አሸባሪው ትህነግ ትጥቅ ይፍታ ተብሏል። አባላቱና ደጋፊዎቹ ትጥቅ አንፈታም እያሉ ነው። እፈታለሁ ቢል እንኳን ትህነግ ትጥቅ ዘርፎ ሲደብቅ የኖረ ድርጅት ነው። የትህነግ ዋናው ትጥቅ ግን የጦር መሳርያ አይደለም። የትህነግ የነፍስ መከፍ፣ የቡድን፣ ከባድ መሳርያው ፀረ አማራ ጥላቻ ነው። እስካሁን የፈፀመው ውድመት በፀረ አማራ ትርክት የተፈፀመ ነው።
1) አሸባሪው ትህነግ ተመስርቶ፣ የጎለመሰው በአማራ ጥላቻ ነው። በግላጭ አማራን የሚረግም ማንፌስቶ አርቅቆ፣ አባላቱን ብቻ ሳይሆን ህዝብን ወዝ የጠገበ ጥላቻ አስታጥቋል። ይህን ትጥቅ መፍታት አለበት። ይህ ትጥቅ የሚፈታው የአማራን ህዝብ ይቅርታ በመጠየቅ ነው።
2) የትህነግ ፀረ አማራ ጥላቻ ለአማራ ህዝብ ብቻ የተወሰነ አይደለም። ፀረ ኢትዮጵያም ነው። የኢትዮጵያ ታሪክን ከአማራ ጥላቻ ጋር አጋምዶ ኢትዮጵያን ቅኝ ገዥ አድርጓ አውግዟታል። በዚህ አስተሳሰብ መሰረት ነው የሀሰት ትርክት ያስተማረው። አማራን ለማጥቃት ብሎ የሸዋ ገዥ መደብ እያለ እስከ አሁን የሚያኝከው አማራውን ብቻ አይደለም። የአማራውን ያህል አይሁን እንጅ ኦሮሞውንም፣ ጉራጌውንም አብሮ ፈርጆታል። ኢትዮጵያን የአማራ ኢምፓየር አድርጎ “የአማራ ኢምፓዬር መፍረስ አለበት” ብሎ ነው ኢትዮጵያን አሁን ወደገባችበት ውጥንቅጥ ያስገባት።
3) ሰሜን ዕዝን ሲያጠቃ ከአማራ በተጨማሪ ኦሮሞዎች፣ ጉራጌዎች የተጨፈጨፉት በጥላቻ ነው። በአማራ የጀመረውን “ትምክተኛ” ለኦሮሞም ለሌላውም አብሮ አድሎታል። ስልጣን ላይ ያለውን ኃይል ትምክተኛ ነው የሚመራው በሚል ነው እንደ አዲስ ህዝብን የቀሰቀሰው። ለትህነግና ለሚቀሰቅሰው ህዝብ የሶማሊ ክልል ሙስጦፌ አማራ ነው። ስልጣን ላይ ያለው ኃይል አማራ ተብሎ ተፈርጇል። ትህነግ ህዝብን አስተባብሮ ሰራዊቱን ያጠቃው የትምክት ኃይል ነው ብሎ ፈርጆ ነው።
4) ሰሜን ዕዝም ሆነ ከዛ በኋላ ሰራዊቱ የተመታው በመሳርያ ብቻ አይደለም። ዋነኛው በጥላቻ ነው። አሁንም ትምክተኛ ሊገዛህ ነው እየተባለ የተቀሰቀሰ ህዝብ ሰራዊቱ አይን ላይ በርበሬ በትኗል። በድንጋይና ዱላ ቀጥቅጦታል። የሰራዊቱን መሳርያ የዘረፉት በጥላቻ ነው። አማራ፣ ትምክተኛ ሊያጠፋን ነው በሚል ትርክት ነው አገር እታደጋለሁ ብለው የሚያምኑትን የትግራይ ተወላጅ የመከላከያ ሰራዊት አባላት ጭምር ያስከዷቸው፣ አብሯቸው የቆሰለውን ሰራዊት እንዲመቱ ያደረጓቸው። በጥላቻ ነው የትግራይ ህዝብ 20 አመት ሙሉ ሲጠብቀው፣ ተቋም ሲገነባለት፣ ትግሬ አግብቶ ልጆች አፍርቶ ሌላ ቦታ ያሉ ወላጆቹን የረሳን ሰራዊት እንዲመታ የተደረገው።
