የህ.ወ.ሓ.ት ከሽብርተኝነት መሰረዝ ዘላቂ ሰላምን፣ እፎይታንና ቅቡልነትን የሚያመጣ አይደለም! ኢዜማ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው «ልዩ ጉባኤ» ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት)ን ከአሸባሪነት እንደሰረዘው ማወቅ ችለናል፡፡ ኢዜማ የትኛውም አይነት በሀገራችን ላይ የሚፈጠሩ ልዩነቶች በውይይት መፈታት እንዳለባቸው በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል። በህ.ወ.ሓ.ት ጸብ አጫሪነት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የተነሳውም ጦርነት ላይ ከዚህ የተለየ አቋም አልነበረውም፡፡ በኢዜማ እምነት ውይይት ተደርጎ ችግሮችን መፍታት የሚቻለው የሃሳብ ልዩነት ያላቸው አካላት በሙሉ ልብ ፈቃደኛ እስከሆኑ እና የመንግሥት ስልጣን በኃይል እንደማይያዝ መተማመን ሲኖር ብቻ ነው፤ ሕ.ወ.ሓ.ት እነዚህን ሃቆች ለመቀብል ሳይፈልግ ቀርቶ ጦርነትን ሲያውጅ … [Read more...] about ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ
tplf terrorist
በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ
ከለውጥ ወዲህ መላው የኢትዮጵያ ክፍል ሲታመስ ሰላሙ ተጠብቆ የነበረው በትግራይ ነበር። በአገሪቷ ውስጥ እየተከሰተ ያለው የሰላም መታጣት ያሳሰባቸው እናቶች ወደ ተለያዩ ክልሎች ሄደው ስለ ሰላም ሲማጸኑ ቆይተው ትግራይ ሲደርሱ የተነገራቸው እነርሱንም ያስደመመ ነበር። በወቅቱ ከታቦት እኩል ለአምልኮ የደረሰው ደብረጽዮን የመለሰላቸው በትግራይ ሰላም ነው፤ ሰው ወጥቶ ይገባል፤ ሰላም የታጣው በሌላ ክልል ነው፤ እዚያ ሄዳችሁ ብታለቅሱ ይሻላል ነበር ያላቸው። ሌላው የአገሪቱ ክልል ቀውስ ውስጥ መግባት ዋናው መሪ እና ግጭት ቀማሚ ህወሓት መሆኑን የካደ ግብዝነት የተሞላበት ምላሽ ነበር። እጅግ ከፍተኛ የኢኮኖሚ፣ የማኅበራዊ፣ የፖለቲካ ቀውስ ውስጥ ያለችው ትግራይ እስካሁን ድምጽ ሳይሰማባት ቆይቶ ዛሬ በተቃውሞ ስትናወጥ ውላለች። በጦርነቱ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው በመለስ ዜናዊ አነጋገር … [Read more...] about በጌታቸው ምርጫ ማግስት በትግራይ ሕዝባዊ ዐመፅ ተጀመረ
በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ
ከአድዋ ወደ ራያ የዞረው የትግራይ አስተዳደር አዲስ መሪና ከመሪው ጀርባ የሚያጦዝ አዲስ ስብሃት ነጋን አግኝቷል። አዲሱ የስብሃት ነጋ ምትክ ንጉሥ ፈጣሪ (kingmaker) ጻድቃን ገብረ ትንሳኤ ሲሆን፣ የትግራይ ቲቪ ይፋ እንዳደረገው የትግራይ መሪ የሆነው ጌታቸው ረዳ ነው - ሁለቱም ከአማራ ከተወሰደው ራያ!! በይፋ በሚታዩ መረጃዎች ጌታቸው ረዳ በትግራይ ታጋይ ሳይሆን ትግራይን የመራ ብቸኛ ካድሬ ሆነው ይመዘገባል። ጌታቸው ረዳ ሌላ የሚያስመዘግበው ሪኮርድ ደግሞ በጥላቻና “እረኛውን ምታ በጎቹ ይበተናሉ” በሚል መርህ የተፈለፈሉ ሚዲያ፣ አክቲቪስቶች፣ በአማራና ኦሮሚያ ክልል የብሔራቸው ተቆርቋሪ መስለው ሲንቀሳቀሱና ጥላቻን ሲያሰራጩ የነበሩ፣ በየክልሉ የክልልነት ጥያቄ በማስነሳት ግጭት እና አገር ብጥበጣ ውስጥ የገቡ፣ ሁሉ በጌታቸው አመራር ሥር ስለነበሩ ቆጣሪያቸው … [Read more...] about በትግራይ ሥልጣንና ንጉሥ ፈጣሪነት ከአድዋ ወደ ራያ ተሻገረ
ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው
በኤርሚያስ ለገሰ እና በሃብታሙ አያሌው ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የሚታየው ውዝግብ በርካታዎችን ሲነጋግር የቆየ ነበር። በተለይ በመካከላቸው ጥል እንዳለ በግልጽ በሚታይ መልኩ በአደባባይ እየወጡ የሚናገሩት ከበስተጀርባ ምን እየተደረገ ነው የሚል ጥያቄ ብዙዎች እንዲያነሱ አድርጓቸዋል። አሁን ግን ሁኔታው ግልጽ እየሆነ የመጣ ይመስላል። በኤርሚያስ እና በሃብታሙ መካከል ሰሞኑን የታየው ልዩነት አስመልክቶ ጥቂቶቹን ቪዲዮዎች እንመልከት፤ ከዚህ ሌላ የጌታቸው ሹመት በተሰማበት ቅዳሜ ዕለት እንደተለመደው ከሃብታሙ ጋር ለውይይት መውጣት የነበረበት ኤርሚያስ አልወጣም። ሃብታሙ ከሌላ ግለሰብ ጋር ለወሬ የወጡ ሲሆን በበረከት እና ጌታቸው ሥልታዊ የካድሬ ትንታኔው የበርካታዎችን ቀልብ የሚስው ኤርሚያስ በዚህ ወሳኝ ቀን ለትንታኔ አለመከሰቱ ምናልባት ለጌታቸው “ሹመት ያዳብር” … [Read more...] about ኤርሚያስ ከጌታቸው ረዳ ጋር ምሥጢራዊ የስልክ ግንኙነት ነበረው
አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን
* አሜሪካ ለሰብዓዊ ዕርዳታ የሚውል የ331 ሚሊዮን ዶላር ታደርጋለች * ኢትዮጵያ ወደ አጎዋ ትመለሳለች በመንግሥትና ሕወሓት መካከል ለተደረሰው የሰላም ስምምነት ተግባራዊነት አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኗን በኢትዮጵያ የስራ ጉብኝት እያደረጉ ያሉት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን መናገራቸውን የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ትናንት ምሽት አዲስ አበባ የገቡት የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን፤ ከምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱን የተከታተሉት የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል-አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም፤ በሁለትዮሽና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገ ፍሬያማ ምክክር ማድረጋቸውን ገልጸዋል። በኢትዮጵያና በአሜሪካ … [Read more...] about አሜሪካ ሁለገብ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ ናት – አንቶኒ ብሊንከን
የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ!
ስሙ የክህደት መጠሪያ ሆነ እንጂ የስሙ ትርጉም ግሩም ነው። ይሁዳ የሚለው ቃል በእብራይስጥም “ይሁዳ” ማለት ነው፤ “ያዳ” ነው ሥርወ ቃሉ ይላሉ የሙያው ባለቤቶች። ይህ ደግሞ ትርጉሙ “ማመስገን” ማለት ነው። በግሪክም ትርጓሜው ተመሳሳይ ነው - “የተመሰገነ”፣ “ምስጉን” ማለት ነው። “የአስቆሮቱ” የሚለው ቃል ደግሞ የክፋት መጠሪያ አይደለም። በተለምዶ “የአስቆሮቱ ይሁዳ” በማለት ከሃዲዎችን ስንጠራቸው “አስቆሮቱ” የይሁዳ የክፋት ማዕረግ ይመስለናል። ሊቃውንቱ እንደሚሉን ከሆነ ትርጉሙ “የኬሪዮት ሰው” ወይም “የአራዳ ልጅ” እንደ ማለት ነው ይላሉ። ስለዚህ በከሃዲነቱ ባናውቀው ኖሮ “ተመስገን ያራዳ ልጅ” ብለን እንጠራው ነበር። ስሙ ግን ከግብሩ ፍጹም የራቀ ነው፤ እንዲያውም ተጻራሪ። ይሁዳ ከሃዲ ብቻ አይደለም፤ ማሳካት የሚፈልገው ዓላማ ያለውና የሚያደርገውን … [Read more...] about የውርደት ፖለቲካና ፕሮፓጋንዳ!
“አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ
በአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ ላይ ለመታደም የመጣችው የኒጀር ዜግነት ያላት የፊልም ባለሙያዋ ራህማቶ ኪታ አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም በማድረግ አፍሪካዊያንም እንዲያውቁት ማድረግ ይገባል ብላለች። ባለሙያዋ የፍራንኮ አፍሪካን ፊልም አዋርድን አሸንፋለች። በሥራዎቿ ዙሪያ ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥታለች። የፊልም ጸሐፊ፣ ዳይሬክተር እና ፕሮዲውሰር ራህማቶ ኪታ አማርኛ የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ እንዲኾን በአደባባይ ጥረት የጀመረችው የቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ጋር በማነጋገር መኾኑን አብራርታለች። በቅርቡም ይፋዊ ደብዳቤዋን ለአፍሪካ ኅብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋቂ ማህማት መሥጠቷን አብራርታለች። በተለያዩ የአውሮፓ ሀገራት የታየላት "የጋብቻ ቀለበቱ" የተሰኘው ፊልሟ በፊልሙ ዕይታ ማጠናቀቂያ ላይ የተሳታፊዎችን … [Read more...] about “አማርኛን የአፍሪካ ኅብረት የሥራ ቋንቋ በማድረግ የኢትዮጵያ ብቻ ሣይኾን የአፍሪካም ማድረግ ይገባል” ራህማቶ ኪታ
ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት
የኦሮሚያ ክልል ርእሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ በክልሉ ታጥቆ ለሚብቀሳቀሰው የኦነግ ሸኔ ቡድን የሰላም እና የእርቅ ጥሪ አቀረቡ። ጨፌ ኦሮሚያ በዛሬው እለት መደበኛ ስብሰባውን እያደረገ ይገኛል። አቶ ሽመልስ አብዲሳ መንግሥት የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥ በትኩረት እየሰራ ነው ብለዋል። ጨፌ ኦሮሚያ በዛሬው እለት መደበኛ ስብሰባውን ማድረግ የጀመረ ሲሆን፣ የክልሉ ርእሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ አብዲሳ የክልሉ መንግሥት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበዋል። በዚህም አቶ ሽመልስ፣ "ሰላም ለሁሉም ነገር መሰረት ነው፣ ሰላም በሌለበት ስለ ልማት ማሰብ አይቻልም" ያሉ ሲሆን፣ የኦሮሚያ ክልል መንግሥት የክልሉን ሰላም ለማረጋገጥ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑንም አስታውቀዋል። ርእሰ መስተዳደር አቶ ሽመልስ በንግግራቸው፣ "በዚህ በተከበረው ጨፌው ፊት በክልላችን ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ … [Read more...] about ኦነግ ሸኔ አሸባሪነቱ ሳይነሳለት በሽመልስ የሰላምና የእርቅ ጥሪ “በክብር” ቀረበለት
በሰማዕትነት ጥሪ ቤተመንግሥቱን ባቋራጭ መቆጣጠር
ይህ ለውጥ እውን ከሆነ በኋላ ሕዝብን ስሜታዊ የሚያደረጉ ተግባራት ናቸው በቅስቀሳ መልኩ የሚሰራጩት። ሰው ይገደልና ይሰቀላል። ተሰቅሎ ሲወገር ፊልም ይቀረጻል። ወዲያው ለሕዝብ ላይቭ ይለቀቃል። “እኔ ከእገሌ ብሔር አልተወለድኩም በል” እየተባለ ሰው በማንነቱ ሲገደል የሚያሳይ ፊልም በቅጽበት አየር ላይ እንዲውልና በብርሃን ፍጥነት እንዲሰራጭ ይደረጋል። ንጹሐን እንዲታገቱ ይደረግና እገታው በሚፈለገው መንገድ ተቀነባብሮ በማኅበራዊ ሚዲያ እንዲጎን ይደረጋል። ነፍሰጡር ስትሞት፣ ሕጻን እያየ አባት ሲገደል፣ ንብረት ሲቃጠልና ሌሎች በሟችና በሚወድመው ንብረት ሲዛበቱ የሚያሳይ ምስል በተቀናበረ ሁኔታ በማኅበራዊ ሚዲያዎች ይጦዛል። ይህ በትግራይ፣ በኦሮሚያ፣ በማራ፣ አፋር … ሆኗል። አሁን ደግሞ መልኩን ቀይሮ እየሆነ ነው። ሲሆን ንጹሐን ላይ የደረሰን ጉዳት ለፖለቲካ ገበያ ለማዋል … [Read more...] about በሰማዕትነት ጥሪ ቤተመንግሥቱን ባቋራጭ መቆጣጠር
የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ
ለዘመናት የአፍሪካ ኅብረት ዋና ጽሕፈት ቤትን ከኢትዮጵያ ለማንሳት እጅግ በርካታ ሙከራዎች ተደርገዋል። ይቀርቡ የነበሩት ምክንያቶች ውሃ የማይቋጥሩ ሆነው በመገኘታቸው ሁሉም ስኬት እንደናፈቃቸው መና ሆነው ቀርተዋል። ሙከራው ግን አላቆመም፤ አሁንም ቀጥሏል። ኢትዮጵያ ከትግራይ ሕዝብ ነጻ አውጪ የወንበዴ ቡድን ጋር ጦርነት የገጠመች ጊዜ ይኸው አጀንዳ ቀጠለ። ጦርነቱ ከነበረው በርካታ ድብቅ ዓላማዎች በዋነኛነት የሚጥቀሰው ይህ እንደነበር ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ይመሰክራሉ። በተለይ በኮቪድ ምክንያት የኅብረቱ ስብሰባ ለሁለት ዓመታት በመስተጓጎሉ በዚያው ከኢትዮጵያ ምድር ተረስቶ እንዲቀር ያልተፈነቀለ ድንጋይ አልነበረም። በተለይ የሰሜኑ ጦርነት "በአገሪቱ መረጋጋት የለም" ለሚለው አመክንዮ እንደ ማሳያ ተቆጥሮ ስብሰባው እንዳይካሄድ ከፍተኛ ጫና፣ ግፊት ሲደረግ በነበረበት ወቅት … [Read more...] about የሲኖዶሱ ውዝግብ አካሄድና መጪው የአፍሪካ ኅብረት ጉባዔ










