• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

WhatAboutism በመረጃ ‘ጦርነት’ ውስጥ

September 5, 2022 04:51 pm by Editor Leave a Comment

WhatAboutism ስትራቴጂው በሰዎች ባህሪ ውስጥ ብቻ ሳይወሰን በፖለቲካ እሰጣገባዎች ውስጥም የሚተገበር ሆኗል፤ ወቀሳ እና ትችት ሲሰነዘር የወቃሽ መሰል ወንጀል በአፃፋነት ማቅረብ…። Whataboutism እንደ ፖሮፓጋንዳ ስትራቴጂ ቆየት ቢልም በኮቪድ 19 ሰሞን ጡዘት ላይ የደረሰበት ነበር። የኮቪድ መነሻ ቻይና ነች የሚለው የምዕራባዊያን የሚዲያ ዘመቻ ከቻይና በተጨማሪ ሩሲያን ያካተተ ቅንጅታዊ የመልስ ምቶይ እንዲያይሉ ያደረገ ነበር። የቻይና እና ሩሲያ ባለስልጣናት አሜሪካ በቤተ ሙከራ ፈጥራ አሰራጨቻቸው የሚባሉትን የበሽታ ዝርዝሮች ቆየት ያሉ ፋይሎች እየፈለፈሉ ይጠቅሱ ነበር። የራሳቸው የምዕራባዊያን ተቋማት ቀደም ሲል ያወጧቸውን ጥናታዊ ማጋለጫዎች እንደማጠናከሪያ መጠቀማቸው ሞስኮ እና ሩሲያን በ whataboutism ፕሮፖጋንዳው በለስ ሆኖላቸዋል።

“Whataboutism” በዚህ ስያሜው ጥቅም ላይ የዋለው 1974 እኤአ በ Sean O’Conaill ነበር። በወቅቱ “The Irish Times” ላይ ለጥፋታቸው ሲጠየቁ “እገሌስ ቢሆን..” ሲሉ የሚመልሱ ሰዎችን ባህሪ “Whatabouts” በማለት ገልፀዋቸው ነበር፤ አይሪሽ ታይምስ ላይ ባስነበቡት መጣጥፋቸው።ሮማውያንም መሰል ባህርያትን የሚገልፁበት ላቲንኛ አላቸው፤ እሱም “tu quoque,” ሲሆን “you, also” ወይም “አንተ ራሱ..” የሚል ፍቺ ይኖረዋል።በቀዝቃዛው ጦርነት ወቅትም ይህ የፕሮፓጋንዳ ዘዴ ጥቅም ላይ ስለመዋሉ ድርሳናት ይጠቅሳሉ። በተለይም ሶቭዬት ህብረት የአሜሪካን የጥቁር ዜጎች በደል በተደጋጋሚ በመተቸት ተጠቅማበታለች ይባላል።

የቻይና WhatAboutism ስትራቴጂ

Whataboutism የሚሰነዘርን የሰላ ትችት ፀጥ ለማሰኘት አገራት ይጠቀሙበታል። ይህ ስትራቴጂ የኮቪድ 19 ወረርሽኝን ተከትሎ ከመቸውም በላይ ተሰርቶበታል። የወረርሽኙን ተጠያቂ ቻይና እንድትሆን፤ ከዚህ ሲሻገርም የቻይናን ገፅታ በአለማቀፍ ደረጃ ለማጠልሸት አሜሪካና ሼሪኮቿ በወቅቱ ለጀመሩት የሚዲያ ዘመቻ ቤይጂንግ ዝም አላለችም። ቻይና ሆዬ “እኔ አይደለሁም እመኑኝ” በማለት ስትለማመጥ አሊያም በማስረጃ አስደግፋ ስትንደፋደፍ አልተገኘችም። ይልቁንም ምዕራባዊያኑ ከኢቦላ እስከ ኤችአይቪ እንዲሁም የተለያዩ የ”ፍሉ” አይነት ወረርሽኞችን ስለመፈብረካቸው የራሳቸውን ምዕራባዊ ጥናቶች እያጣቀሰች ትጠዘጥዛቸው ያዘች እንጂ…። ስለ ኡግሁር ሙስሊሞች የመብት ጥሰት ሲወቅሷት በምላሹ አሜሪካና ሸሪኮቿ በኢራቅ በሶሪያ በየመን በኮሶቮ በሊቢያና በሌሎችም አገራት በሚገኙ ሙስሊሞች የፈፀሙትን ግፍ መዘርዘር የቤይጂንግ WhatAboutismማዊ የመልስምት ነበር።

