስ May 6, 2026 11:55 pm
  • የፋኖ ኃይል በደረሰበት ጉዳት ሃምሳ ሺህ የሚጠጋ ትጥቅ ጥሎ ጠፋ April 29, 2026 02:27 pm
  • አዲሱ የቴድሮስ ካሳሁን 888 ኮድ፤ እንደ 666?! April 15, 2026 05:53 am
  • ምኑ ነው ያሳቃችሁ፤ ያስደሰታችሁ? April 2, 2026 10:52 am
  • የጀዋር መሃመድ የፖለቲካ ማንነት እና የባዕዳን ተልዕኮ April 2, 2026 10:16 am
  • ከግብፅ በዳያስፖራ ትርምስ ጠማቂዎች በኩል ፋኖ ወደ አዲስ አበባ የላከው “ስጦታ” March 27, 2026 09:14 am
  • “ሰላማዊ ታጋዮቹ” እነ ልደቱ ከአራጁ ሸኔ ጋር ተጣምረዋል March 25, 2026 01:04 pm
  • ጸረ-ኢትዮጵያዊ የሆነው የሪፖርተር አዘጋገብ March 19, 2026 11:54 am
  • የአውሬው ሪፖርተር ቀላቢዎች፡ የኦሮሚያ የልማት ድርጅቶች March 18, 2026 10:48 am
Copyright © 2026 · Goolgule