ሚዲያ ኃይል ነው፤ ሚዲያ አራተኛው የመንግሥት ክንፍ ነው፤ ሚዲያ … ያነሳል ይጥላል፤ ሚዲያ መልካሙን ስም ያዋርዳል፤ ሚዲያ የተበላሸ ስም ይቀድሳል፤ ሚዲያ ነፍሰ ገዳዩን ቅዱስ ያደርጋል፤ ሚዲያ ብርቱ ነው። በተለይ በውጪ መንግሥታት እየተደገፉ ወደ አገራችን የሚተላለፉት የቋንቋ ሚዲያ አውታሮች ውስጥ የሚሠሩት ስብዕናቸውን የሸጡና በሚከፈላቸው ዳረጎት ልክ ራሳቸውን አዋርደው፤ አንገታቸውን ደፍተው የሚኖሩት ሚዲያውን የከፈቱን ታማኝ ሎሌዎች፣ የፍላጎታቸው ማስፈጸሚያዎች ናቸው። ይህንን ስል ግን ለሙያቸው ያደሩና እንከን የማይወጣላቸው ስመጥር የሚዲያ ሰዎች መኖራቸውን ሳልዘነጋ ነው።
ጃል መሮ የተባለውን ነፍሰ በላ ወንበዴ፤ መሣሪያ ታጥቆ ምስኪን ገበሬ፣ እናቶችንና ሕጻናትን የሚያርድ በላዔ ሰብ አሁን ላለበት ቁመና ያበቃው በሚዲያ ውስጥ የሚገኙ ስንኩላን ናቸው። አንዳንዶቹ ልዩ ተልዕኮ ያላቸው ሲሆኑ ሌሎቹ ግን ሳንቲም ለቃሚ የኅሊና ድህነት በእጅጉ ያጠቃቸው ናቸው።
በውጭ አገር ያሉና በሚገኙበት አገራት መንግሥት በጀት የሚተዳደሩ የሚዲያ አውታሮችና ጋዜጠኞች ለትውልድ አገራቸው ጥቅም የሚሠሩ ሳይሆን ቀጣሪዎቻቸው የሚያገለግሉ ናቸው። ለምሳሌ የአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ርዕሰ አንቀጽ ባሰማ ቁጥር “ይህ የአሜሪካ መንግሥት አቋም ነው” ይላል። ይህንን የሚናገረው ግን ለኢትዮጵያውያን አድማጮቹ ነው። ዶይቸ ቨሌም (የጀርመን ድምፅ) እንዲሁም አገር ውስጥ ቁጭ ብሎ አገር አፍራሽ መረጃ የሚያትተው ቢቢሲም ከቪኦኤ ባይብሱ እንጂ በምንም ያልተለዩ ናቸው።
በአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ውስጥ የሚደረገውን አሻጥርና አገር የማፍረስ ተግባር እዚህ ላይ መዘርዘር ለቀባሪው አረዱት ይሆንብኛል። የበረከት ስምዖንን ዘመድና የወያኔን አቀንቃኝ ሔኖክ ሰማእግዜርን ከመቅጠር ጀምሮ ሲፈጸም የቆየው ሤራ ብዙ የሚያስብል ነው። ቪኦኤ ደርግን ሲቃወም በነበረበት ዐቅም ወያኔን በግማሹ እንኳ ሳይቃወም መቆየቱ አሁን ከወያኔ ጋር በምናደርገው የኅልውና ጦርነት አንጻር ተመልክተን ከበቂ በላይ ምላሽ ያገኘንበት ነው። አሜሪካ ወያኔን ለማዳን ብቻ ሳይሆን መልሳ ወደ ሥልጣን ለማምጣት የሄደችበት ርቀት ቪኦኤ በርግጥም የማን ልሳን እንደሆነ ቁልጭ አድርጎ የሚነግረን ሆኗል።
ለዚህም ነው ጃል መሮ ካለበት ጎሬ ፈልጎ ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ለቢቢሲም ሆነ ለአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ ቀላል የሆነላቸው። በተለይ በቪኦኤ ላይ እስካሁን ጃል መሮ ያደረጋቸውን ቃለ ምልልሶች የተከታተለ ሰው “ማነው ቃለ መጠይቁን ያደርግለት የነበረው?” ብሎ ቢጠይቅ ምላሹ ጽዮን ግርማ ነች የሚል ይሆናል።
በተለይ አምና በመጋቢት ወር ጃል መሮን በቀጥታ ስልክ ጽዮን ደውላ ባነጋገረችው ጊዜ ምናልባት የሚዲያው መመሪያ ስላልፈቀደላት ይሆናል እንጂ “ጃልዬ፤ ጃሎ፤ ጃሌ ፍቅር፤ …” ብላ ብትጠራው የምትፈልግ ትመስል ነበር። ቢመልስም ባይመልስም ማንነቱን መጠየቅ ቀዳሚ ተግባሯ ነበር። ዓላማው ምን እንደሆነ እና በወለጋ ህዝብ ለምን እንደሚታረድ ለዚህም የእርሱ ቡድን ስሙ እንደሚነሳ መጠየቅ ሌላው ኃላፊነቷ ነበር። ይናገራል ብዬ ሳይሆን አለመናገሩ በራሱ የሚፈለግ ስለሆነ ነው።
የጃል መሮንና የጽዮንን ፍቅር በተመለከተ መረጃ ስፈልግ ይህንን አገኘሁ፤ …
“ቀደም ሲል በሃጫሉ ግድያ ኦነግ ሸኔ እጁ እንዳለበት በመታወቁ እጅግ የተቆጣውን ህዝብ ለማብረድ በናኮር መልካ አመቻችነት የቪኦኤ ዘጋቢ የሆነችው ጽዮን ግርማ ጃል መሮ በሬዲዮ ጣቢያው ቀርቦ ሳይፈተን እንዲፈነጭና ሃጢያቱን እንዲያራግፍ ፈቅዳለት እንደነበር ይታወሳል። ቢያንስ ማንነቱን መጠየቅ ሲገባ፣ ንጹሃንን በየቦታው እያደፈጠ ለሚጨፈጭፍ ሽፍታ፣ ሚዲያውንም ሌላ ጫካ በማድረግ የጨፍጫፊዎችን መሪ ቀረርቶ ስታሰማ “አይ ቪኦኤ ኤዲተርም፣ አለቃም፣ የሌለው ቤት ሆኗል” በሚል በርካቶች ሐዘናቸውን መግለጻቸው አይዘነጋም። …
“የሆሮ ጉድሩ ሰለባዎች እና የጭፍጨፋው ምስክር የሆኑት ድንጋጤ ባዛለው ድምጽ፣ ሳግ እየተናነቃቸው “ኦነግ ሸኔ አረደን” እያሉ ነበር ለጽዮን የነገሯት። ሆኖም ጽዮን ግርማ “የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት” ዘርና ሃይማኖት ለይቶ እንደማያጠቃ ጃል መሮ ሲነገራት “ኦነግ ሸኔ” ብሎ ስሙን እንዲያስተካክል አላደረገችም። በቃለ ምልልሱ ወቅት በስህተት ቢዘነጋ እንኳ በጽሁፍ መንደርደሪያ ሲሰራለት አልተስተካከለም። ይህም ከደም ጋር ተያይዞ የቆሸሸውን ወንጀለኛውን ኦነግ ሸኔ ስሙን በመቀየር ቪኦኤ ተባባሪ እንዲሆን ያስቻለ በራሱ ወንጀል የሆነ ተግባር ነው።”
በወለጋ በቃላት ለመግለጽ በሚዘገንን መልኩ ለሚጨፈጨፈው ሕዝብ በቀጥታ ተጠያቂ የሆነው ሸኔ ሆኖ ሳለ ጽዮን ግን ጃል መሮ “እኔ የኦሮሞ ነጻአውጪ ሠራዊት” ነኝ ሲላት “እሺ አንበሳዬ” ማለት ሲቀራት ነው አሜን ብላ የተቀበለችው። ከላይ እንዳልኩት በወለጋ የሚታረዱት ወገኖቻችን ግን በየጊዜው የሚናገሩት “ኦነግ ሸኔ ጨፈጨፈን” በማለት ነው። በሌላ አነጋገር እስከ ቃለ መጠይቁ ድረስ በወለጋ ለተጨፈጨፉት ተጠያቂው ኦነግ ሸኔ እንጂ አሁን ጃል መሮ “የኦሮሞ ነጻ አውጪ ሠራዊት” ብሎ የዳቦ ስም የሰጠው ቡድን አይደለም።
ከላይ እንደተባለው በሃጫሉ ግድያም የሸኔ ቀጥተኛ እጅ እንዳለበት ስልክ ደውሎ ያስፈራራው የሸኔ አባል ምስክር ነው። ከዚህ ሌላ ሃጫሉ ራሱ “እየደወሉ ያስፈራሩኛል” ብሎ የተናገረ ሲሆን የቀብሩ ዕለት አምቦ ስታዲየም የኦነግ ሸኔ ባንዲራ መንጭቆ የወረወረው ዘመዱ ተግባር ብዙ የሚናገረው ነገር አለ። ይህንን ሁሉ የተከማቸ ወንጀልን ነው ጃል መሮ “እነ ሸኔ አይደለሁም” ብሎ ለጽዮን ሲነግራት “እሺ ፍቅሬ” ያለችው። ታዲያ ይህንን ለመሰለ የስም ዕድሳትና ውለታ የት ይገኛል?