የ Black lives Matter ዘመቻን በመደገፍ የተቃውሞው አካል ከመሆንም ቻይናን ያገዳት አልነበረም። ታዲያ ዘዴው ቻይናን በእጅጉ የጠቀመ ነው የሆነው። ዘመኑ ዲጂታል ነው።ዲጂታል ሚዲያውን አጥብቃ በመቆጣጠር የምትታወቀው ቻይና ፋይዳውንም ጠንቅቃ ትገነዘባለች። ፊቷን ወደ ትዊተር አዞረች። ኮቪድ በተነሳበት ወቅት ከመንደሪን በተጨማሪ በእንግሊዝኛ ቋንቋም ትዊተር ላይ ተከሰተች። Wolf Warriors የሚል አለማቀፍ ስያሜ በሂደት የተቸራቸው ዲፕሎማቶቿ የትዊተር ጀግኖች ሆነው ዘመቱ። በወቅቱ የቻይና ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት የትዊተር ገፁን በእንግሊዝኛ ሀ ብሎ ከፍቶ በመጀመሪያው ሳምንት 16 ሺ ተከታይ ነበር ያገኘው። አሁን ላይም ተተኩሰዋል። እድሜ ለውጭ ጉዳይ ምኒስትር ቃል አቀባያቸው “Liyu ziyan” የማይመክቱት የትዊተር ፊታውራሪ ወጣው። የቻይና ትዊተራዊ wolf warriors ለበርካታ ምዕራባዊ የጥናት ተቋማት የምርምርና መጣጥፎች አጀንዳ ለመሆን መብቃታቸው የስኬታቸው ማሳያ ነው። ቃሉን አስገብታችሁ ጎግል ብታደርጉ ማአት ጥናት ታገኛላችሁ።

ጥናትና መጣጥፎቹ ቤይጅንግ እንዴት? በምን መንገድና በምን ስትራቴጂ? ወዘተ ከሚለው ርዕሳቸው በተጨማሪ “የቻይናን Wolf Warriors” እነ አሜሪካ እንዴት መመከት እንደሚችሉ..” መላ ለመዘየድ የተደጉ መኖራቸውን ስንመለከት ደግሞ ቤይጂንግ ከመከላከል ተሻግራ ከባድ ጥቃት ላይ መሆኗን እንረዳለን። ለቻይና የ WhatAboutism የፕሮፓጋንዳ ስኬት ተመሳሳይ ፀረ-አሜሪካ አቋም የሚያራምዱ አገራትን የዲጂታል ዘመቻ ከጎኗ ማሰለፍ መቻሏ ተጨማሪው ስትራቴጂ ነው። በኮቪድ ዙሪያ የተከፈቱባትን ስም ማጥፋቶች ለመመከት የብራዚል መሪዎች ሳይቀር ትዊተር ላይ ዘምተውላታል። በተለይ ሩሲያ ደግሞ በወታደራዊ፣ በኮቪድ ዲፕሎማሲ እና በጂኦፖለቲካዊ ጉዳዮች ሁሉ ከቻይና ጋር መሳ ለመሳ እንደተሰለፈች ነው የምትገኘው። እንደ RT የመሳሰሉ የሩሲያ አነጋጋሪ ሚዲያዎች በትዊተር ገፃቸው ጭምር ቤይጅንግን እንዲደግፉ ተደርጓል።

