• Skip to primary navigation
  • Skip to content
  • Skip to primary sidebar

Goolgule

Ethiopian News

  • ስለ እኛ/about
  • አስፈንጣሪዎች/links
  • ቤተ መዝገብ/archives
  • አድራሻችን/contact
Header Banner Image
  • Home
    ዋና ገጽ
  • Editorials
    ርዕሰ አንቀጽ
  • News
    ዜና
  • Socio-Political
    ማኅበራዊ-ሽከታ
  • Religion
    ሃይማኖታዊ
  • Interviews
    እናውጋ
  • Law
    የሕግ ያለህ
  • Opinions
    የኔ ሃሳብ
  • Literature
    ጽፈኪን
    • Who is this person
      እኚህ ሰው ማናቸው?
  • Donate
    ለባለድርሻዎች

ህወሓትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ የወሰናችሁ ሁሉ ተጠያቂዎች ናችሁ – ኢዜማ

March 22, 2023 12:06 pm by Editor Leave a Comment

የህ.ወ.ሓ.ት ከሽብርተኝነት መሰረዝ ዘላቂ ሰላምን፣ እፎይታንና ቅቡልነትን የሚያመጣ አይደለም!

ኢዜማ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ.ም. ባካሄደው «ልዩ ጉባኤ» ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህ.ወ.ሓ.ት)ን ከአሸባሪነት እንደሰረዘው ማወቅ ችለናል፡፡ ኢዜማ የትኛውም አይነት በሀገራችን ላይ የሚፈጠሩ ልዩነቶች በውይይት መፈታት እንዳለባቸው በተደጋጋሚ ሲገልጽ ቆይቷል።

በህ.ወ.ሓ.ት ጸብ አጫሪነት በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የተነሳውም ጦርነት ላይ ከዚህ የተለየ አቋም አልነበረውም፡፡ በኢዜማ እምነት ውይይት ተደርጎ ችግሮችን መፍታት የሚቻለው የሃሳብ ልዩነት ያላቸው አካላት በሙሉ ልብ ፈቃደኛ እስከሆኑ እና የመንግሥት ስልጣን በኃይል እንደማይያዝ መተማመን ሲኖር ብቻ ነው፤ ሕ.ወ.ሓ.ት እነዚህን ሃቆች ለመቀብል ሳይፈልግ ቀርቶ ጦርነትን ሲያውጅ በተቃራኒው ኢዜማ የሀገራችን ህልውና ቅድሚያ የሚሰጠው መሆኑን በፅኑ ስለሚያምን እንደ ፓርቲም ሆነ አባላቱ በጦር ግንባር በመገኘት ከሀገራቸው ጎን ቆመው መስዋዕትነትን ከፍለዋል። ይህንንም በማድረጋችን ትልቅ ሀገራዊ ኩራት ይሰማናል። የዛሬው የውሳኔ ሂደትም ጊዜውን የጠበቀና ትክክል ካለመሆኑም በላይ ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብም ዘላቂ ሰላምን፣ እፎይታንና ቅቡልነትን የሚያመጣ አይደለም፡፡

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ)  የኢትዮጵያ ህዝብ ተወካዮች ም/ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው ስብሰባ የወሰነው ውሳኔን ከዚህ በታች በተጠቀሱት ምክንያቶች የሕ.ወ.ሓ.ትን ከሽብርተኝነት መሰረዝ በጽኑ ይቃወማል፤

1. በፕሪቶሪያው ስምምነት አንቀጽ 6 መሠረት ህ.ወ.ሓ.ት ትጥቅ ሙሉ በሙሉ አለመፍታቱ፤

2. በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት የትግራይን የሽግግር መንግሥትን የፌደራሉ መንግሥት በበላይነት እንዲያቋቁም ስምምነት ላይ ቢደረስም አሁንም ሕ.ወ.ሓ.ት በብቸኝነት የሽግግር መንግሥቱ አውራ ኾኗል። ይኽም ሕ.ወ.ሓ.ት ዳግም የሀገር ስጋት የሚኾንበትን ዕድል እንደመስጠት የሚቆጠር ነው። የሰላም ስምምነቱ ትግበራ እና ውጤት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ በማሳረፍ በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዳይሰፍን እንቅፋት እንዳይሆን ያሰጋናል፡፡ በመሆኑም የፌደራል መንግሥቱ የስምምነት ግዴታዎቹን ሲወጣ ሕወሓትም ስምምነት ድንጋጌዎቹን ማክበሩን በጋራ በተቋቋመው ጥምር ኮሚቴ መረጋገጡን ከግምት እያስገባ መኾን ነበረበት፤

3. በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት እንዲፈጸም ያዘዙ፣ ሰብዓዊ ቀውስ ያደረሱ፣ ዜጎችን በጦርነት እንዲማቅቁ ያደረጉ፣ የሀገር ኢኮኖሚና፣ በአጠቃላይ ኢትዮጵያን ቀውስ ውስጥ የከተቱ የሕ.ወ.ሓ.ት አመራሮች በሕግ አለመጠየቃቸው፤

4. በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት የሀገር መከላከያ ሠራዊት ሙሉ በሙሉ ትግራይን እንዲቆጣጠር አለመደረጉ፤

5. የተጨፈጨፉ የሰሜን ዕዝ አባላት የመስዋዕትነት ምልክት የሚኾን ሐውልት ወይም ማስታወሻ በሰሜን ዕዝ ዋና ማዘዣ አለመደረጉ፤

6. በህ.ወ.ሓ.ት ቆስቋሽነት ሀገራችን ላይ ለደረሰው ውድመትና ሰቆቃ ፍትሕ እና ካሣ አለመሰጠቱ፤

7. ህ.ወ.ሓ.ት የሚለው የፖለቲካ ድርጅት ስም በሕግ እንዲታገድ አለመደረጉ እነዚህ ከላይ የተዘረዘሩ ቅድመ ሁኔታዎች ሳይሟሉ የሕ.ወ.ሓ.ትን ቡድን ከሽብርተኝነት ሰርዞ ከተጠያቂነት ነፃ ማድረግ ሊቀለበስ የማይችል ጥፋት ነው። ከዚህ በኋላ በህ.ወ.ሓ.ት አማካኝነት ለሚደርስ ሀገራዊ ጉዳትም ዋነኛ ተጠያቂዎች ገዢው የብልጽግና ፓርቲ እና መንግሥት እንደሚኾኑ ከወዲሁ መግለጽ እንወዳለን።

ምክር ቤቱ ሌላው ቢቀር በፕሪቶሪያው ስምምነት መሠረት ግዴታዎች አየተፈፀሙ መሆኑን በቅጡ ሳያረጋግጥ፣ ሕ.ወ.ሓ.ት በኢትዮጵያ ሕዝብ እና መንግሥት ላይ ለፈጸመው የሀገር ክህደት ወንጀል ተጠያቂ ሳይሆን እና በሕ.ወ.ሓ.ት የእብሪት ጦርነት የግፍ ገፈት ቀማሽ ለሆኑ በተለይ በትግራይ፣ በአማራ እና በአፋር ለሚገኙ ወገኖቻችን ፍትሕ ሳይሰጥ ቡድኑን ከሽብርተኝነት መዝገብ እንዲሰረዝ መወሰኑ ታሪክ ይቅር የማይለው ፍርደ ገምድልነት  ነው።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል የተከሰተው ጦርነት እና እሱን ተከትሎ ለደረሰው ሀገራዊ ቀውስ ቁጥር አንድ ተጠያቂ የሕ.ወ.ሓ.ት የሽብር ቡድን እንደኾነ ያምናል፡፡ ሕ.ወ.ሓ.ት የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት የሰሜን ዕዝ አባላትን በመጨፍጨፍ የሀገር ክህደት ፈጽሟል፡፡ የትግራይን ክልልን ሕዝብ ከወገኖቹ ኢትዮጵያዊያን ጋር እርስ በእርስ እንዲተላለቁ እንዲሁም የሀገር ኢኮኖሚ እንዲወድም ያደረገው ይኸው ህወሓት የተሰኘ ድርጅት ነው፡፡ ይህን የመሰለ ታላቅ ወንጀል የፈፀመ ቡድን ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ከአሸባሪነት መዝገብ እንዲፋቅ ማድረግ በሕዝብ፤ በፍትሕ እና በሀገር ሉዓላዊነት  ላይ በደል መፈጸም ነው፡፡ የሀገር ክህደት ወንጀል የፈጸሙ ግለሰቦችን እና ቡድኖችን ያለምንም ተጠያቂነት እና መተማመኛ ከሽብርተኝነት ነፃ ማውጣት ሽብርተኝነት እና የሀገር ክህደት መፈጸምን ለሌሎች ማለማመድ መኾኑን አለመገንዘብ ሀገር ከሚመሩ ኃይሎች የማይጠበቅ አሳፋሪ ድርጊት ነው፡፡ እጅ አውጥተው ይህንን ውሳኔ የደገፉ የሕዝብ ተወካዮች በስሙ እንደራሴ የኾኑለትን የኢትዮጵያ ሕዝብ መብት እና ጥቅምም በአደባባይ እንደናዱት መገንዘብ ይኖርባቸዋል፡፡

ኢዜማን ወክለው በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተመረጡ እንደራሴዎቻችን ህ.ወ.ሓ.ት ከሽብርተኝነት እንዳይሰረዝ ብርቱ ሙግት አድርገዋል። ድምፃቸውንም በተቃውሞ አስመዝግበዋል። በዚህ አጋጣሚ ህ.ወ.ሓ.ት ከአሸባሪነት መነሳት እደሌለበት በምክንያት አስረድታችሁ ውሳኔውን በመቃወም ከታሪክ ተጠያቂነት ራሳችሁን ነፃ ያወጣችሁ የምክር ቤት አባላት ምስጋና ይገባችኋል፡፡

ህ.ወ.ሓ.ትን ከሽብርተኝነት እንዲሰረዝ ውሳኔ ያሳለፋችሁ የገዢው ፓርቲ አመራሮች እና አባላት በህወሓት ቡድን ለተፈጸመው የሀገር ክህደት ወንጀል፣ የሉዓላዊነት መደፈር፣ የሕዝብ ሰቆቃ እና የኢኮኖሚ ውድመት ዕውቅና በመስጠታችሁ እና ተጠያቂነት ባለማስፈናችሁ በእንደራሴነታችሁ የተጎናጸፋችሁትን “ለሕግ፣ ለሕዝብ እና ለህሊና” ተጠሪነታችሁን ከመደምሰሳችሁም በላይ የህወሓት ጥፋት ወራሾች እና የተፈጸሙ ወንጀሎች ተጠያቂዎች መኾናችሁንም እንገልጻለን።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ  (ኢዜማ)

መጋቢት 13 ቀን 2015 ዓ.ም.

Filed Under: Left Column, Politics Tagged With: ethiopian terrorists, ezema, operation dismantle tplf, tplf, tplf terrorist