5) ትህነግ የተጠቀመው የወረራ ስልት “ሕዝባዊ ማዕበል” የተሰኘ ነው። በዚህ ስልት ያሰማራው አብዛኛው ትጥቅ አልነበረውም። ትጥቁ ፀረ አማራ፣ ከፀረ አማራ ጥላቻ የተቀዳ ፀረ ኢትዮጵያ ጥላቻ ነው። አማራ የኢትዮጵያ ኢምፓዬር ተደርጋ ተስላለት፣ ስልጣን ላይ ያለው ኦሮሞም ይሁን፣ ሶማሊ፣ ሲዳማም ይሁን ወላይታ “ትምክተኛ” ተብሎ አማራ ቅብ ጥላቻ ታትሞበት ነው ወረራው የተፈፀመው። ሕዝባዊ ማዕበል ተብሎ ለወረራ የተሰማራው መሳርያ ሳይኖረው በጥላቻ ነው የዘመተው።
6) አሸባሪው ትህነግ በመሳርያ ሳይሆን በጥላቻ ነው አሸንፋለሁ ብሎ የሚያምነው። ከጫካ እንደወጡ “አማራ ላይ ሂሳብ እናወራርዳለን” አሉ። በዚህ መሰረት ህዝብን ሰበኩት፣ በዚህ መሰረት አወደሙ። ጨፈጨፉ። ያ ሁሉ ውድመት ከጥላቻ የመጣ ነው። በጦርነቱ አማራን የሚሰድቡ የድሮ ሙዚቃዎችን አራብቶ አሰራጭቷል። የስልጠና ሰነዶቹ ፀረ አማራ ናቸው። አማራ የሚሉት ስለ ኢትዮጵያ የሚያስበው፣ ከየትኛውም ብሄር ሆኖ ትህነግን የማይቀበለው ጭምር ነው።
7) በቀጥታ ጦርነቱ ብቻ ሳይሆን በመላ ኢትዮጵያ የሚቀሰቀሱ፣ ትህነግና ጋሻ አጃግሬዎቹ ያሉበት ግጭት የትህነግ ፀረ አማራ ጥላቻ የወለደው ነው።
ትጥቅ ፈትቶ እንኳ ነገ ጦርነት ልጀምር ቢል በፀረ አማራ ሙዚቃዎች፣ ሰነዶች ቢቀሰቅስ በሳምንታት ውስጥ ባዶ እጁን የሚዘምት በጥላቻ የናወዘ በርካታ ኃይል ማሰለፍ ይችላል። በርካታ በጥላቻ የሰከረ ኃይልን መሳርያ ከያዘ ሰራዊት ጋር አጋጥሞ ያስጨርሳል። ይህን ጥላቻ ማስፈታት ለትግራይ ህዝብም ህልውና ጭምር መፍትሄ ነው።
ስለሆነም ሰላም እንዲመጣ ከተፈለገ መጀመርያ ከትህነግ ብቻ ሳይሆን፣ በትህነግ ከተሰበከው ህዝብ ላይ ማራገፍ የሚያስፈልገው ፀረ አማራ ጥላቻን ነው። ትህነግ ከማንፌስቶው ጀምሮ በግልፅ ያራመዳቸው ፀረ አማራ ጥላቻዎችን ጥፋት መሆኑን፣ ህዝብን ማሳሳቱን፣ በቅስቀሳዎቹ ምክንያት ውድመትና ጭፍጨፋ መድረሱን አምኖ በአደባባይ ይቅርታ መጠየቅ አለበት። ፀረ አማራነትን የሚሰብኩ ሰነዶች፣ ሙዚቃዎች ለዘር ጭፍጨፋ መሳርያ በመሆናቸው ከአሁን በኋላ የተወገዙና የሚያስቀጡ መሆን አለባቸው። ጥላቻውን ትህነግ ብቻ ሳይሆን ሌሎች የትግራይ ድርጅቶችና ተቋማትም የተጠቀሙበት በመሆኑ ትህነግ በእነዚህ አካላትና በሕዝብ ስም የአማራን ሕዝብ በግላጭ ይቅርታ ከጠየቀ ብቻ ነው ሰላም ሊመጣ የሚችለው። (ጌታቸው ሽፈራው)
ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣ
Leave a Reply