ከቻይና ዲፕሎማቶች፣ ባለስልጣናት፣ ከቻይና ሚዲያዎች ወዘተ የሚለጠፉ ዘመቻዎች በሩሲያ ባለስልጣናትና ሚዲያዎች በተመሳሳይ ይለጠፋሉ፣ ሼር ይደረጋሉ፤ ታግ እና ኮመንትም በተመሳሳይ። በአጭሩ በቅንጅታዊ የትዊተር ጦር አውድማዎች ላይ የቻይና Wolf Warriors ድል በድል እንደሆኑ ነው የሚገኙት።[ ቻይናና አጋሮቿ ከአሜሪካና ጭፍሮቿ እያደረጉት በሚገኘውና በዚህ መጣጥፍ ርዕሴ ላይ “አንደኛው የዓለም የመረጃ ጦርነት” ብዬ ለመሰየም አሳማኝ ሆኖ ባገኘሁት የትዊተር ላይ ትንቅንቅ ] የትዊተር ጦር በ WhatAboutism ስትራቴጂ ለኢትዮጵያበአገራችን ላይ ያነጣጠረው ውሸት-መራሽ አለማቀፍ የዘመቻ አውድማው ዲጂታሉ አለም ነው። ከዚህ የተንሸራሸረው የሀሰት ምርት ወደ ማቀነባበሪያዎቹ የሀያላን ፖሊሲ አውጭዎች የሚደርሰው።

አገራችን “Wolf Warrior” ከተሰኘው የቻይና ትዊተራዊ የመረጃ ጦርነት ስትራቴጂ መቅሰም የግድ በሚል ወቅት ላይ ነን። ሰቅዘው የያዙን ምዕራባዊያንን መፈናፈኛ እያሳጡ የሚገኙ አገራት በ”ጠላቴ ጠላት” ከኛ ጎራ ናቸው። እንዳጋጣሚም በተለያዩ ዘርፎች አጋሮቻችንም ናቸው። የ Wolf Warrior ጦር ባለቤትና በ WhatAboutism ስትራቴጂም መሪዎች ናቸው። ይህን አካሄድ አገራችን መተግበር የምትችለው ሲሆን ታተርፍበት ዘንድም የተመቹ ነገሮች የሞሉበት ነው። ዜጎች ባለስልጣናት ታዋቂ ሰዎች ዲፕሎማቶች ለኢትዮጵያ የትዊተር Wolf Warrior እንሁን። ሳንውል ሳናድር፤ (በተቻለ ፍጥነት) አሁኑኑ!ጉልበተኛ አገራት በፍትህ ሚዛን መለካት በይፋ ማቆማቸውን እያየን እየተመለከትን እኛ በሞራላዊ- እውነታዊ አካሄድ ላይ ሙጥኝ ማለት መከራችንን ያራዝማል። WhatAboutism ባለስልጣናትና ዲፕሎማቶቻችን ሊጓዙበት ግድ ይላል። በዲጂታሉ ዓለም በተለይም ትዊተርን የተቆጣጠረ ታላላቁን ሚዲያ ተቆጣጠረ፤ ታላላቁን ሚዲያ የተቆጣጠረ የሃያላን አገራት ፖሊሲ አውጭዎች ላይ ተፅዕኖ አሳረፈ፤ በዚህም በአለማቀፍ የዲፕሎማሲ ውድድር አሸነፈ። ይህ አካሄድ በውሸትም ሆነ በእውነት ጎዳና ለአለማቀፍ የዲፕሎማሲ ሚዛን “SI-Unit” ሆኖ ይገኛልና።

የዓባይ ልጅ Esleman Abay

Print Friendly, PDF & Email
facebookShare on Facebook
TwitterTweet
FollowFollow us

Filed Under: Middle Column, Opinions Tagged With: operation dismantle tplf, whataboutism