Reader Interactions

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Primary Sidebar

Recent Posts

  • በትግራይ በወራት ጊዜ ውስጥ ክልላዊ ምርጫ ለማካሄድ ዝግጅት እየተደረገ ነው October 4, 2026 01:20 am
  • የትህነግ ከፍተኛ ወታደራዊ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በተፈናቃዮች ላይ አዲስ አፍና ታወጀ October 1, 2026 02:18 pm
  • ትህነግ የራሱን ታጣቂዎች ለማስረሽን የኤርትራ ገዳይ ስኳድ (Hit Squad) ማስገባቱ ተሰማ፤ “አፈሙዛችንን ወደ አመራሩና ወደ ኤርትራ እናዞራለን” ታጣቂው October 1, 2026 11:08 am
  • ትህነግ፤ እጅግ ከፍተኛ የጦር መሣሪያዎችን አስረክቦ ወደ ትግራይ መፈርጠጡ ተሰማ September 29, 2026 07:27 am
  • በስታሊን ገብረሥላሴ በአሜሪካ የሕግ እርምጃ እንዲወሰድ ጥሪ ቀረበ September 27, 2026 11:27 pm
  • Stalin Gebreselassie’s Social Media Post on Bole Airport Calls for U.S. Legal Action September 27, 2026 10:48 pm
  • ከትህነግ ጎን የተሰለፉ ከ2,000 በላይ የሻዕቢያ ታጣቂዎች በርካታዎቹ ተደመሰሱ September 27, 2026 12:42 pm
  • የትህነግ እና የኡጉጉሞ ከፍተኛ አመራሮች ተደመሰሱ፤ በሰሜን ወሎ፣ ሰቆጣ እና አፋር በርካታ አዛዦች ሙት እና ቁስለኛ ሆኑ September 27, 2026 11:46 am
  • “ህወሓት ጉድ ሠራን” — በሰሜን ወሎ የሚንቀሳቀሰው የፋኖ ቡድን ተበታትኖ ተስፋ መቁረጡ ተገለጸ September 27, 2026 11:27 am
  • “ማጥቃት ከጀመርን ትግራይ ላይ አንቆምም፤ ግባችን ቀይ ባህር ላይ ባንዲራ መትከል ነው” ጄኔራል አበባው September 27, 2026 10:15 am
  • የትህነግና ተባባሪዎቹ የጥፋት መዋቅር እያበቃለት ነው September 26, 2026 10:09 pm
  • የትህነግ፣ የሻዕቢያ፣ የአገው ሸንጎ እና የፋኖ ጥምረት በሰቆጣና አብዓላ ግንባሮች ተደመሰሰ September 25, 2026 11:07 pm
  • የትህነግ ታጣቂዎች በከፍተኛ ሁኔታ እየተመቱና እየተበታተኑ ይገኛሉ September 25, 2026 02:39 pm
  • የሶማሌ ክልል በሦስት ዋና ዋና የአስተዳደር ቀጣናዎች (ክላስተር) ሊዋቀር ነው September 24, 2026 10:20 pm
  • የአሜሪካ መንግሥት ትህነግ “ሊያሸንፈው የማይችለውን” ከንቱ ጦርነት መጀመሩን በጥብቅ ኮነነ September 23, 2026 10:20 pm
  • በራያና ሰሜን ወሎ በተደረገ የድሮን ጥቃት፤ ከ270 በላይ ታጣቂዎች ተገደሉ September 22, 2026 10:56 pm
  • ኢትዮጵያ ጨምሮ የቀይ ባሕር ሀገራት ቀጣናዊ ስጋቶች በመጨመራቸው የባሕር ትብብር ለማጠናከር ወሰኑ August 28, 2026 11:32 am
  • የመካነ ኢየሱስ ሕንጻ የጠራራ ፀሐይ ወግና “የብሌን ሠራዊት” በችሎት ደጃፍ August 5, 2026 02:35 am
  • ለሱዳንና ኤርትራ ሲከራከሩ የነበሩት አበባው ባለመመረጣቸው “በጣም ተድጃለሁ” አሉ June 26, 2026 12:29 am
  • “ትህነግ ወደ ዓለምአቀፍ ወንጀለኛነትና አሸባሪነት እየተምዘገዘገ ነው” June 25, 2026 01:00 am
  • አሜሪካ በሕገወጡ ትህነግ አመራሮች ላይ ጠንካራ የቪዛ እገዳ ጣለ June 18, 2026 10:29 am
  • እንደ ሌሊት ወፏ የሚንቀሳቀሰው ኢህአፓ/ትብብር   June 18, 2026 09:36 am
  • የታርጋ ጫጫታ June 15, 2026 05:16 pm
  • ፋንታኹን ዋቄ ከአሜሪካ የሃይማኖት እልቂት አወጁ June 15, 2026 02:12 am
Copyright © 2026 · Goolgule