መንግሥት ጃል መሮን እና ሸኔን ለማጥፋት ብዙ እየጣረ ነው። በኦሮሚያ ክልላዊ መስተዳድር ውስጥ ባለ የተቀናጀ የወንበዴ ቡድንና በሌሎች እገዛ የወያኔ ፍርፋሪ ለቃሚው ጃል መሮ በሸኔ ታጣቂዎቹ አሁንም ወገኖቻችንን ማረዱን ቀጥሏል። ወያኔ ስትታነቅ ሸኔም እንደሚተን ግን ምንም ጥርጥር የለም። ቢሆንም ሸኔን ሲያነግሡ የነበሩት እነ ጽዮንን ዝም ማለት አግባብ አይመስለኝም።
በተለይ ባሁኑ ሰዓት ወያኔን አስወግዶ ሸኔን አብሮ መሸኘት አግባብ ያለው ተግባር በመሆኑ ጃል መሮን በቁጥጥር ሥር ማዋሉ በቀዳሚነት ሊሠራበት የሚገባ ጉዳይ ነው። ይህንን ደግሞ መንግሥት የሚያጣው አይመስለኝም። ስለዚህ ጃል መሮን ለማግኘት ባሁኑ ሰዓት አዲስ አበባ የምትገኘውን የጃል መሮን “ሚስት” ጽዮን ግርማን መንግሥት “እንዴት ነሽ? ሰላም ነው?” ቢላት ጥሩ ይመስለኛል። የስልክ ቁጥሩን እና በስንት ሰዓት ሲደወልለት ስልክ እንደሚያነሳ ብቻ ከተናገረች በቂ ነው። “ጽዮን የት ትገኛለች?” ብሎ ለሚጠይቅ ደግሞ መልሱ ጥሬ ሥጋ ያለበት ቦታ በሙሉ አትጠፋም ነው የጥቆማ መልሴ። እኔም ጥሬ ስትቆርጥ ባጋጣሚ አይቼ ነው ይህንን ጥቆማ የሰጠሁት። በዚህ አጋጣሚ እሷንም ሆነ አብረው ከጥሬው የሚቆርጡትን በሙሉ በወለጋ የታረዱትን ወገኖቻችንን በዓይነ ኅሊናችሁ እየተመለከታችሁና በጽዮን ያላሰለሰ ልፋትና ትጋት ለዚህ ዕድል መብቃታችሁን እያመሰገናችሁ ጥሬውን በደማቸው አወራርዱት።
ናኮር ግርማይ ነኝ
“ጎልጉል፡ የድረገጽ ጋዜጣ የሕዝብ” እንደመሆኑ በ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ ሥር የድርጅቶችና የማንኛውም ግለሰብ ነጻ ሃሳብ የሚስተናገድ ሲሆን ከአንባቢያን የሚላኩልን ጽሁፎች በጋዜጣው የአርትዖት (ኤዲቶሪያል) መመሪያ መሠረት ያለ መድልዖ በዚህ ዓምድ ሥር ይታተማሉ። ይህ በጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣበ“የኔ ሃሳብ (Opinion)” ዓምድ የታተመ ጽሁፍ የጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ™ አቋም ሳይሆን የጸሃፊው ነው።
Leave a Reply