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

በማኅበራዊ ገጾቻችን ይከታተሉን

Follow by Email
Facebook
fb-share-icon
Twitter
Tweet

Recent Posts

  • “አስደንጋጭ”! 1 ሚሊዮን ከሚጠጋ ተፈታኝ ተማሪ ወደ ዩኒቨርሲቲ የሚገባው 30 ሺህ (3.3%) ብቻ ነው  January 27, 2023 09:11 am
  • የማይዘነጋዉ የኢትዮጵያዊያኖች የጀግንነት ተጋድሎ ታሪክ፡- ኮሎኔል ባጫ ሁንዴ (ታጠቅ) January 27, 2023 06:12 am
  • ጎርጎራ – የመጻዒው ዘመን ሙሽራ! የዉበት ፈርጥ! January 17, 2023 04:18 pm
  • ሁለተኛው መስቀል አደባባይ January 17, 2023 04:13 pm
  • በአቡዳቢ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን January 17, 2023 04:08 pm
  • በንፋስ ስልክ ላፍቶ ስምንት የመሬት ሌቦች ተያዙ January 16, 2023 11:36 am
  • ሺሻ ሲያስጨሱ በተገኙ ሆቴሎችና የምሽት ጭፈራ ቤቶች ላይ እርምጃ ተወሰደ January 16, 2023 08:50 am
  • በሐሰተኛ መታወቂያ የደኅንነት አባል ነን ብለው ሲያጭበረብሩ የነበሩ ተያዙ January 13, 2023 02:03 pm
  • ተሽከርካሪ ወንበር ለትግራይ – “ናይ ኣካል ጉዱኣት ተሽከርካሪ ዘለዎ ወንበር” January 12, 2023 07:17 pm
  • የአማራው ኩራት፣ የኢትዮጵያ ዘብ፣ የትህነግን ቅስም ሰባሪ! January 12, 2023 04:00 pm
  • በኢትዮጵያ ላይ የተጣሉ ማዕቀብ እና ሌሎች አስገዳጅ ሕጎች ሙሉ ለሙሉ ተሰረዙ January 12, 2023 01:52 pm
  • የቻይና ዕዳ ስረዛ “Payday Loan Diplomacy” ወይስ ኢትዮጵያን ያዳነ ተግባር? January 12, 2023 11:00 am
  • የአዲስ አበባ አስተዳደር ከቋንቋ ጋር በተያያዘ ውሳኔ አስተላለፈ January 12, 2023 10:46 am
  • “አምባሳደሩ” የቀድሞ ጌቶቻቸውን እንዲያቋቁሙ ተሾሙ January 11, 2023 03:47 pm
  • መከላከያ ሸኔን የሚዋጉ ሚሊሻዎችን አሠልጥኖ አስመረቀ January 10, 2023 05:37 pm
  • በሰባት ተጠርጣሪዎች ላይ ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ January 10, 2023 03:36 pm
  • የሽግግር ፍትሕ ፖሊሲ አቅጣጫ January 6, 2023 03:26 pm
  • “ከዕብሪቱ አስተንፍሰነዋል” – ኢሳያስ January 2, 2023 07:29 pm
  • [ኢትዮጵያን] “አስታክኮ ኤርትራን መውጋት ለሚፈልግ ኃይል አንተባበርም” January 2, 2023 07:11 pm
  • የ፰ ወር ሕጻንና ጨቅላ ወንዶች የሚደፈሩባት ትግራይ December 14, 2022 02:49 pm
  • “ሰውን ለመርዳት ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው” የደጎች አውራ የመቄዶኒያው ቢንያም በለጠ December 14, 2022 09:59 am
  • “የሀብት ምዝገባ መረጃው ለሕዝብ ክፍት ይደረግ “ December 13, 2022 10:30 am
  • የኢትዮጵያ ዓለምአቀፋዊ የሌብነት ደረጃ December 13, 2022 09:42 am
  • ለብረት አቅላጮች ለመሸጥ በኤሌክትሪክ የብረት ማማዎች ስርቆት የ100 ሚሊዮን ብር ኪሳራ December 13, 2022 09:26 am

ጎልጉል የድረገጽ ጋዜጣን በኢሜይል ለማግኘት ይመዝገቡ Subscribe to Golgul via Email

ከዚህ በታች ባለው ሣጥን ውስጥ የኢሜይል አድራሻዎን ያስገቡና “Subscribe” የሚለውን ይጫኑ፡፡
Enter your email address to receive notifications of new posts by email.

Copyright © 2023 · Goolgule