
ትህነግ አሸንፎ ቢሆን ኖሮ …
- ድርድሩ የተደረገው ትህነግ ደብረብርሃንን፣ ባህርዳርን፣ ጎንደርን ይዞ ቢሆን ኖሮ ትጥቅ ይፍታ ይባል የነበረው ጥምር ጦሩ ነበር።
- ክብር ለጀግኖቻችን ይሁንና ድርድሩ የተደረገው ባለፈው አመት ምዕራባውያን ዲፕሎማቶቻቸውን ባስወጡበት ወቅት ቢሆን ኖሮ ጥምር ጦሩ ያለ እንቅፋት ወደ መቀሌ ይግባ ሳይሆን፣ ትህነግ ወደ አዲስ አበባ ይግባ ነበር የሚባለው።
- ክብር ለጀግኖቻችን ይሁንና፣ አምና ትህነግ እንደወረረን የባሰ ገፍቶ ቢሆን ኖሮ የጊዜያዊ አስተዳዳሪ መዳቢው ትህነግ ነበር። ያውም እንደህዝብ እንድንኖር ከፈቀደልን።
- ክብር ለጀግኖቻችን ይሁንና እንደ ጠላቶቻችን ቢሆን ኖሮ የትህነግ ጀኔራሎች ነበሩ ትጥቅ አስፈችዎች።
- ክብር ለጀግኖቻችንና ወልዲያና፣ ላሊበላን፣ ጋሸናና ደባርቅን ይዘው አልተደራደሩም።
- ክብር ለጀግኖቻችን ይሁንና አላማጣ ትህነግ ያቋረጠው መብራት ተቀጥሎላታል። ዛሬ ወልቃይት ጠገዴ ነገ የሰሜን ዕዝን ውለታ በትልቅ ድግስ ታከብራለች።
- ክብር ለጀግኖቻችን ይሁንና፣ ትህነግ አዲስ አበባን ከብቦ ቢሆን ኖሮ አንድ ሰራዊት የሚባለው ተበትኖ፣ የአገር ሰራዊት ለመሆን ይሰባሰብ የነበረው የትህነግ፣ ኦነግ፣ ጉምዝ ታጣቂ ወዘተ ነበር
ክብር ለጀግኖቻችን ይሁን!
ግን! ነገም ሌላ ፈተና አለብን! ትህነግ አይታመንም። ካልሰራን መቸም ችግሩ ይመጣል። አንድ ካልሆንን በርካታ ፈተና ከፊታችን አለ።
ጌታቸው ሽፈራው
የሃገር መከላከያን የተዳፈሩ፣ ያረዱ፣ አገር ያስቆረሱ፣ አገር ያስወረሩ፣ ህዝብን ከህዝብ ያባሉ፣ አማራን ያስጠሉ፣ መንግሰትን አላውቅም ያሉ፣ ሃገር የዘረፉ፣ ትውልድ ያመከኑ…… ቢያንስ ለሃምሳ ዓመት ሲያደሙን የኖሩ አሁንም ይህንኑ እንዲፈጸሙ መፍቀድ ኣሳዛኝ ነው፡፡ ኢህአዴግ ነው የሚታየኝ!!!!!!
ድርድር ከትህነግ (አሸባሪ) ባህርይ ጋር የሚሄድ አይደለም፤ እውቅና መስጠት ነው የሆነብኝ፤ ጊዜ እየገዛን ነው ወይስ ጊዜ እየገዙ፤ በጫና ውስጥ የተደረገ ስምምንት እንደሆነ እገምታለሁ፡፡ ላዩ ወደኛ ያደላ ቢመስልም እነሱም ተሸንፈው አሸንፈውናል፡፡ ስዩም መስፍን የባድሜ ወዘተ. ውሳኔ ላይ ህዝብን ሰልፍ እንዳስወጣው ዓይነት ሆኖብኛል፤
ድርድር ባንገባ ኖሮ፣ መቀሌ ገብተን ቢሆን ኖሮ፣ መሪዎቹን ይዘን ወይም ደምስሰን ቢሆን ኖሮ, … ህግ አስከብረን ቢሆን ኖሮ…