
“ለዐማራነቴ፤ ለኢትዮጵያዊያነቴ ህይወቴን እሰጣለሁ” እንዳልህ ይኼው ደማህ፤ ልክ እንደ አድዋው ጀግና ፊታውራሪ ገበየሁ “ህወሓትን ፈርቼ ስሸሽ ከኋላዬ ከተመታሁ አሞራ ይብላኝ፤ ከፊት ለፊት ስፋለም ከወደቅሁ ግን ልጆቼን አደራ” እንዳልህ ክንድህ ላይ በፈሰሰው የደም ጠብታ ቃልኪዳንህን አፀናህ። ባለፈ ጊዜ ለእረፍት መጥቶ ሚስቱ “እባክህ በልጆችህ ልለምንህ አትሂድ” ስትለው “ልጆቼ ከሀገሬ አይበልጡም” ነበር ያላት።
በርግጥ ይህ የአባቶቻችን ውርስ ነው። ዐፄ ቴዎድሮስ መቅደላ አፋፉ ላይ ሽጉጣቸውን ከወገባቸው ላይ መዘው ሊጨልጡት ባሉበት ቅፅበት ልጃቸው ልዑል አለማየሁን የወለዱላቸው እቴጌ ጥሩ ወርቅ “እባክዎትን ለአንድ ልጅዎት ለልዑል ዓለማየሁ ሲሉ እንኳን ይህን ሀሳብዎን ትተው ይቆዩለት” ቢሏቸው “ልጅ አለማየሁ ከሀገሬ ከኢትዮጵያ አይበልጥም። አንዲት ኢትዮጵያ በዐይኑ እንደዞረች ሞተ ብለሽ ንገሪው’ ነበር ያሏት። ታላቁ አርበኛ ደጃዝማች በላይ ዘለቀ የፋሽስት ጣሊያን ጦር ልጃቸውን ይዞ ከትግላቸው ሊያስተጓጉላቸው ሲሞክር “እንዳሻህ አድርጋት ልጅ ከሀገር አይበልጥም” ብለው ነበር የመለሱት። (ፋኖነት፣ 19)
ሻለቃም ከቤተሰቡ ይልቅ ኢትዮጵያዊ ዐማራነት አስቀደመ።
ለአገርና ለወገን የሚተርፍ ታሪክ ሠርቶ እንደ ተከበረ፣ እንደኮራና እንዳማረ የማለፍን የአባቶቻችን ጥልቅ ሚስጥር ስለሚያውቀው ጦር እየመራ ተዋጋ፤ ምሽግ ሰበረ፤ በመጨረሻም ክንዱ ላይ ቆሰለ። ሻለቃ አሁን ላይ በህክምና ይገኛል፤ እኔም በስልክ አነጋግሬው እንዲህ ነበር ያለኝ፣
” የሞርታሩ ፍንጣሪ አስወጥቼ እስከመጨረሻዋ እስትንፋሴ ድረስ እዋጋለሁ። ልጆቼ በዚች ቅፅበት ከጠላት ጋር እየተዋጉ ናቸው። ሞቴ ከእነሱ ጋር ነው። ስሞት ግን ትርጉም ያለው ሞት ነው የምሞተው። እኔ ሞቼ ከዚህ በኋላ ዐማራ እንደ ህዝብ ማኅበራዊ ኅረፍት እንዲያገኝ፤ ኢትዮጵያም እንደ ሀገር እንድትቀጥል ነው።”
የዐማራ ልዩ ኃይል፣ መከላከያ እና ፋኖ ስለምትከፍሉልን መሰዋእትነት እናመሰግናለን። (ታደለ ጥበቡ)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply