WhatAboutism ስትራቴጂው በሰዎች ባህሪ ውስጥ ብቻ ሳይወሰን በፖለቲካ እሰጣገባዎች ውስጥም የሚተገበር ሆኗል፤ ወቀሳ እና ትችት ሲሰነዘር የወቃሽ መሰል ወንጀል በአፃፋነት ማቅረብ…። Whataboutism እንደ ፖሮፓጋንዳ ስትራቴጂ ቆየት ቢልም በኮቪድ 19 ሰሞን ጡዘት ላይ የደረሰበት ነበር። የኮቪድ መነሻ ቻይና ነች የሚለው የምዕራባዊያን የሚዲያ ዘመቻ ከቻይና በተጨማሪ ሩሲያን ያካተተ ቅንጅታዊ የመልስ ምቶይ እንዲያይሉ ያደረገ ነበር። የቻይና እና ሩሲያ ባለስልጣናት አሜሪካ በቤተ ሙከራ ፈጥራ አሰራጨቻቸው የሚባሉትን የበሽታ ዝርዝሮች ቆየት ያሉ ፋይሎች እየፈለፈሉ ይጠቅሱ ነበር። የራሳቸው የምዕራባዊያን ተቋማት ቀደም ሲል ያወጧቸውን ጥናታዊ ማጋለጫዎች እንደማጠናከሪያ መጠቀማቸው ሞስኮ እና ሩሲያን በ whataboutism ፕሮፖጋንዳው በለስ ሆኖላቸዋል። “Whataboutism” … [Read more...] about WhatAboutism በመረጃ ‘ጦርነት’ ውስጥ