የአማራ ልዩ ኃይል፣ ኢትዮጵያ ችግር በገጠማት ወቅት እንደ ብሔራዊ ጦር ያገለገለ የአገር ዘብ ነው። አማራን አዋርዳለሁ ብሎ የመጣውን ደግሞ ልኩን አሳይቶታል። የዘንድሮው ጀብዱማ ልዩ ነው። ትህነግ በሰላም ስምምነት ከባድ መሳርያ ጠጋግኖ አስረከብኩ ከማለቱ በፊት የአማራ ልዩ ኃይል በቡድን መሳርያ ከባድ መሳርያ ማርኮታል።
በአስቸጋሪው ወቅት የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የአማራ ልዩ ኃይልን አምኖበት “ከባድ መሳርያውን እንካ ተዋጋበት” ብሎት ተዋግቶ ድል አምጥቶበታል። ይህ ሰራዊት ኢትዮጵያን ለማዳን ከትህነግ ጋር ተናንቆ ክብር ያስጠበቀ የአገር ባለውለታ ነው።
ትህነግ ከባድ መሳርያ ለመስጠት ብቻ አይደለም፤ በክፋቱ ባያስረክብ እንኳ ትጥቅ ለመደበቅም የተገደደው በእነዚህ ነብሮች መስዋዕትነት ጭምር ነው። ትህነግ ዓለምን ለምኖ ተኩስ ይቁምልኝ ያለው የእነዚህን ጀግኖች ተኩስንም ነው። ትህነግ ከወረረው ቀጠና ወጥቶ ወደ ጉድጓዱ የሸሸው በእነዚህ ጀግኖች መስዋዕትነት ጭምር ነው። ትህነግና ወዳጆቹ እምበር ተጋዳላይን ትትው ሰላም ሰላም ያሉት በእነዚህ አንበሶች ጠንካራ ክንድ ጭምር ነው። አማራ ብቻ ሳይሆን ውለታ የሚያውቅ፣ አገሩን የሚወድ ኢትዮጵያዊ ሁሉ ይኮራባቸዋል። ትህነግና ወዳጆቹ ደግሞ ሰላም አሉ ቅብጥርጥስ የእነዚህ ጀግኖች ክንድ ያረፈበት ጠባሳቸውና ሽንፈቱ እየጠዘጠዛቸው ይቆያል።
የሰላም ስምምነት እያለ ካድሬው በአደባባይ የሚያወራበትን እነዚህ ጀግኖች ከወንድሞቻቸው ጋር ሆነው ባመጡት ድል የተገኘ ነው። በእነዚህ ጀግኖች ምክንያት ጠ*ላ*ት አንገት ደፍቷል። ወገን አንገቱን ቀና አድርጓል!
ይህ ጦር እነ ስብሃት “አከርካሪውን ሰብረነዋልና አይነሳም” ካሉት ከአማራው አብራክ የወጣ ነው። የራሱን ህዝብ ብቻ ሳይሆን እንደ አባቶቹ የአገር ክብር ያስጠበቀ ኃይል ነው። ትህነግ እያፈረ ይመሰክራል! የኢትዮጵያ መከላከያ ዛሬም በኩራት መስክሯል።
ፎቶው ትህነግን እስከ ሰፈሩ ድረስ ያጥረገረገው የአማራ ልዩ ኃይል ከግዳጅ ሲመለስ የሚያሳይ ነው። የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ አንግቦ የሚመለሰው የመከላከያ ሰራዊቱም፣ መንግስትም፣ ጠላትም የሚያውቀው አገራዊ ግዳጁን ተወጥቶ ሲመለስ ነው። ይህ ባለውለታ ጦር ከመከላከያ ጋር ለግዳጅ ትህነግ ቀጠናዬ ነው እስከሚለው ድረስ ሲያስጨንቀው ወዳጅም ጠላትም አይቷል። ይህ ጀግና ጦር የፈፀመውን ጀብዱ፣ የሰራውን ታሪክና ውለታ ሳስብ ደስታዬ ወደር የለውም!
dubale kasemay says
lairs with inferior complex always bosting can do nothing,but tring to creat problems to the nation.for the last 150 yr. what did Amara did for Ethiopia ? poverty war torture diseaseand what not.Individuals and some groups areconsidering themselvs important among the Amaras and exploit Amara mas they are arrogant embicilsand morons.They travel from one place to the other for begging or to find food and shelter;after while they want to be a master;shame on them.